ለአሜሪካ የታሪፍ እርምጃ አፀፋዊ ምላሽ እንወስዳለን - የብራዚሉ ፕሬዝዳንት
*********************
የብራዚል ፕሬዝዳንት ሉዊዝ ኢናሲዮ ሉላ ዳ ሲልቫ አሜሪካ በብራዚል ምርቶች ላይ ለምትጥለው ማንኛውም ታሪፍ ተመጣጣኝ እርምጃ ለመውሰድ ዝግጁ ነኝ ብለዋል።
የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከብራዚልጋር የገቡበትን እሰጣ ገባ በሚያባብስ ሁኔታ በብራዚል በተመረቱ ሸቀጦች ላይ የ50 በመቶ ቀረጥ ለመጣል ማቀዳቸውን ገልጸዋል።
ትራምፕ ለታሪፍ ጭማሪ እንደምክንያት ያነሱት ብራዚል በቀድሞው ፕሬዝዳንት ዣየር ቦልሶናሮ ላይ እያደረገችው ባለው ልክ ያልሆነ አያያዝ እንደሆነ ተናግረዋል።
የቀድሞ የብራዚል ፕሬዝዳንት ቦልሶናሮ በ2022 በብራዚል በተደረገው ምርጫ በአሁኑ ፕሬዝዳንት ከተሸነፉ በኋላ መፈንቅለ መንግስት ለማድረግ ሞክረዋል በሚል ክስ እንደቀረበባቸው ይታወቃል።
ትራምፕ ቦልሶናሮን በዓለም ዙሪያ ካሉ መሪዎች በጣም የተከበሩ መሪ ናቸው ሲሉ ገልጸው፤ ብራዚልም በቀድሞው ፕሬዝደንት ላይ የጀመረችውን ክስም በአስቸኳይ እንድታቆም ጠይቀዋል።
የብራዚሉ ፕሬዝዳንት በበኩላቸው፤ ሀገራቸው ከማንም የሚመጣን ጣልቃ ገብነት እንደማትቀበል እና ማንም ከሕግ በላይ እንዳልሆነ ተናግረዋል።
እንደ ቢቢሲ ዘገባ ፕሬዝዳንቱ በአንድ ወገን የሚደረግ የታሪፍ ጭማሪ እንደማይኖር እና ብራዚልም በአሜሪካ ምርቶች ላይ ተመጣጣኝ ታሪፍ እንደምትጥል አስጠንቅቀዋል።
አሜሪካ ከቻይና በመቀጠል የብራዚል ሁለተኛዋ ትልቅ የንግድ አጋር ስትሆን ከ10% ወደ 50% የሚጨመረው ታሪፍ የሃገሪቱን ኢኮኖሚ ሊጎዳ ይችላል ተብሏል።
በቢታንያ ሲሳይ
#ebc #america #brazil #tariffs

1 year ago