Logo
YenetaTube
ማሊ ሁለተኛውን የሊቲየም ማዕድን ማውጫ አስመረቀች

*የ250 ሚሊዮን ዶላር ኢንቨስትመንት ነው ተብሏል

ማሊ ሁለተኛውን የሊቲየም ማዕድን ማውጫ በዛሬው ዕለት ማስመረቋን የፕሬዚዳንቱ ቢሮ አስታውቋል፡፡

የማዕድን ማውጫው የሚገኘው በቡጉኒ ክልል ሲሆን፣ በየዓመቱ 400 ሺህ ቶን የሊቲየም ክምችት ያመርታል ተብሎ ይጠበቃል። ይህም ማሊን ከአፍሪካ ግዙፍ የዘርፉ አምራቾች አንዷ ያደርጋታል ተብሏል።

"ሊቲየም ማይንስ ኦፍ ቡጉኒ"፤ የተባለው የማዕድን ማውጫ 65 በመቶው የብሪታኒያው ኮዳል ማይኒንግ ሲሆን፤ 35 በመቶው ደግሞ የማሊ መንግሥት ነው።

ፕሮጀክቱ የ250 ሚሊዮን ዶላር ኢንቨስትመንት መሆኑን የዘገበው ስፑትኒክ፤ በሺዎች ለሚቆጠሩ የማሊ ዜጎች ቀጥተኛና ቀጥተኛ ያልሆኑ የሥራ ዕድሎችን መፍጠሩን ጠቁሟል፡፡

የአፍሪካ ግዙፉ የማዕድን ማውጫ እንደሆነ የሚታሰበውና በቡጉኒ ክልል የሚገኘው የማሊ የመጀመሪያው የሊቲየም ማዕድን ማውጫ ጉላሚና ተብሎ የሚጠራ ሲሆን፤ በ2017 ዓ.ም አጋማሽ ላይ ወደ ስራ ገብቷል።

ሊቲየም በአሁኑ ወቅት ለኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ባትሪዎች፣ ለቀጣይ ትውልድ ተሽከርካሪዎችና ለዘመናዊ የቴክኖሎጂ መሣሪያዎች ምርት ወሳኝ የሆነ ስትራቴጂያዊ ብረት ነው።

Via Addis admas

7 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.