Logo
Getu Temesgen
የአይን ብሌን የሚሰበስቡ ባለሙያዎች ቁጥር እጅግ አነስተኛ መሆናቸው ተገለፀ
#ethiopia | እንደ ሀገር በጅማ ስልጠና እየወሰዱ ያሉ 3 ባለሙያዎችን ጨምሮ የአይን ብሌን የሚሰበስቡ 9 ባለሙያዎች ብቻ መኖራቸውን የኢትዮጲያ ደም እና ህብረ ህዋስ ባንክ አገልግሎት አስታውቋል፡፡

የአገልግሎቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ሀብታሙ ታዬ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳሉት፤ ስልጠናው ከሀገር ውጪ በመሄድ መወሰድ ያሉባቸው ስልጠናዎችን የሚጠይቅ እና ግብዓቱም በስፋት ሀገር ውስጥ ባለመገኘቱ ሰፊ ስራን የሚፈልግ ነው ብለዋል፡፡

በሀገራችን እንደ አጠቃላይ የአይን ብሌን ንቅለ ተከላ መስራት የሚችሉ ባለሙያዎች 13 ብቻ መሆናቸውንም ገልፀዋል፡፡

በተጠናቀቀው 2017 በጀት ዓመት ወደ 3መቶ10 የአይን ብሌን ለመሰብሰብ ታቅዶ 3መቶ50 የሚሆን የአይን ብሌን ማንሳት መቻላቸውን ነዉ የነገሩን፡፡

እንዲሁም አይን ብሌናቸውን ለመለገስ ቃል የገቡ ሰዎች ቁጥር 7መቶ19 እንደሆኑ ተናግረዋል፡፡

እንደ ሀገር ያለው የአይን ባንክ አዲስ አበባ ከተማ ብቻ ያለ በመሆኑ ክልሎች አካባቢ የተደራሽነት ጥያቄዎች መኖራቸውንም ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ አንስተዋል፡፡

ይህንንም በመገንዘብ ጅማ ላይ ዝግጅት ሲደረግ መቆየቱን እና ባለሙያዎችም ስልጠናዎችን ወስደው በመጨረስ ላይ እንደሚገኙ አስታውቀዋል፡፡

በአጠቃላይ ቀደም ሲል ካለው የተሻለ የአይን ብሌን መሰብሰብ መቻሉን እንዲሁም የአይን ብሌናቸውን ለመለገስ ቃል የሚገቡ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን አቶ ሀብታሙ ተናግረዋል፡፡ #ethiofm

11 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.