በህዳሴ ግድብ ላለዉ የአሳ ሀብት የአስተዳደር ልዩ መመሪያ መፅደቁ ተገለፀ
#ethiopia | በህዳሴ ግድብ ላይ የተገኘዉን የአሳ ሀብት ለማልማት እንዲቻል እና ሀብቱንም ለመጠበቅ የሚያስችል የአሳ ሀብት አስተዳደር ልዩ መመሪያ ተዘጋጅቷል ተብሏል።
ከጣቢያችን ጋር ቆይታ ያደረጉት በግብርና ሚኒስቴር የእንስሳት ሀብት ልማት ዘርፍ ሀላፊ ዶ/ር አለማየሁ መኮንን፤የአሳ ሀብቱ እንዳይሟጠጥ ለመጠበቅ እየተሞከረ እንደሆነ ይገልፃሉ።
ምን አይነት አሳ በምን አይነት ማጥመጃ መጠቀም ያስፈልጋል የሚለዉ ሁሉ መመሪያ እንደወጣላቸዉ ሀላፊዉ ገልፀዋል።
በዉሃ ክፍሉ የትኛዉ አካባቢ ነዉ ከፍተኛ የአሳ ምርት ያለዉ እና ምን አይነት ዝርያዎች የሚለዉን እየለዩ መጠቀም የሚቻልበት እንደሚሆን ዶ/ር አለማየሁ አንስተዋል።
የአሳ ሀብቱን በአግባቡ ለማስተዳደር ባለድርሻ አካላት እና የሙያ ዘርፉ ባለሙያዎች ባሉበት መመሪያዉ የጋራ ስምምነት ላይ በመድረስ መፅደቁን ሰምተናል።
በቀጣይ መመሪያ የትግበራ ምዕራፍ ላይ የሚደረስበት ይሆናል ተብሎ እንደሚጠበቅም ሀላፊዉ አክለዋል።
በቦታዉ በቀን 14 ሺህ ኪሎ ግራም ዓሣ የማምረት አቅም መፈጠሩን በቅርቡ የግብርና ሚኒስቴር ያወጣው መረጃ ያመላክታል።
#ethiofm

12 months ago