9 hours ago
የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከቪዛ ኩባንያ ጋር በመተባበር አዲስ ዓለም አቀፍ የክፍያ ካርድ ይፋ አደረጉ
*************
የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከዓለም አቀፉ ቪዛ ኩባንያ ጋር በመተባበር፣ ደንበኞች በየትኛውም የዓለም ክፍል ሆነው በቀላሉ ግብይት እንዲፈጽሙ የሚያስችል አዲስ የተቀናጀ ዓለም አቀፍ የክፍያ ካርድ በይፋ አስጀምረዋል።
ይህ አዲስ የክፍያ ካርድ በተለይም የኢትዮጵያ አየር መንገድ የ“ሸባ ማይልስ” አባላት የሆኑ መንገደኞች በሚደርሱበት ማንኛውም የዓለም መዳረሻ ፈጣን፣ ቀላል እና አስተማማኝ ክፍያዎችን እንዲፈጽሙ ዕድል ይሰጣቸዋል።
ካርዱ የዕለት ተዕለት ግብይቶችን ከማቅለሉ ባሻገር፣ ለአጠቃቀም እጅግ ቀላልና አስተማማኝ የደኅንነት ጥበቃ ሥርዓት ያለው መሆኑ ተገልጿል። በተጨማሪም የሦስቱንም ተቋማት ዓርማና ምልክት በአንድ ላይ የያዘ ነው።
አዲሱ ዓለም አቀፍ የግብይት ካርድ ለደንበኞች ልዩ ልዩ ሽልማቶችንና ጥቅማጥቅሞችን የሚያስገኝ ሲሆን፣ ለአዲስም ሆነ ለነባር የኢትዮጵያ አየር መንገድ ደንበኞች ክፍት መሆኑ ተረጋግጧል።
የአገልግሎቱ ተጠቃሚዎች በየጉዟቸው የሚያደርጉት ግብይት ተጠራቅሞ ወደ ጉዞ ዕድል (ማይልስ) የሚቀየርላቸው ሲሆን፣ ካርዱን በሽያጭ ማሽን (POS) ወይም በኢ-ኮሜርስ (e-commerce) አማካኝነት ለኦንላይን ግብይት በሚጠቀሙበት ወቅትም ለተጨማሪ ሽልማቶች ያላቸውን ዕጩነት በከፍተኛ ደረጃ ያሰፋላቸዋል።
ይህ አገልግሎት የሮያሊቲ (ታማኝ) ደንበኞችን ክብርና ጥቅማጥቅም ከመጠበቁ በላይ፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የደንበኞቹን ዘመናዊ ፍላጎት ለማሟላት ለሚያደርገው ጉዞ ትልቅ ፋይዳ እንዳለው ተጠቅሷል።
በሌላ በኩልbox እነዚህ ሁለቱ አንጋፋ ሀገራዊ ተቋማት ከዓለም አቀፉ ቪዛ ካርድ ጋር በጋራ ለመሥራት መፈራረማቸው ተቀባይነታቸውንና የገበያ ድርሻቸውን ይበልጥ የሚያሳድግላቸው ሲሆን፣ ለቪዛ ካርድም ቢሆን በማደግ ላይ ወዳሉ ሀገራት ገበያ ለመግባትና ተደራሽነቱን ለማስፋት ምቹ የሥራ ዕድል እንደሚፈጥርለት ተገልጿል።
በሳራ ሳህለሥላሴ
#commercialbankofethiopia #ethiopianairlines #visacard #cobrandedcard #shebamiles #digitalpayment #ethiopianbroadcastingcorporation

15 days ago
ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተሰጠ አስቸኳይ መግለጫ!
* የታገዱ ሂሳቦች መፍትሄ አገኙ
#ethiopia | ለተከበራችሁ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ (CBE) ውድ ደንበኞች በሙሉ፤ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መመሪያ መሠረት፣ በተመረጡ ከተሞች የሚገኙና ከ"ፋይዳ" መታወቂያ ጋር ያልተሳሰሩ የባንክ ሂሳቦች ላይ ተጥሎ የነበረው የእንቅስቃሴ እገዳን በተመለከተ ባንኩ አዲስና ፈጣን መፍትሄዎችን የያዘ መግለጫ አውጥቷል።
የእገዳው መነሻና አዲሱ መፍትሄ
እስከ ግንቦት 06 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ የፋይዳ መታወቂያ ቁጥራቸውን ከባንክ ሂሳባቸው ጋር ያላስተሳሰሩ ደንበኞች ሂሳባቸው እንዳይንቀሳቀስ ተደርጎ መቆየቱ ይታወሳል።
ይህንን ተከትሎ የደረሰውን ከፍተኛ የደንበኞች ጫና ለመቋቋም ባንኩ የሚከተሉትን እርምጃዎች ወስዷል፦
1. የታገዱ ሂሳቦች መለቀቅ
ከግንቦት 7 እስከ ግንቦት 12 ቀን ድረስ በእገዳ ምክንያት እንዳይንቀሳቀሱ ከተደረጉት ሂሳቦች ውጪ፣ የፋይዳ መታወቂያቸውን ያስተሳሰሩ ደንበኞች ሂሳባቸውን ወዲያውኑ ማንቀሳቀስ እንዲችሉ ተደርጓል።
2. አውቶማቲክ እገዳ ማንሳት
ከግንቦት 12 ጀምሮ ደንበኞች የፋይዳ መታወቂያቸውን ከሂሳባቸው ጋር እንዳስተሳሰሩ፣ የባንኩ የመረጃ ስርዓት (System) **በራሱ ጊዜ እገዳውን እንዲያነሳ** ተደርጓል።
አዲስ የቀነ-ገደብ ማሳሰቢያ
እስካሁን ያላስተሳሰሩ እና በሌሎች የሀገሪቱ ክፍሎች የሚገኙ ደንበኞች፣ የፋይዳ መታወቂያቸውን እስከ ሰኔ 30 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ በማስተሳሰር ሂሳባቸውን በቀጣይነት ማንቀሳቀስ እንዲችሉ ባንኩ በጥብቅ አሳስቧል።
የማስተሳሰሪያ አማራጮች፦
በማንኛውም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ በአካል በመገኘት።
በባንኩ የበይነ መረብ (Online) ማስተሳሰሪያ አማራጭ፦ 👉 https://cbefayda.cbe.com.e...
ባንኩ ደንበኞች በመጉላላታቸው ይቅርታ የጠየቀ ሲሆን፣ የደንበኞችን እርካታ እውን ለማድረግ መስራቱን እንደሚቀጥል አረጋግጧል።
#getu #cbe #commercialbankofethiopia #nationalid #faydaid #bankblockethiopia #onlineregistration #systemupdate #customersatisfaction #ሰበርዜና #ኢትዮጵያንግድባንክ #ፋይዳመታወቂያ #የባንክእገዳ #የዲጂታልኢትዮጵያ #ጌጡተመስገን #getutemesgen

4 months ago
🏦 የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከ91% በላይ ብድሩን ለግሉ ዘርፍ መስጠቱን አስታወቀ
#ethiopia | "በግማሽ ዓመት 293.9 ቢሊዮን ብር ለግል ባለሀብቶች እና ድርጅቶች ቀርቧል"
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተጠናቀቀው ግማሽ የበጀት ዓመት ያቀረበው የብድር መጠን ለግሉ ዘርፍ (Private Sector) ትልቅ ትኩረት የሰጠ መሆኑን ገለጸ።
ቁልፍ የብድር መረጃዎች:
💰 ጠቅላላ ብድር: ባንኩ በግማሽ ዓመቱ በአጠቃላይ 321 ቢሊዮን ብር ብድር አቅርቧል።
🏭 የግሉ ዘርፍ ድርሻ: ከጠቅላላው ብድር ውስጥ 293.9 ቢሊዮን ብሩ (91%) ለግሉ ዘርፍ የተሰጠ ነው።
☪️ ሲቢኢ ኑር: ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት (CBE Noor) ተጠቃሚዎች 51.3 ቢሊዮን ብር የብድር አቅርቦት አግኝተዋል።
ብድሩ ለማን ቀረበ?
ለአምራች ኢንዱስትሪዎች
ለአስመጪ እና ላኪዎች
በአገልግሎት ዘርፍ ለተሰማሩ
ለሌሎች የኢንቨስትመንት መስኮች
ይህ እርምጃ የግሉን ዘርፍ የኢኮኖሚ ተሳትፎ ለማሳደግ ትልቅ ሚና ይጫወታል ተብሎ ይታመናል።
#cbe #commercialbankofethiopia #privatesector #loan #economy #ethiopia #cbenoor #investment

5 months ago
አጠቃላይ ተቀማጭ ገንዘቤ ከ2 ትሪሊዮን ብር በላይ ደረሰ
- የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
#ethiopia | አንጋፋው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ (CBE) አጠቃላይ የተቀማጭ ገንዘብ መጠኑን ከ2 ትሪሊዮን ብር በላይ በማድረስ በታሪኩ ከፍተኛውን ውጤት ማስመዝገቡን አስታወቀ።
ባንኩ ይፋ ባደረገው መረጃ መሠረት፣ ይህ አሃዝ በኢትዮጵያ የባንክ ኢንዱስትሪ ውስጥ አንድ የፋይናንስ ተቋም የደረሰበት ከፍተኛው የተቀማጭ ገንዘብ መጠን ነው።
የባንኩ ተጨማሪ ስኬቶች 🔎
*የዲጂታል ባንክ አገልግሎት መስፋፋት፦ የሲቢኢ ብር (CBE Birr) እና የሞባይል ባንኪንግ ተጠቃሚዎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ መጨመር።
*የቅርንጫፎች ተደራሽነት፦ ባንኩ በሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች ያለውን የቅርንጫፍ ተደራሽነት በማስፋፋት አዳዲስ ደንበኞችን ማፍራቱ።
* የቁጠባ ባህል ማሳደግ፦ ማህበረሰቡ ገንዘቡን በባንክ የማስቀመጥ ልምዱ እያደገ እንዲመጣ ማስቻሉ።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ይህንን ግዙፍ ካፒታል ለሀገራዊ የልማት ፕሮጀክቶች ፋይናንስ ለማድረግና ለግል ዘርፉ የብድር አቅርቦት ለማዋል ትልቅ አቅም እንደሚፈጥርለት ተረድተናል። ባንኩ በቀጣይ አገልግሎቶቹን ይበልጥ በማዘመንና ተወዳዳሪነቱን በማሳደግ የኢኮኖሚውን እድገት ለመደገፍ እንደሚሰራ ይጠበቃል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#cbe #commercialbankofethiopia #ethiopianeconomy #bankingnews #financeethiopia #digitalbanking #2trillion