Logo
Getu Temesgen
የኢራን ጦር ኢትዮጵያውያንን ለምን አመሰገነ?
#ethiopia | የኢራን ጦር ሠራዊት ባለፉት 48 ሰዓታት ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የማህበራዊ ትስስር ገጹ አዳዲስ ተከታዮችን ኢትዮጵያን ጨምሮ ከበርካታ አገራት ማግኘቱን በመግለጽ ምስጋናውን አቅርቧል፡፡

ጦር ሰራዊቱ በፌስቡክ ገጹ ባሰፈረው መልዕክት፤ ከኢትዮጵያ፣ ጋና፣ አፍጋኒስታን፣ ሶማሊያ፣ ኬኒያና ደቡብ አፍሪካ በርካታ አዳዲስ ተከታዮችን አግኝቻለሁ ብሏል፡፡

የአፍሪካ ህዝቦች ለኢራን ያለማቋረጥ አጋርነታቸውን አሳይተዋል ያለው የኢራን ጦር፤ የአፍጋኒስታን ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ሁልጊዜም በታማኝነትና በፍቅር ከጎናችን እንደቆሙ ናቸው ብሏል፡፡

ለዚህም ምስጋናውን አቅርቧል - የኢራን ጦር ሠራዊት፡፡ #addis_admas

1 year ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.