3 months ago
ኤምሬቶች ለዓለም እውነተኛ ሰብዓዊነትን ያስተማረችበት እርምጃ
እንግዶችን ከሆቴል አታስወጡ፤ መንግሥት ወጪያቸውን ይሸፍናል
እንግዶቹ ለእረፍት ነበር የመጡት... ነገር ግን የአየር ክልል በድንገት ተዘጋ። በረራዎች ተሰረዙ። ከ20,000 በላይ መንገደኞች በመላው ባሕረ ሰላጤው አገራት ሜዳ ላይ ቀሩ።
ነገር ግን በተለመደው ቀውስ ፋንታ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ አንድ ታሪካዊ እርምጃ ወሰደች።
🏨 "ማንንም አታስወጡ!"
የአቡ ዳቢ የባህልና ቱሪዝም መምሪያ በከተማዋ ለሚገኙ ሆቴሎች በሙሉ ጥብቅ መመሪያ አስተላለፈ፦ "እንግዶቹን አታስወጡ። ቆይታቸውን አራዝሙ። ሂሳቡን ለእኛ ላኩ!"
ዱባይም በጥቂት ሰዓታት ውስጥ ተመሳሳይ ትእዛዝ አስተላለፈች። እንደ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን መረጃ ከሆነ፣ መንግስት የተጎጂዎችን የመኝታ እና የምግብ ወጪ ሙሉ በሙሉ እየሸፈነ ይገኛል።
የግል ተቋማትም ዝም አላሉም መንግስት ብቻ ሳይሆን የግል ድርጅቶችም ተሳትፈዋል። የቤት አከራይ ድርጅቶች አፓርታማዎቻቸውን በነፃ ሲከፍቱ፣ ከ250 በላይ አባወራዎችም ቤታቸውን ለእንግዶች ክፍት አድርገዋል።
• ዋጋ መጨመር የለም!
• አውሮፕላን ማረፊያ ወለል ላይ መተኛት የለም!
• "ራሳችሁን ቻሉ" የሚል ግዴለሽነት የለም!
ይልቁንም፣ እያንዳንዱ ጎብኚ በሰላም ወደ ቤቱ እስኪመለስ ድረስ አገሪቱ ወጪውን በሙሉ በፀጋ ተቀብላ አስተናግዳለች።
Addis admas

7 months ago
ማሊ ሁለተኛውን የሊቲየም ማዕድን ማውጫ አስመረቀች
*የ250 ሚሊዮን ዶላር ኢንቨስትመንት ነው ተብሏል
ማሊ ሁለተኛውን የሊቲየም ማዕድን ማውጫ በዛሬው ዕለት ማስመረቋን የፕሬዚዳንቱ ቢሮ አስታውቋል፡፡
የማዕድን ማውጫው የሚገኘው በቡጉኒ ክልል ሲሆን፣ በየዓመቱ 400 ሺህ ቶን የሊቲየም ክምችት ያመርታል ተብሎ ይጠበቃል። ይህም ማሊን ከአፍሪካ ግዙፍ የዘርፉ አምራቾች አንዷ ያደርጋታል ተብሏል።
"ሊቲየም ማይንስ ኦፍ ቡጉኒ"፤ የተባለው የማዕድን ማውጫ 65 በመቶው የብሪታኒያው ኮዳል ማይኒንግ ሲሆን፤ 35 በመቶው ደግሞ የማሊ መንግሥት ነው።
ፕሮጀክቱ የ250 ሚሊዮን ዶላር ኢንቨስትመንት መሆኑን የዘገበው ስፑትኒክ፤ በሺዎች ለሚቆጠሩ የማሊ ዜጎች ቀጥተኛና ቀጥተኛ ያልሆኑ የሥራ ዕድሎችን መፍጠሩን ጠቁሟል፡፡
የአፍሪካ ግዙፉ የማዕድን ማውጫ እንደሆነ የሚታሰበውና በቡጉኒ ክልል የሚገኘው የማሊ የመጀመሪያው የሊቲየም ማዕድን ማውጫ ጉላሚና ተብሎ የሚጠራ ሲሆን፤ በ2017 ዓ.ም አጋማሽ ላይ ወደ ስራ ገብቷል።
ሊቲየም በአሁኑ ወቅት ለኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ባትሪዎች፣ ለቀጣይ ትውልድ ተሽከርካሪዎችና ለዘመናዊ የቴክኖሎጂ መሣሪያዎች ምርት ወሳኝ የሆነ ስትራቴጂያዊ ብረት ነው።
Via Addis admas

8 months ago
ጄነራል ታደሰ ወረደ ምን አሉ?
"ፌደራል መንግሥቱ በትግራይ ላይ ሌላ ዙር ጦርነት
ለመክፈት ዝግጅት እያደረገ ይገኛል"
የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት ሌተናንት ጀኔራል ታደሠ ወረደ፣ ፌደራል መንግሥቱ በትግራይ ላይ ሌላ ዙር ጦርነት ለመክፈት ዝግጅት እያደረገ ይገኛል በማለት ትላንት በኢትዮጵያ ከተመድ የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን ሃላፊ ጋር በተወያዩበት ወቅት መናገራቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን አስታውቋል።
ጀኔራል ታደሰ፣ ጊዜያዊ አስተዳደሩ የጦርነት ደመናን ለመግፈፍና ከፍተኛ ጥረት እያደረገ መሆኑን ለሃላፊው እንዳረጋገጡላቸው ቢሮው ገልጧል።
በትግራይ በኩል የሚጀመር ጦርነት አይኖርም ያሉት ጀኔራል ታደሰ፣ ጊዜያዊ አስተዳደሩ በትግራይ የተሟላና ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን ከፌደራል መንግሥቱ፣ ከዓለማቀፍ ድርጅቶችና ከውጭ ዲፕሎማቶች ጋር የቅርብ ግንኙነት በማድረግ ላይ መሆኑንም ገልጸዋል ተብሏል።
Via addis admas

11 months ago
የዳንጎቴ ሃብት በ24 ሰዓት የ414 ሚ. ዶላር ጭማሪ አስመዘገበ
• በዓለም የባለጸጎች ዝርዝር ከ74ኛ ወደ 73ኛ ደረጃ ተሸጋግሯል
#ethiopia | በአፍሪካ ቀዳሚ ቢሊየነር የሆነው ናይጄሪያዊው አሊኮ ዳንጎቴ፣ ባለፈው ሐሙስ ሃምሌ 10 ቀን 2017 ዓ.ም የተጣራ ሃብቱ በ24 ሰዓት ውስጥ በ414 ሚሊዮን ዶላር መጨመሩ ተዘግቧል፡፡
የዳንጎቴ ሃብት በአንድ ቀን ውስጥ ይህን ያህል ጭማሪ ያሳየው፣ የስኳርና ሲሚንቶ አክስዮን ዋጋው በመጨመሩና ኢንቨስተሮችን በመሳቡ ነው ተብሏል፡፡
የብሉምበርግ መረጃ እንደሚያሳየው፤ ግዙፉ ኩባንያው ዳንጎቴ ሲሚንቶ ትልቁን ትርፍ ያስመዘገበ ሲሆን፤ የአክስዮን ሽያጩ የ9.99 በመቶ ጭማሪ በማሳየት በአንድ ቀን ውስጥ የተጣራ ሀብቱን ከ27.8 ቢሊዮን ዶላር ወደ 28.2 ቢሊዮን ዶላር እንዲያድግ አድርጎታል፡፡
በዚህም ዳንጎቴ በዓለም የባለጸጎች ዝርዝር ውስጥ ቀድሞ ከነበረበት የ74ኛ ደረጃ ወደ 73ኛ ደረጃ እንደተሸጋገረ መረጃው ይጠቁማል፡፡
የሲሚንቶ ድርሻው ብቻ 410 ሚሊዮን ዶላር መጨመሩ ታውቋል፡፡ የስኳርና የምግብ አክስዮን ድርሻውም የጨመረ ሲሆን፤ የነዳጅ ማጣሪያና የማዳበሪያ ድርሻው ግን አልተለወጠም ተብሏል።
በኢትዮጵያ በ3 ቢሊዮን ዶላር የማዳበሪያ ፋብሪካ ለማቋቋም ከስምምነት ላይ የደረሰው ናይጄሪያዊው ቢሊየነር ዳንጎቴ፤ በናይጄሪያ አዲስ የባህር ወደብ ለማቋቋም በዝግጅት ላይ እንደሆነ የቢዝነስ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡
#addis_admas

ፕሮፌሰር አምሳሉ አክሊሉ ሲታወሱ
#ethiopia | ብዙዎቻችን በመዝገበ ቃላታቸው ተምረናል። አልያም በአስተማሪ እና ደራሲነታቸው እናውቃቸዋለን። ፕሮፌሰር አምሳሉ አክሊሉ።
የቋንቋው ሊቅ፣ የቃላት መዝገቡ
“ጥሩ የቋንቋ ሊቅ እንደምን ያለ ነው?” ተብሎ ከተጠየቀ መልሱ “እንደ ዶክተር አምሳሉ አክሊሉ ያሉ” ልንል ይቻለናል፡፡
መቸም የቋንቋን ነገር እጥግ ድረስ የተከታተሉ ሰዎች አሉ ከተባለ ዶክተር አምሳሉ አክሊሉ አንዱ መኾን አለባቸው፡፡ በተለይ በሥነ ልሳን ትምሕርት “ሴማዊ” የሚል ስም በተሰጣቸው ቋንቋዎች (አማርኛ ግእዝ፣ ዓረብኛና ዕብራይስጥ) ላይ የተራቀቁ ነበሩ፡፡
የዶክተር አምሳሉ አክሊሉ የቋንቋ ችሎታ በነዚህ አይወሰንም፡፡ ከአውሮፓውያኑ እንግሊዝኛን፣ ጀርመንንና ጣሊያንኛን ጥርት አድርገው የሚያውቁ ነበሩ፡፡ ከነዚህ ውስጥ ባንዱ ቋንቋዊ ጉዳዮችን መጻፍና ማስረዳት የሚችሉ ልዩ ሰውም ነበሩ፡፡
“ቋንቋ እውቀት አይደለም፣” ይባላል፤ እውቀትን ማግኚያ እንጂ፡፡ ሁለቱንም የሚኾነው ለባለሞያው ነው። እንደዚያ ከኾነ፣ ዶክተር አምሳሉ አክሊሉ ከምር የቋንቋ ሊቅ ነበሩ፡፡ ይህንንም ሊገልጡ በሚችሉ መሠረታዊ ሥራዎቻቸው አስመስክረዋል።
ዶክተር አምሳሉ አክሊሉ በደሴ ከተማ አቅራቢያ ነሐሴ 27 ቀን 1922 ተወለዱ፡፡ የንግሥተ ነገሥታት ዘውዲቱ ዘመን ማብቂያ ላይ የተወለዱት አምሳሉ፤ እዚያው ደሴ አካባቢ የትውፊታዊውን
ት/ቤትና የ፩ኛ ደረጃ ትምሕርታቸውን ፈጽመው ወደ አዲስ አበባ በመምጣት፣ በቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ት/ቤት የ፪ኛ ደረጃ ትምሕርታቸው ቀጥለዋል። ይኽንንም በከፍተኛ ውጤት በማጠናቀቃቸው የነፃ ከፍተኛ ትምሕርት ዕድል በማግኘት ወደ ግብፅ ሔዱ፡፡
በግብፅ ካይሮ ውስጥ በሚገኝ መንፈሳዊ ኮሌጅ የስነ መለኮት ትምሕርታቸውን እየተከታተሉ፣ እዚያው ካይሮ ውስጥ ባለው የአሜሪካ ዩኒቨርሲቲ ደግሞ የሶሺዮሎጂ ትምሕርታቸውን ተምረዋል፡፡ በሁለቱም ትምሕርታቸው በ1949 ዓ.ም በአስደናቂ ውጤት ሁለት ዲግሪ አግኝተዋል።
ከዚያም ወደ ጀርመን በመሔድ በቲዩቢንገን ዩኒቨርሲቲ በ1954 ዓ.ም የፒኤች.ዲ ዲግሪአቸውን አግኝተዋል፡፡
ዶክተር አምሳሉ አክሊሉ ከቲዩቢንገን የፒኤችዲ ዲግሪያቸውን እንዳገኙ ወደ ሀገራቸው በመመለስ፣ በብሔራዊ ቤተመዛግብት ወመዘክር የሳይንስ ቡድን ዳይሬክተር በመኾን ለሁለት ዓመት አገልግለዋል፡፡
ከ1956 ዓ.ም. ጀምረው በአ.አ.ዩ. የቋንቋ ትምሕርት ክፍል መምሕር በመኾን የግእዝ፣ የአማርኛ፣ የኢትዮጵያ ሥነ ጽሑፍና መዝገበ ቃላት ማጠናቀርን ለሠላሳ ሁለት ዓመት ሲያስተምሩ ቆይተዋል፡፡ በ1988 ዓ.ም. ጡረታ እስኪወጡ ድረስ ባገለገሉበት የአ.አ. ዩኒቨርሲቲ በርካታ የጥናትና ምርምር ሥራዎችንም አከናውነዋል፡፡
በጀርመን ሀምቡርግ ዩኒቨርሲቲ የአፍሪካ እና የኢትዮጵያ ጥናት ክፍል የአማርኛ እና ግእዝ መምሕር በመኾን እስከ 1996 ዓ.ም ድረስ አገልግለዋል፡፡
ከ1996 ዓ.ም በኋላ ቀድሞ ሲያስተምሩ በቆዩበት አ.አ.ዩ፣ በነገረ ጽሕፈት ትምሕርት (ፊሎሎጂ) የድኅረ ምረቃ ተማሪዎችን በማስተማርና በማማከር አገልግሎታቸው የ2ኛ እና የ3ኛ ዲግሪ ተማሪዎችን አፍርተዋል፡፡
ከነዚህም ሌላ ከስምንት ያላነሱ ልዩና መሠረታዊያን የኾኑ መጻሕፍትን በማቅረብ፣ የቋንቋ እውቀታቸውን ከማስመስከራቸውም በላይ፣ እውቀታቸውን ለትውልድ በጽሑፍ ትተው ያለፉ ምሁር ናቸው፡፡
የአምሳሉ አክሊሉን እንግሊዝኛ - አማርኛ መዝገበ ቃላት የማያውቃት ተማሪ አለ ለማለት ይከብዳል፡፡ መጀመሪያ በኢትዮጵያ ውስጥ መምሕር ከነበሩት ከጂ.ፒ ሞስባክ ጋር ያዘጋጇት እንግሊዝኛ - አማርኛ መዝገበ ቃላት፤ በየትኛውም የአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ተማሪ ንትብ ብላ እስክታልቅ ድረስ መገልገያ የኾነች ናት። ከአቀራረቡ ዓይነት ጀምሮ፣ ከቃላት ትርጉምም በላይ የኾነው ሌላው አስደናቂ ሥራቸው ደግሞ አማርኛ-እንግሊዝኛ መዝገበ ቃላት ነው፡፡
እጅጉን የከበደ እና ጊዜ ፈጅ የኾነውን የመዝገበ ቃላት ማጠናቀር ሥራ ያስተምሩ የነበሩት ዶክተር አምሳሉ አክሊሉ፣ ጀርመን-አማርኛ መዝገበ ቃላትንም አሳትመው አቅርበዋል፡፡
ከነዚህም ሌላ ከአቶ ሙኒር አብራር ጋር በመኾን ዓረብኛ-አማርኛ መዝገበ ቃላትንም ሠርተዋል፡፡
ዶክተር አምሳሉ፤ በአካዳሚክ ተቋማት እጅግ ያስከበሯቸውንና የተለያዩ ማዕረጐችን ያሰጧቸውን ብዙ የምርምርና የጥናት ሥራዎችን ያቀረቡም ነበሩ፡፡ ዓለም ዓቀፋዊ ዕውቅና ባላቸው በተለያዩ መጽሔቶች፣ መጻሕፍት፣ በመዛግብተ ስብእ፣ በዓውደ ጥበባት እና በመድብለ ጉባዔዎች የምርምር ሥራዎቻቸው ለህትመት በቅተዋል።
ዶክተር አምሳሉ አክሊሉ በእርግጥም “የቋንቋ ሊቅ እንደምን ያለ ነው” ተብሎ ቢጠየቅ “እንደ ዶክተር አምሳሉ አክሊሉ” ብለው ቢመልሱ፣ የማይበዛባቸው ታላቅ መምሕር፣ ታላቅ አባት ነበሩ።
እኝህ አባት መምሕር በ84 አመታቸው ታኅሣሥ 11 ቀን 2006 ዓ.ም ዐርፈው በየካ ደብረ ሣህል ቅዱስ ሚካኤል ወዳጅ ዘመዶቻቸው፣ የሙያ ባልደረቦቻቸውና ተማሪዎቻቸው እንዲሁም በሥራዎቻቸው የሚያውቋቸውና አድናቂዎቻቸው በተገኙበት ቀብራቸው ተፈጽሟል፡፡ #addis_admas

"የኢትዮጵያ የወደፊት ተስፋዋ በወጣቶች እጅ ላይ ነው"
#ethiopia | በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ብናልፍ አንዱዓለም፣ ታዳጊውን ትውልደ ኢትዮጵያዊ ሳይንቲስት በኤምባሲው ተቀብለው ማነጋገራቸው ተገለጸ፡፡
ሄመን በቀለ በአሜሪካ የቆዳ ካንሰርን የሚከላከል ሳሙና በመፍጠር እ.ኤ.አ 2023 "የአሜሪካ ከፍተኛ ወጣት ሳይንቲስት" የሚል ስያሜ ያገኘ ሲሆን፤ በ2024 ደግሞ ‘’Time Kid of the Year’’ ሆኖ ተመርጧል፡፡
ታዳጊው ኢትዮጵያዊ የፈጠረው ሳሙና በፀሐይ ጨረር ምክኒያት ሊከሰት የሚችል የቆዳ ካንሰርን ለመከላከል የሚያስችልና ለበርካቶች ተስፋን የሚሰጥ እድል ይዞ የመጣ እንደሆነ ተነግሮለታል፡፡
አምባሳደር ብናልፍ ወጣት ሄመንን ባነጋገሩበት ወቅት፣ ኢትዮጵያ የወደፊት ተስፋዋ በወጣቶች እጅ ላይ መሆኑን በጽኑ እንደሚያምኑና የሄመንም እንቅስቃሴ ይህንኑ እምነታቸውን ያረጋገጠላቸው መሆኑን አንስተዋል፡፡
በሰራው ስራ እውቅናና ሽልማት ማግኘቱ ብቻ ሳይሆን ለአገሩ ያለው ፍቅርና ተጋላጭ ለሆኑ ማህበረሰቦች የጤና አጠባበቅን ተደራሽ ለማድረግ ያለው ቁርጠኝነቱ እንዳስደነቃቸው አምባሳደሩ ገልጸዋል፡፡
በመጨረሻም ለነበራቸው ውይይት አመስግነው፤ ወጣቱ ለሚያደርገው ጥረት ኤምባሲው ሙሉ ድጋፉን እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል፡፡ #addis_admas

ከመነኮሳት ጋር ወሲብ ፈጽማ 11.9ሚ. ዶላር
ተቀብላለች የተባለችው ግለሰብ ተያዘች
#ethiopia | በታይላንድ ከቡድሂስት መነኮሳት ጋር ወሲብ ከፈጸመች በኋላ ፎቶዎችንና ቪዲዮዎችን ገንዘብ ለማግኘት በማስፈራሪያነት ተጠቅማ ከፍተኛ ሃብት አከማችታለች የተባለችው ግለሰብ በቁጥጥር ስር መዋሏን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
ፖሊስ "ሚስ ጎልፍ" በሚል ቅጽል ስም የጠራት ይህች ግለሰብ፣ ቢያንሰ ከዘጠኝ መነኮሳት ጋር ወሲብ መፈጸሟን ማክሰኞ ዕለት ፖሊስ በጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቋል።
ግለሰቧ በባለፉት ሦስት ዓመታት መነኮሳቱን አስፈራርታ 11.9 ሚሊዮን ዶላር እንዳገኘች ፖሊስ ያምናል።
ቤቷን የፈተሹ መርማሪዎች መነኮሳቱን ለማስፈራራት የተጠቀመችባቸውን ከ80 ሺህ በላይ ፎቶዎችንና ቪዲዮዎችን ማግኘታቸውን የፖሊስ ቃል አቀባይ ተናግረዋል።
በታይላንድ በቅድስና እና ክብር ከፍተኛ ስፍራ የሚሰጠው የቡድሂስት ተቋም በቅርብ ዓመታት ውስጥ በተለያዩ ቅሌቶች መነከሩ እየተነገረ ሲሆን፤ ከነዚህም ውስጥ አደገኛ ዕጽ ዝውውር እንዲሁም ወሲባዊ ጥቃቶች ናቸው። በቅርቡ የዚህች ግለሰብ ተግባር የእምነቱን ተቋም ያናጋ ሆኗል፤ ብሏል የቢቢሲ ዘገባ፡፡ #addis_admas

የቢዮንሴ ያልተለቀቀ ሙዚቃ መሰረቁ ተገለጸ
#ethiopia | የታዋቂዋ አሜሪካዊቷ ሙዚቀኛ ቢዮንሴ ያልተለቀቁ ዘፈኖችን ጨምሮ ላፕቶፕና ሌሎች በርካታ ዕቃዎች በአትላንታ ከመኪና ውስጥ መሰረቃቸው ተገለጸ።
ካውቦይ ካርተር ከተሰኘ አልበሟ ጋር ተያይዞ የሙዚቃ ጉዞ ላይ ያለችው ሙዚቀኛዋ፤ በአትላንታ የተገኘችው ለኮንሰርት ነው።
ከሙዚቃ ዝግጅቱ ሁለት ቀናት ቀደም ብሎም ዘፈኖቿን የያዘው ሃርድ ዲስክ ከኪራይ መኪና ተሰርቋል ተብሏል።
ሃርድ ዲስኩ የቢዮንሴ ያልተለቀቁ ዘፈኖችን፣ የሙዚቃ ጉዞ የጊዜ ሰሌዳዎችን፣ የኮንሰርት ዕቅዶችን ይዞ እንደነበር የሙዚቀኛዋ አንደኛው ዳንሰኛና የዳንስ ዝግጅት አቀናባሪ መናገራቸውን ከፖሊስ ሪፖርት የተገኘውን መረጃ ጠቅሶ ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
ቢዮንሴ በአትላንታ ለመጀመሪያ ጊዜ ከምታደርገው የሙዚቃ ዝግጅት ሁለት ቀናት ቀደም ብሎ፣ ሐምሌ 1 ቀን 2017 ዓ.ም መሰረቁ ተገልጿል። #addis_admas

Sponsored by
Surafel
11 months ago
ሩሲያ በማዕከላዊ አፍሪካ የአልማዝ ማዕድን ለማውጣት ተፈቀደላት
#ethiopia | ማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ፣ የሩሲያ ኩባንያዎች የአልማዝ ማዕድን እንዲያወጡ ፈቃድ መስጠቷን ስፑትኒክ ዘግቧል፡፡
ባለፈው ዓመት የአልማዝ የወጪ ንግድ እገዳ ሙሉ በሙሉ መነሳቱ ለማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው፤ የሀገሪቱ የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር ቴሪ ፓትሪክ አኮሎዛ ለሩሲያ ሚዲያ ተናግረዋል፡፡
"ምክንያቱም ያለ ማዕቀብ ሀገሪቱ የማልማትና የማዕድን ምርቶቿን በመሸጥ ጥሩ ገቢ የማግኘት እድል አላት” በማለት አዲሱ ነጻነት የሚሰጠውን ኢኮኖሚያዊ አቅም አጉልተው ማሳየታቸውን ዘገባው ጠቁሟል፡፡
እ.ኤ.አ ሕዳር 21 ቀን 2024 ዓ.ም ለአልማዝ ንግድ ዓለም አቀፍ እውቅና የሚሰጠውና ተቆጣጣሪ አካል የሆነው ‘የኪምበርሊ ሂደት’ ማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ አልማዝ ወደ ውጭ እንዳትልክ ጥሎ የነበረውን እገዳ አንስቷል፡፡ እቀባው በግጭት ስጋት ምክንያት መጀመሪያ የተጣለባት በፈረንጆቹ 2013 ነበር፡፡
በ2016 እግዱ በከፊል መነሳቱን ተከትሎ ከግጭት ነጻ ከተባሉ አምስት ቀጠናዎች አልማዝ ወደ ውጭ እንድትልክ አስችሏታል፡፡ የማዕቀቡ ሙሉ በሙሉ መነሳት ደግሞ ለሰፊ የማዕድን ሥራዎችና ለዓለም አቀፍ አጋርነት መንገድ ከፍቷል ተብሏል።
የሩሲያ የማዕድን ኩባንያዎች በተመሳሳይ በሳኡዲ አረቢያ ማዕድን በማውጣት ሥራ እንዲሰማሩ ፈቃድ ማግኘታቸው ሰሞኑን ተዘግቧል፡፡ #addis_admas

• የፈረንሳዩ አምባሳደር ስለ ኢትዮጵያ የባህር በር ፍላጎት ---
#ethiopia | “...ኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤት ለመሆን የምታደርገው ጥረት ህጋዊና ቅቡልነት ያለው ነው። ከፍተኛ ቁጥር ያለው ህዝብና በፍጥነት እያደገ ያለ ኢኮኖሚ ባለቤት የሆነችው ኢትዮጵያ፤ ደህንነቱ የተጠበቀ የባህር በር እንደሚያስፈልጋት ፈረንሳይ ጽኑ እምነት ያላት ሲሆን፤ ለተግባራዊነቱም ከጎኗ ትቆማለች...ዓለማቀፋዊ ህግን በተከተለ መልክና ጎረቤቶችን ባማከለ ሁኔታ የባህር በር ማግኘት ይኖርባታል--”
(አሌክሲስ ላሜክ፤ በኢትዮጵያ የፈረንሳይ አምባሳደር፤ ለኢትዮጵያን ሄራልድ) #addis_admas

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከዓለም በስንተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል?
#ethiopia | ሃርቫርድ ዩኒቨርሲቲ የአንደኝነቱን ደረጃ እንዳስጠበቀ ቀጥሏል
ኬፕታውን ዩኒቨርሲቲ ከአፍሪካ የአንደኝነት ደረጃ ይዟል
6 የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች በ"ግሎባል 2000" ዝርዝር ተካተዋል
የዓለም ዩኒቨርሲቲዎች ደረጃ አሰጣጥ ማዕከል በዘንድሮ እትሙ፣ ለ21,462 የትምህርት ተቋማት ደረጃ የሰጠ ሲሆን፤ ከእነዚህም መካከል ከፍተኛ ደረጃ ላይ የሚገኙትን "ግሎባል 2000" ዝርዝር ውስጥ አካቷል። በዚህ ዝርዝር ከተካተቱት ውስጥ ስድስት የኢትየጵያ ዩኒቨርሲቲዎች ይገኙበታል፡፡
ማዕከሉ ዩኒቨርሲቲዎችን በአለም አቀፍ ደረጃ ለመመዘን 74 ሚሊዮን የዳታ ነጥቦችን በአራት ዋና ዋና መለኪያዎች ላይ ተመስርቶ ገምግሟል፤ እነርሱም፡-
የትምህርት ጥራት (25%)
ቅጥር (ተቀጣሪነት) (25%)
የፋኩልቲዎች ጥራት (10%)
የምርምር አፈጻጸም (40%) ናቸው።
የአሜሪካ ዝነኛ የትምህርት ተቋም የሆነው ሃርቫርድ ዩኒቨርሲቲ፣ ለአስራ አራተኛ ተከታታይ ዓመት፣ የአንደኛ ደረጃነቱን አስጠብቆ የቀጠለ ሲሆን፤ የማሳቹሴትስ የቴክኖሎጂ ተቋምና የስታንፎርድ ዩኒቨርሲቲ ሁለተኛና ሦስተኛ ደረጃን ይዘዋል። የካምብሪጅ ዩኒቨርሲቲና የኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ ተከታዩ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል፡፡
ፕሪንስተን ዩኒቨርሲቲ፣ ፔንስልቬኒያ ዩኒቨርሲቲ፣ ኮሎምቢያ ዩኒቨርሲቲ፣ ዬል ዩኒቨርሲቲና ቺካጎ ዩኒቨርሲቲ ደግሞ ከስድስተኛ አስከ አስረኛ ያለውን ደረጃ የያዙ ሲሆን፤ ሁሉም የአሜሪካ የግል የትምህርት ተቋማት ናቸው።
በሌላ በኩል፤ ቻይና 346 ዩኒቨርሲቲዎቿ በ"ግሎባል 2000" ዝርዝር ውስጥ የተካተተላት ሲሆን፤ ብዛት ያላቸው ተቋማት በማካታት በአንደኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች፡፡
ከአፍሪካ የደቡብ አፍሪካው ኬፕታውን ዩኒቨርሲቲ ከአለም 271ኛ ደረጃ፣ ከአፍሪካ ደግሞ የአንደኛ ደረጃን ማግኘት ችሏል፡፡
የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች ደረጃ
አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ከኢትዮጵያ አንደኛ፣ ከአለም 808ኛ
ጎንደር ዩኒቨርስቲ ከኢትዮጵያ ሁለተኛ፣ ከአለም 1607ኛ
ጅማ ዩኒቨርስቲ ከኢትዮጵያ ሦስተኛ፣ ከአለም 1701ኛ
መቐሌዩኒቨርሲቲ ከኢትዮጵያ አራተኛ፣ ከአለም 1757ኛ
ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ከኢትዮጵያ አምስተኛ፣ ከአለም 1803ኛ
ሀረማያ ዩኒቨርሲቲ ከኢትዮጵያ ስድስተኛ፣ ከአለም 1903ኛ
የትምህርት መረጃ #addis_admas

ኢትዮጵያ የራሷን ዋትስአፕ፣ ጂ-ሜይልና ቴሌግራም እያበለፀገች ነው ተባለ
#ethiopia | በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢንሳ) አማካኝነት የተገነቡት የዲጂታል ቴክኖሎጂ መድረኮች የሳይበር ደህንነትን ለማሻሻልና ከኢትዮጵያ የቁጥጥር ማዕቀፍ ውጪ በሆኑ የውጭ ኩባንያዎች ላይ ያለውን ጥገኝነት ለመቀነስ የታለሙ እንደሆኑ ስፑትኒክ ዘግቧል፡፡
ለጂሜይል አማራጭ ሆኖ የቀረበው “እርጋሜል” ከወዲሁ በመንግሥት ተቋማት ሥራ ላይ መዋል እንደጀመረ ተነግሯል፡፡ "ሰርኩትኒ" የዋትስአፕ እና ቴሌግራም ምትክ እንዲሆን የሚጠበቅ ሲሆን፤ ገና በትግበራ ላይ እንደሚገኝ ታውቋል፡፡
ለቨርቹዋል ግንኙነቶች ታስቦ በኢንሳ የበለፀገው “ደቦ” ደግሞ በሙከራ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ዘገባው አመልክቷል፡፡ #addis_admas

ከአሁን በኋላ አፍሪካን እንደ ጥሩ የንግድ አጋር ነው የምናያት - አሜሪካ
#ethiopia | "ከአሁን በኋላ አፍሪካን እርዳታ እንደምትፈልግ አህጉር ሳይሆን፤ እንደ ጥሩ የንግድ አጋር አድርገን ነው የምናያት፡፡ ለዓመታት ትኩረት ሲሰጠው ያላየነው "ንግድ እንጂ ዕርዳታ አይደለም" የሚለው መፈክር፣ አሁን በትክክል የአፍሪካ ፖሊሲያችን ነው። ምክንያቱም ዕርዳታ በለጋሽና ተቀባይ መካከል የሚደረግ ግንኙነት ሲሆን፤ ንግድ ግን በአቻዎች መካከል የሚደረግ ግንኙነት ነው።" - ትሮይ ፌትሬል፤ የአፍሪካ ጉዳዮች ከፍተኛ ቢሮ ኃላፊ

ለህገ-ወጥ እርድ የተዘጋጁ 62 የቁም እንስሳት ተያዙ
📌የቁም እንስሳቱ ለመንግስት ገቢ ተደርገዋል
#ethiopia | ለህገ-ወጥ እርድ የተዘጋጁ 62 የቁም እንስሳት መያዛቸዉን የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን አስታወቀ፡፡
በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 ልዩ ቦታው ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን አካባቢ ጥናት ላይ ተመስርቶ በተካሄደ ኦፕሬሽን 12 የታረዱ በጎች፤ 1 የታረደ በሬና 62 ያልታረዱ የቁም እንስሳት መያዛቸዉን ባለስልጣኑ አስታዉቋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ለአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዲጂታል ሚዲያ እንደገለጹት፤ የድርጊቱ ፈፃሚዎችን በህግ ተጠያቂ በማድረግ፣ በቦታው የተገኙት የቁም እንስሳቶች ለመንግስት ገቢ መደረጋቸውን ገልጸዋል፡፡
ህገ-ወጥ እርድ ሲያከናውን የተያዘው ግለሰብ 15 ሺህ ብር በመቅጣት በህግ እንዲጠየቅ በቁጥጥር ስር ማዋሉንም ጨምረዉ ተናግረዋል፡፡
በህገ ወጥ መንገድ የተያዘው ስጋ እንዲወገድ መደረጉንም ገልጸዋል፡፡ #addis_admas

"ለኢትዮጵያ የሚሰጠው እርዳታ አይቋረጥም"
#ethiopia | አሜሪካ ለኢትዮጵያና መሰል ሀገራት የምትሰጠውን እርዳታ የምታስተዳድርበት መንገድ ላይ ወሳኝ ለውጥ አድርጋለች። ከሰሞኑ ተግባራዊ መሆን የጀመረው ይህ ለውጥ፣ የአሜሪካ መንግስት የልማት፣ የጤና እና የምግብ ዋስትና ድጋፎችን የሚያቀርብበትን አካሄድ በአዲስ መልክ ያዋቅራል።
ከዚህ ቀደም በአሜሪካ ዓለም አቀፍ የልማት ድርጅት (USAID) ይከናወኑ የነበሩ ቁልፍ ተግባራት፣ አሁን በቀጥታ በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ስር እንዲሆኑ ተደርጓል።
ይህም በሁለት የተለያዩ ቢሮዎች የሚሰሩ ተቀራራቢ ስራዎችን ወደ አንድ ማዕከል በማምጣት የተሻለ ቅንጅት ለመፍጠር ያለመ ነው ተብሏል።
ይህ ለውጥ ለኢትዮጵያ የሚሰጠው እርዳታ እንዲቋረጥ ያደርጋል? የሚለውን ጥያቄ "አንዳፍታ" በአዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ የሰጠውን መልስ በመጥቀስ እንደማይቋረጥ በዘገባው አመልክቷል፡፡
ኤምባሲው እንዳረጋገጠው፣ ከአሁኑ የኢትዮጵያ መንግስት ጋር የተደረሱ የእርዳታ ስምምነቶች እንደተጠበቁ ሆነው ይቀጥላሉ። በተለይም ህይወት አድን የሆኑና ወሳኝ ድጋፎች ማለትም፦ የሰብዓዊ እርዳታ፣ የዓለም አቀፍ የጤና ድጋፍ፣ የምግብ ዋስትና ፕሮግራሞች ሳይስተጓጎሉ በአዲሱ መዋቅር ስር ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተገልጿል።
በፕሬዚዳንት ትራምፕና በውጭ ጉዳይ ጸሃፊ ሩቢዮ አመራር የተጀመረው ይህ እቅድ፣ በመጨረሻም በዓለም ዙሪያ የሚሰጠው ድጋፍ ግቡን እንዲመታና ህይወት እንዲያድን ለማድረግ ያለመ ስልታዊ እርምጃ ነው ተብሏል፡፡

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ቻይናን ሊጎበኙ ነው
#ethiopia | የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ፣ ቻይናን ሊጎበኙ አሊያም የቻይናው ፕሬዚዳንት ዚ ቺንፒንግ አሜሪካን ሊጎበኙ እንደሚችሉ አርብ ዕለት መናገራቸውን ማክስኒውስ ዘገበ፡፡
"እኔ ቻይናን ልጎበኝ ወይም ዚ እኛን ሊጎበኝ ይችላል" ብለዋል፤ ትራምፕ፡፡
ባለፈው ወር ሁለቱም መሪዎች አንዳቸው የሌላኛቸውን አገር እንዲጎበኙ መጋበዛቸው ተጠቁሟል፡፡ #addis_admas

ፑቲን ወደ ኢትዮጵያ !
ፑቲን በታላቁ ህዳሴ ግድብ የምረቃ መርሃ ግብር ላይ ሊጋበዙ ይችላሉ ተባለ።
በኢትዮጵያ ታላቁ የህዳሴ ግድብ ምርቃት ላይ የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን እንዲገኙ የኢትዮጵያ መንግሥት ግብዣ ሊልክ እንደሚችል ስፑትኒክ ዘግቧል፡፡
ባለፈው ሳምንት በፓርላማ ተገኝተው ለህዝብ ተወካይ ም/ቤት አባላት ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ የሰጡት ጠ/ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ፣ ታላቁ የህዳሴ ግድብ ክረምቱ እንደወጣ በመስከረም ላይ እንደሚመረቅና በዚህ ታላቅ በዓል ላይ የግብጽና ሱዳን ባለሥልጣት እንዲገኙ በይፋ መጋበዛቸው ይታወሳል፡፡
በሌላ በኩል፣ የግብጽ ውሃና መስኖ ሚኒስትር፤ ‹‹የግብፅን ውሀ መብት በመቀነስ የኢትዮጵያን ልማት ለማምጣት የሚደረግ ማናቸውንም ጥረት አንቀበልም›› ሲሉ መናገራቸው ተዘግቧል፡፡
የግብፅ ውሀና መስኖ ሚኒስትር ዶ/ር ሀኒ ስዊላም ይህን ያሉት፣ ዛሬ ከአገራቸው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር በመሆን በውጭ አገራት ለተሾሙ አዳዲስ አምባሳደሮች የስራ መመሪያ በሰጡበት ወቅት ነው ተብሏል፡፡ #addis_admas

የኢራን ጦር ኢትዮጵያውያንን ለምን አመሰገነ?
#ethiopia | የኢራን ጦር ሠራዊት ባለፉት 48 ሰዓታት ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የማህበራዊ ትስስር ገጹ አዳዲስ ተከታዮችን ኢትዮጵያን ጨምሮ ከበርካታ አገራት ማግኘቱን በመግለጽ ምስጋናውን አቅርቧል፡፡
ጦር ሰራዊቱ በፌስቡክ ገጹ ባሰፈረው መልዕክት፤ ከኢትዮጵያ፣ ጋና፣ አፍጋኒስታን፣ ሶማሊያ፣ ኬኒያና ደቡብ አፍሪካ በርካታ አዳዲስ ተከታዮችን አግኝቻለሁ ብሏል፡፡
የአፍሪካ ህዝቦች ለኢራን ያለማቋረጥ አጋርነታቸውን አሳይተዋል ያለው የኢራን ጦር፤ የአፍጋኒስታን ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ሁልጊዜም በታማኝነትና በፍቅር ከጎናችን እንደቆሙ ናቸው ብሏል፡፡
ለዚህም ምስጋናውን አቅርቧል - የኢራን ጦር ሠራዊት፡፡ #addis_admas