6 months ago
🚧 የመረሐቤቴ መንገድ፡ የትናንት ታሪክ፣ የዛሬ እንግልት እና የነገ ተስፋ!
"ታሪክ የሚሰራው በመንገድ ብቻ ሳይሆን በህብረት ነው!"
#ethiopia | የመረሐቤቴ መንገድ ጉዳይ የረጅም ዘመን የህዝብ ጥያቄ ነው። በ1950ዎቹ አባቶቻችን በዶማ እና በማረሻ እግር በእግር ተጉዘው የሰሩት ይህ መንገድ፤ ዛሬ ላይ ለዘመናት የጠየቀውን እንክብካቤ አላገኘም።
ከታሪክ ማህደር:
ከደጃዝማች ሸዋረገድ እስከ ደጃዝማች ገለታ ቆርቾ፤ ከዚያም እስከ ሻለቃ ጌታቸው መንግስቴ ድረስ የነበሩ አባቶች በህዝብ ተሳትፎ የሰሩት ታሪክ አይረሳም።
የአሁን እውነታ:
ላለፉት 40 ዓመታት አካባቢ መንገዱ ስር ነቀል ለውጥ አላገኘም። በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ፡-
1️⃣ የተጀመረው የኮኮብ መስክ - ጀማ የአስፓልት ስራ በመቋረጡ፣
2️⃣ ከጀማ - አለም ከተማ ያለው መንገድ ከፍተኛ ጥገና በማጣቱ፣
3️⃣ የስሚንቶ ፋብሪካው የጭነት መኪኖች ጫና በመፍጠራቸው ህዝቡ ለእንግልት ተዳርጓል።
ተስፋ እና ጥሪ:
የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን (ERA) ችግሩን ተረድቶ የተቋረጠውን የአስፓልት ግንባታ እና የጥገና ስራ ለማስጀመር ዝግጁነቱን ገልጿል።
ይህ መልካም ዜና ቢሆንም፤ ቃሉ ወደ ተግባር እስኪቀየር ድረስ፡-
የአካባቢው ተወላጆች፣
የሀገር ሽማግሌዎች እና
የህዝብ ተወካዮች ከመቼውም ጊዜ በላይ ተባብረን መንግስትን መጠየቅ አለብን።
አባቶቻችን በጉልበት የሰሩትን መንገድ፤ እኛ በህብረት እናልማው!
#ንጉሥ ወዳጅነው
#merhabete #roadproject #infrastructure #history #jemma #alemketema #ethiopia #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን

🚧 የ1.3 ቢሊዮን ብር ፕሮጀክት! የቱሉቦሎ-ኬላ አስፋልት መንገድ ተመረቀ
"የዘመናት የህዝብ ጥያቄ የነበረውና ሁለት ክልሎችን የሚያስተሳስረው መንገድ ለአገልግሎት በቃ"
#ethiopia | የኦሮሚያ እና ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልሎችን የሚያገናኘው የ80 ኪሎ ሜትር የቱሉቦሎ-ኬላ አስፋልት መንገድ በከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ተመርቆ ዛሬ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል።
ፕሮጀክቱ
🛣 ርዝመትና ደረጃ:
80 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን እና በአስፓልት ኮንክሪት ደረጃ የተገነባ።
💰 ወጪ:
1.3 ቢሊዮን ብር (ሙሉ በሙሉ በፌዴራል መንግስት የተሸፈነ)።
🏗 ገንቢ እና አማካሪ:
በቻይናው "ሁናን ሁንዳ" የተገነባ ሲሆን፤ በሀገር በቀሉ "የተባበሩት የምኅንድስና አማካሪዎች" ቁጥጥር የተደረገበት።
የመንገዱ ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ:
ይህ መንገድ የአካባቢውን ማህበረሰብ የልማት ጥያቄ ከመመለሱም በላይ፤ የአዲስ አበባ-ቡታጅራ-ሆሳዕና እና የአዲስ አበባ-ወልቂጤ-ጅማ መስመሮችን በማገናኘት ለትራንስፖርት እና ለገበያ ትስስር ትልቅ ድርሻ ይኖረዋል።
#infrastructure #roadproject #ethiopia #tulubolo #kela #development #oromia #centralethiopia

Comments