Logo
Getu Temesgen
"ለኢትዮጵያ የሚሰጠው እርዳታ አይቋረጥም"
#ethiopia | አሜሪካ ለኢትዮጵያና መሰል ሀገራት የምትሰጠውን እርዳታ የምታስተዳድርበት መንገድ ላይ ወሳኝ ለውጥ አድርጋለች። ከሰሞኑ ተግባራዊ መሆን የጀመረው ይህ ለውጥ፣ የአሜሪካ መንግስት የልማት፣ የጤና እና የምግብ ዋስትና ድጋፎችን የሚያቀርብበትን አካሄድ በአዲስ መልክ ያዋቅራል።

ከዚህ ቀደም በአሜሪካ ዓለም አቀፍ የልማት ድርጅት (USAID) ይከናወኑ የነበሩ ቁልፍ ተግባራት፣ አሁን በቀጥታ በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ስር እንዲሆኑ ተደርጓል።

ይህም በሁለት የተለያዩ ቢሮዎች የሚሰሩ ተቀራራቢ ስራዎችን ወደ አንድ ማዕከል በማምጣት የተሻለ ቅንጅት ለመፍጠር ያለመ ነው ተብሏል።

ይህ ለውጥ ለኢትዮጵያ የሚሰጠው እርዳታ እንዲቋረጥ ያደርጋል? የሚለውን ጥያቄ "አንዳፍታ" በአዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ የሰጠውን መልስ በመጥቀስ እንደማይቋረጥ በዘገባው አመልክቷል፡፡

ኤምባሲው እንዳረጋገጠው፣ ከአሁኑ የኢትዮጵያ መንግስት ጋር የተደረሱ የእርዳታ ስምምነቶች እንደተጠበቁ ሆነው ይቀጥላሉ። በተለይም ህይወት አድን የሆኑና ወሳኝ ድጋፎች ማለትም፦ የሰብዓዊ እርዳታ፣ የዓለም አቀፍ የጤና ድጋፍ፣ የምግብ ዋስትና ፕሮግራሞች ሳይስተጓጎሉ በአዲሱ መዋቅር ስር ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተገልጿል።

በፕሬዚዳንት ትራምፕና በውጭ ጉዳይ ጸሃፊ ሩቢዮ አመራር የተጀመረው ይህ እቅድ፣ በመጨረሻም በዓለም ዙሪያ የሚሰጠው ድጋፍ ግቡን እንዲመታና ህይወት እንዲያድን ለማድረግ ያለመ ስልታዊ እርምጃ ነው ተብሏል፡፡
#addis_admas

1 year ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.