አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከዓለም በስንተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል?
#ethiopia | ሃርቫርድ ዩኒቨርሲቲ የአንደኝነቱን ደረጃ እንዳስጠበቀ ቀጥሏል
ኬፕታውን ዩኒቨርሲቲ ከአፍሪካ የአንደኝነት ደረጃ ይዟል
6 የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች በ"ግሎባል 2000" ዝርዝር ተካተዋል
የዓለም ዩኒቨርሲቲዎች ደረጃ አሰጣጥ ማዕከል በዘንድሮ እትሙ፣ ለ21,462 የትምህርት ተቋማት ደረጃ የሰጠ ሲሆን፤ ከእነዚህም መካከል ከፍተኛ ደረጃ ላይ የሚገኙትን "ግሎባል 2000" ዝርዝር ውስጥ አካቷል። በዚህ ዝርዝር ከተካተቱት ውስጥ ስድስት የኢትየጵያ ዩኒቨርሲቲዎች ይገኙበታል፡፡
ማዕከሉ ዩኒቨርሲቲዎችን በአለም አቀፍ ደረጃ ለመመዘን 74 ሚሊዮን የዳታ ነጥቦችን በአራት ዋና ዋና መለኪያዎች ላይ ተመስርቶ ገምግሟል፤ እነርሱም፡-
የትምህርት ጥራት (25%)
ቅጥር (ተቀጣሪነት) (25%)
የፋኩልቲዎች ጥራት (10%)
የምርምር አፈጻጸም (40%) ናቸው።
የአሜሪካ ዝነኛ የትምህርት ተቋም የሆነው ሃርቫርድ ዩኒቨርሲቲ፣ ለአስራ አራተኛ ተከታታይ ዓመት፣ የአንደኛ ደረጃነቱን አስጠብቆ የቀጠለ ሲሆን፤ የማሳቹሴትስ የቴክኖሎጂ ተቋምና የስታንፎርድ ዩኒቨርሲቲ ሁለተኛና ሦስተኛ ደረጃን ይዘዋል። የካምብሪጅ ዩኒቨርሲቲና የኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ ተከታዩ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል፡፡
ፕሪንስተን ዩኒቨርሲቲ፣ ፔንስልቬኒያ ዩኒቨርሲቲ፣ ኮሎምቢያ ዩኒቨርሲቲ፣ ዬል ዩኒቨርሲቲና ቺካጎ ዩኒቨርሲቲ ደግሞ ከስድስተኛ አስከ አስረኛ ያለውን ደረጃ የያዙ ሲሆን፤ ሁሉም የአሜሪካ የግል የትምህርት ተቋማት ናቸው።
በሌላ በኩል፤ ቻይና 346 ዩኒቨርሲቲዎቿ በ"ግሎባል 2000" ዝርዝር ውስጥ የተካተተላት ሲሆን፤ ብዛት ያላቸው ተቋማት በማካታት በአንደኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች፡፡
ከአፍሪካ የደቡብ አፍሪካው ኬፕታውን ዩኒቨርሲቲ ከአለም 271ኛ ደረጃ፣ ከአፍሪካ ደግሞ የአንደኛ ደረጃን ማግኘት ችሏል፡፡
የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች ደረጃ
አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ከኢትዮጵያ አንደኛ፣ ከአለም 808ኛ
ጎንደር ዩኒቨርስቲ ከኢትዮጵያ ሁለተኛ፣ ከአለም 1607ኛ
ጅማ ዩኒቨርስቲ ከኢትዮጵያ ሦስተኛ፣ ከአለም 1701ኛ
መቐሌዩኒቨርሲቲ ከኢትዮጵያ አራተኛ፣ ከአለም 1757ኛ
ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ከኢትዮጵያ አምስተኛ፣ ከአለም 1803ኛ
ሀረማያ ዩኒቨርሲቲ ከኢትዮጵያ ስድስተኛ፣ ከአለም 1903ኛ
የትምህርት መረጃ #addis_admas

11 months ago