Logo
Getu Temesgen
የኬኒያው ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ተቃዋሚዎችን አስጠንቅቀዋል
#ethiopia | ፕሬዝዳንቱ በኬኒያ እየተቀሰቀሰ ባለው ተቃውሞ ትእግስታቸው እየተሙዋጠጠ እንደሆነ አሳስበዋል ፡፡

ፕሬዝዳንት ሩቶ በተቃውሞ መንግስትን ለመገልበጥ በሃገሪቱ ሴራ እንዳለ የገለጹ ሲሆን የፖለቲካ ተቀናቃኞቻቸው መንግስታቸውን በሴራ ለመጣል እየሞከሩ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

ዊሊያም ሩቶ ከጥቂት ጊዜያት ወዲህ በተቃዋሚዎች በፖሊስ ጣቢያዎች ላይ የሚደርሰው ጥቃት እንደ ጦርነት ይቆጠራል ሲለዚህም ትእግስታችን እየተሙዋጠጠ ነው ሲሉ አስጠንቅቀዋል፡፡

ፕሬዝዳንቱ ባደረጉት ንግግር የኬኒያ ህዝብ ዲሞክራሲያዊ ህዝብ ነው ስለዚህም ኬኒያውያን የሃገራቸውን መሪ በምርጫ ይመርጣሉ ስለዚህም በአመጽ መሪን መቀየር በዚች ሃገር የሚሆን አይደለም ብለዋል፡፡

ሆኖም በኬኒያ የፖሊስ ከልክ ያለፈ ጭካኔ የኢኮኖሚ ቀውስ እና ሙስና እንዲሁም ሌሎችም የመልካም አስተዳደር ችግሮች ምክኒያ ኬኒያውያን ጠንከር ያለ ተቃውሞ ማሰማታቸው ተገልጹዋል፡፡

ከቅርብ ቀናት ወዲህ በሚደረጉ የተቃውሞ ሰልፎች ኬኒያ በተረጋጋ ሁኔታ ላይ እንደማትገኝ በማህበራዊ ድረገጾች ላይ የተሰራጩት ተንቀሳቃሽ ምስሎች ያሳያሉ፡፡

ፕሬዚዳንት ሩቶ የኬኒያን ሰላም ለማስጠበቅ ያለውን ማንኛውንም መንገድ እጠቀማለሁ ሲሉ አስጠንቅቀዋል፡፡

ከዚህ ቦሃላ በህግ ተቁዋማት ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶችንም እንደማይታገሱ ማሳሰባቸውን #ethiofm

1 year ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.