Logo
YenetaTube
ጄነራል ታደሰ ወረደ ምን አሉ?

"ፌደራል መንግሥቱ በትግራይ ላይ ሌላ ዙር ጦርነት
ለመክፈት ዝግጅት እያደረገ ይገኛል"

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት ሌተናንት ጀኔራል ታደሠ ወረደ፣ ፌደራል መንግሥቱ በትግራይ ላይ ሌላ ዙር ጦርነት ለመክፈት ዝግጅት እያደረገ ይገኛል በማለት ትላንት በኢትዮጵያ ከተመድ የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን ሃላፊ ጋር በተወያዩበት ወቅት መናገራቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን አስታውቋል።

ጀኔራል ታደሰ፣ ጊዜያዊ አስተዳደሩ የጦርነት ደመናን ለመግፈፍና ከፍተኛ ጥረት እያደረገ መሆኑን ለሃላፊው እንዳረጋገጡላቸው ቢሮው ገልጧል።

በትግራይ በኩል የሚጀመር ጦርነት አይኖርም ያሉት ጀኔራል ታደሰ፣ ጊዜያዊ አስተዳደሩ በትግራይ የተሟላና ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን ከፌደራል መንግሥቱ፣ ከዓለማቀፍ ድርጅቶችና ከውጭ ዲፕሎማቶች ጋር የቅርብ ግንኙነት በማድረግ ላይ መሆኑንም ገልጸዋል ተብሏል።

Via addis admas

11 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.