4 months ago
"የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው የነበረውን ስብራት ሙሉ በሙሉ ጠግኗል" - አቶ አህመድ ሺዴ
******************
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በ2019 በጀት ዓመት የፌደራል መንግሥት በጀት ረቂቅ አዋጅ ላይ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር ሰፊ የአስረጅ መድረክ አካሂዷል።
በዚሁ መድረክ ላይ የቋሚ ኮሚቴው አባላት እና የሕግ ማዕከል ባለሙያዎች በረቂቅ በጀቱ ይዘት፣ አወቃቀርና አፈጻጸም ዙሪያ ሰፊ ሙያዊ ማብራሪያና ጥያቄዎችን አቅርበዋል።
ለቀረቡት ጥያቄዎችና አስተያየቶች በሙሉ የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሺዴ ዝርዝር ማብራሪያና ምላሽ ሰጥተዋል።
ሚኒስትሩ በማብራሪያቸው ወቅት መንግሥት ተግባራዊ ባደረገው ሀገራዊ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ላይ ትኩረት ያደረጉ ሲሆን፣ የተወሰደው የፖሊሲ እርምጃ በአሁኑ ወቅት እጅግ አወንታዊ ውጤት እያስመዘገበ መሆኑን ገልጸዋል።
አክለውም የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው ቀደም ሲል በሀገሪቱ የነበረውን የኢኮኖሚ ስብራት ሙሉ በሙሉ የጠገነ መሆኑን አስታውቀዋል።
የ2019 በጀት ዓመት ረቂቅ በጀት የሀገሪቱን ወቅታዊ የኢኮኖሚ ሁኔታ ያገናዘበና ቅድሚያ ለሚሰጣቸው ዋና ዋና የልማት ዘርፎች ልዩ ትኩረት የሰጠ መሆኑ በመድረኩ የተገለጸ ሲሆን፣ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት የተሰበሰቡ ጠቃሚ ግብዓቶችም በጀቱ በምክር ቤቱ ከመጽደቁ በፊት የላቀ ሚና እንደሚኖራቸው ተመላክቷል።
በወይንሸት ደጀኔ
#ethiopianbroadcastingcorporation #ethiopia #macroeconomy #parliamentethiopia #financialpolicy

6 months ago
የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ በከፍተኛ አደጋ ውስጥ መሆኑ ተገለጸ
#ethiopia | የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ በአሁኑ ወቅት በከፍተኛ የደህንነት ስጋት፣ በሰራተኞች ፍልሰትና በመሰረታዊ አገልግሎቶች እጥረት ሳቢያ የህልውና አደጋ ተጋርጦበታል።
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በፋብሪካዎቹ ላይ ባደረጉት የመስክ ምልከታ የተቋሙ ሁኔታ እጅግ አሳሳቢ መሆኑን ይፋ አድርገዋል።
የመኖሪያ ቤት እጥረት፣ አነስተኛ ደመወዝና ለከባድ ስራ የሚመጥን አበል አለመኖር ልምድ ያላቸው ባለሙያዎች ተቋሙን ጥለው እንዲወጡ አድርጓቸዋል።
በልማት ጣቢያዎቹ ውስጥ የንጹህ መጠጥ ውሃ፣ የባንክ፣ የቴሌኮምና የትራንስፖርት አገልግሎቶች አለመሟላት የሰራተኞችን ኑሮ እጅግ አዳጋች አድርጎታል።
ተቋሙ በዓመት 600,000 ቶን ስኳር የማምረት አቅም ቢኖረውም፣ በጸጥታ ችግርና በአመራር ድክመት ምክንያት የታለመውን ያህል ማምረት አልቻለም።
በቢሊዮን የሚቆጠር የሀገር ሀብት የወጣባቸው እነዚህ ግዙፍ ፋብሪካዎች፣ በአፋጣኝ መፍትሄ ካልተገኘላቸው ከጥቅም ውጭ ሊሆኑ እንደሚችሉ ተመልክቷል።
ዛሬ በአትሌቶቻችን ድል ኩራት ቢሰማንም፣ እንደ ስኳር ኢንዱስትሪ ያሉ ግዙፍ የሀገር ተቋማት እንዲህ ሲዳከሙ ማየት ያሳዝናል። ስኳር ለቤታችን ብቻ ሳይሆን ለሀገር ኢኮኖሚም ጣፋጭ ውጤት ማምጣት ነበረበት።
ሰራተኛው ሳይረጋጋና ደህንነቱ ሳይጠበቅ ምርት ማሰብ አይቻልም። መንግስት ለዚህ ዘርፍ የሚሰጠውን ትኩረት ካላሳደገ ኪሳራው የሁላችንም ነው።#ሪፖርተር
#getu #ethiopiansugarindustry #economiccrisis #parliamentethiopia #industrialchallenge #sugarfactory #ethiopianeconomy #reporternews #ስኳርኢንዱስትሪ #የኢትዮጵያኢኮኖሚ #ፓርላማ #አሳሳቢዜና #ጌጡተመስገን #getutemesgen

9 months ago
ኢትዮጵያ ከሶስቱ የብሪክስ አባላት ጋር ወንጀለኞችን አሳልፎ ለመስጠት ተስማማች! ⚖️🤝
#ethiopia | የኢትዮጵያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 9ኛ መደበኛ ስብሰባ፣ ሀገሪቱ ከሦስቱ የብሪክስ (BRICS) አባል ሀገራት ጋር ያደረገችውን ወሳኝ የሕግ ስምምነት በሙሉ ድምፅ አጽድቋል።
🔹 የስምምነቱ ዋና ዋና ነጥቦች፦
* ወንጀለኞችን አሳልፎ መስጠት፦ በኢትዮጵያ፣ በቻይና፣ በብራዚል ወይም በደቡብ አፍሪካ ወንጀል ፈጽመው ወደ አንዱ ሀገር የሸሹ ግለሰቦች ተላልፈው እንዲሰጡ ያስችላል።
* ፍርደኞችን ማስተላለፍ፦ በማንኛውም የትብብር ሀገር ውስጥ ታስረው የሚገኙ ዜጎች ቀሪ ቅጣታቸውን በሀገራቸው እንዲጨርሱ ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል።
* የሕግ ትብብር፦ በወንጀል ምርመራ እና በፍትህ ሂደት ላይ ሀገራቱ መረጃና ማስረጃ እንዲለዋወጡ የጋራ የሕግ ማዕቀፍ ተዘጋጅቷል።
🔹 ስምምነቱ ለምን አስፈለገ?
ኢትዮጵያ ከእነዚህ ሀገራት ጋር ያላት የንግድ፣ የኢንቨስትመንት እና የዲፕሎማሲ ግንኙነት በከፍተኛ ሁኔታ እያደገ መጥቷል። ይህንንም ተከትሎ የሚከሰቱ ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎችን ለመከላከል እና ፍትህን ለማረጋገጥ እንዲህ ዓይነቱ የሕግ ስምምነት አስፈላጊ መሆኑ በምክር ቤቱ ተመላክቷል።
ይህ ስምምነት ኢትዮጵያ በብሪክስ አባልነቷ የምታገኘውን የፖለቲካ እና የፍትህ ትብብር ይበልጥ የሚያጠናክር እርምጃ ተደርጎ ተወስዷል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#ethiopia #brics #justice #china #brazil #southafrica #legalagreement #crimeprevention #parliamentethiopia

Sponsored by
Surafel
Comments