ሩሲያ በማዕከላዊ አፍሪካ የአልማዝ ማዕድን ለማውጣት ተፈቀደላት
#ethiopia | ማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ፣ የሩሲያ ኩባንያዎች የአልማዝ ማዕድን እንዲያወጡ ፈቃድ መስጠቷን ስፑትኒክ ዘግቧል፡፡
ባለፈው ዓመት የአልማዝ የወጪ ንግድ እገዳ ሙሉ በሙሉ መነሳቱ ለማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው፤ የሀገሪቱ የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር ቴሪ ፓትሪክ አኮሎዛ ለሩሲያ ሚዲያ ተናግረዋል፡፡
"ምክንያቱም ያለ ማዕቀብ ሀገሪቱ የማልማትና የማዕድን ምርቶቿን በመሸጥ ጥሩ ገቢ የማግኘት እድል አላት” በማለት አዲሱ ነጻነት የሚሰጠውን ኢኮኖሚያዊ አቅም አጉልተው ማሳየታቸውን ዘገባው ጠቁሟል፡፡
እ.ኤ.አ ሕዳር 21 ቀን 2024 ዓ.ም ለአልማዝ ንግድ ዓለም አቀፍ እውቅና የሚሰጠውና ተቆጣጣሪ አካል የሆነው ‘የኪምበርሊ ሂደት’ ማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ አልማዝ ወደ ውጭ እንዳትልክ ጥሎ የነበረውን እገዳ አንስቷል፡፡ እቀባው በግጭት ስጋት ምክንያት መጀመሪያ የተጣለባት በፈረንጆቹ 2013 ነበር፡፡
በ2016 እግዱ በከፊል መነሳቱን ተከትሎ ከግጭት ነጻ ከተባሉ አምስት ቀጠናዎች አልማዝ ወደ ውጭ እንድትልክ አስችሏታል፡፡ የማዕቀቡ ሙሉ በሙሉ መነሳት ደግሞ ለሰፊ የማዕድን ሥራዎችና ለዓለም አቀፍ አጋርነት መንገድ ከፍቷል ተብሏል።
የሩሲያ የማዕድን ኩባንያዎች በተመሳሳይ በሳኡዲ አረቢያ ማዕድን በማውጣት ሥራ እንዲሰማሩ ፈቃድ ማግኘታቸው ሰሞኑን ተዘግቧል፡፡ #addis_admas

11 months ago