Logo
Getu Temesgen
"የኢትዮጵያ የወደፊት ተስፋዋ በወጣቶች እጅ ላይ ነው"
#ethiopia | በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ብናልፍ አንዱዓለም፣ ታዳጊውን ትውልደ ኢትዮጵያዊ ሳይንቲስት በኤምባሲው ተቀብለው ማነጋገራቸው ተገለጸ፡፡

ሄመን በቀለ በአሜሪካ የቆዳ ካንሰርን የሚከላከል ሳሙና በመፍጠር እ.ኤ.አ 2023 "የአሜሪካ ከፍተኛ ወጣት ሳይንቲስት" የሚል ስያሜ ያገኘ ሲሆን፤ በ2024 ደግሞ ‘’Time Kid of the Year’’ ሆኖ ተመርጧል፡፡

ታዳጊው ኢትዮጵያዊ የፈጠረው ሳሙና በፀሐይ ጨረር ምክኒያት ሊከሰት የሚችል የቆዳ ካንሰርን ለመከላከል የሚያስችልና ለበርካቶች ተስፋን የሚሰጥ እድል ይዞ የመጣ እንደሆነ ተነግሮለታል፡፡

አምባሳደር ብናልፍ ወጣት ሄመንን ባነጋገሩበት ወቅት፣ ኢትዮጵያ የወደፊት ተስፋዋ በወጣቶች እጅ ላይ መሆኑን በጽኑ እንደሚያምኑና የሄመንም እንቅስቃሴ ይህንኑ እምነታቸውን ያረጋገጠላቸው መሆኑን አንስተዋል፡፡

በሰራው ስራ እውቅናና ሽልማት ማግኘቱ ብቻ ሳይሆን ለአገሩ ያለው ፍቅርና ተጋላጭ ለሆኑ ማህበረሰቦች የጤና አጠባበቅን ተደራሽ ለማድረግ ያለው ቁርጠኝነቱ እንዳስደነቃቸው አምባሳደሩ ገልጸዋል፡፡

በመጨረሻም ለነበራቸው ውይይት አመስግነው፤ ወጣቱ ለሚያደርገው ጥረት ኤምባሲው ሙሉ ድጋፉን እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል፡፡ #addis_admas

11 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.