ታጣቂዎች ከ200 በላይ ተማሪዎችና ሠራተኞችን ከትምህርት ቤት አግተው ወሰዱ፤ ፕሬዜዳንቱም የቡድን 20 ጉባዔ ተሳትፏቸውን ሰረዙ
#ethiopia | በማዕከላዊ ናይጀሪያ የናይጄሪያ ክርስቲያኖች ማኅበር እንደገለጸው አርብ ማለዳ ታጣቂዎች ወደ ትምህርት ቤቱ በመግባት 215 ተማሪዎች እና 12 ሠራተኞችን ወስደዋል።
እገታው የተፈጸመው በኒጀር ግዛት ፓፓሪ በሚገኘው የቅድስት ማርያም ትምህርት ቤት ሲሆን፣ ባለሥልጣናቱ በፀጥታ ስጋት ምክንያት ሁሉም አዳሪ ትምህርት ቤቶች በጊዜያዊነት እንዲዘጉ ትዕዛዝ ሰጥተው ነበር።
የጅምላ እገታው በዚህ ሳምንት ለሁለተኛ ጊዜ የተፈጸመ ነው። ሰኞ ዕለት በኬቢ ግዛት ከሚገኝ አዳሪ ትምህረት ቤት ከ20 በላይ ሴት ተማሪዎች ታግተው ተወስደዋል ተብሏል።
እንዲሁም፣ በክዋራ ግዛት የሚገኝ አንድ ቤተ ክርስትያን የአምልኮ ሥነ ስርዓቱ በቀጥታ ስርጭት እየተላለፈ በተፈፀመ ጥቃት ሁለት ምዕመናን ሲገደሉ 38 ደግሞ ታግተው ተወስደዋል።
ፕሬዝዳንት ቦላ ቲኑቡ እነዚህን የጸጥታ ጉዳዮች ለመፍታት በሚል በዚህ ሳምንት መጨረሻ በደቡብ አፍሪካ የሚካሄደው የቡድን 20 ጉባኤ ላይ እንደማይሳተፉ አስታውቀዋል። #ethiofm

6 months ago