Logo
Getu Temesgen
የ80 ዓመቱ ዩዌሪ ሙሴቬኒ፤ በመጪው ዓመት ለሚካሄደው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ዕጩ ሆነው ቀረቡ
#ethiopia | የ80 ዓመቱ ዩዌሪ ሙሴቬኒ፤ በመጪው ዓመት ለሚካሄደው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ የገዢው ፓርቲ ዕጩ ሆነው በመመረጥ፤ 40 ዓመት ገደማ የቆዩበት ስልጣን ማስቀጠል የሚችሉበትን መንገድ አመቻችተዋል፡፡

ፕሬዝዳንት ሙሰቬኒ እጩ ሆነው ከተመረጡ በኋላ ባደረጉት ንግግር ለምርጫ እንዲቀርቡ ለተደረገላቸው ጥሪ ምላሽ መስጠታቸውን ገልጸዋል።

ከተመረጡም የኡጋንዳን ወደ "ከፍተኛ መካከለኛ ገቢ ያላት ሀገር" እንድትሆን የማድረግ ተልዕኮአቸውን እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል።

የሙሴቬኒ ተቺዎች፤ ፕሬዝዳንቱ እ.አ.አ በ1986 የአማጺ ቡድን መሪ ሆነው የሀገሪቱን ሥልጣን ከተቆናጠጡበት ጊዜ አንስቶ ሀገሪቱን በአምባገነንነት ሲገዙ መቆየታቸውን ያነሳሉ።

ፕሬዝዳንቱ ስልጣን ከያዙ ጊዜ ጀምሮ በተደረጉት ምርጫዎች ሁሉ አሸንፈዋል።

በስልጣን ላይ እንዲቆዩ ለማድረግም ለፕሬዝዳንትነት በሚወዳደሩ እጩዎች ላይ የተቀመጡት የዕድሜ እና የሥልጣን ዘመን ገደቦችን ለማስወገድ ሲባልም የሀገሪቱ ህገ መንግሥት ሁለት ጊዜ ተሻሽሏል።

በሚቀጥለው ዓመት ጥር በሚካሄደው ምርጫ የሙሴቬኒ ዋና ተፎካካሪ ይሆናል ተብሎ የሚጠበቀው ከፖፕ ሙዚቃ አቀንቃኝነት ወደ ፖለቲከኛነት የተለወጠው ቦቢ ዋይን ነው።

ዋይን፤ 'ናሽናል ዩኒቲ ፕላትፎርም' የተሰኘው ፓርቲው በእጩነት እንዲቀርብ የሚመርጠው ከሆነ ከሙሴቬኒ ጋር እንደሚፎካከር በሚያዝያ ወር ለቢቢሲ ተናግሮ ነበር። #ethiofm

11 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.