ከመነኮሳት ጋር ወሲብ ፈጽማ 11.9ሚ. ዶላር
ተቀብላለች የተባለችው ግለሰብ ተያዘች
#ethiopia | በታይላንድ ከቡድሂስት መነኮሳት ጋር ወሲብ ከፈጸመች በኋላ ፎቶዎችንና ቪዲዮዎችን ገንዘብ ለማግኘት በማስፈራሪያነት ተጠቅማ ከፍተኛ ሃብት አከማችታለች የተባለችው ግለሰብ በቁጥጥር ስር መዋሏን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
ፖሊስ "ሚስ ጎልፍ" በሚል ቅጽል ስም የጠራት ይህች ግለሰብ፣ ቢያንሰ ከዘጠኝ መነኮሳት ጋር ወሲብ መፈጸሟን ማክሰኞ ዕለት ፖሊስ በጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቋል።
ግለሰቧ በባለፉት ሦስት ዓመታት መነኮሳቱን አስፈራርታ 11.9 ሚሊዮን ዶላር እንዳገኘች ፖሊስ ያምናል።
ቤቷን የፈተሹ መርማሪዎች መነኮሳቱን ለማስፈራራት የተጠቀመችባቸውን ከ80 ሺህ በላይ ፎቶዎችንና ቪዲዮዎችን ማግኘታቸውን የፖሊስ ቃል አቀባይ ተናግረዋል።
በታይላንድ በቅድስና እና ክብር ከፍተኛ ስፍራ የሚሰጠው የቡድሂስት ተቋም በቅርብ ዓመታት ውስጥ በተለያዩ ቅሌቶች መነከሩ እየተነገረ ሲሆን፤ ከነዚህም ውስጥ አደገኛ ዕጽ ዝውውር እንዲሁም ወሲባዊ ጥቃቶች ናቸው። በቅርቡ የዚህች ግለሰብ ተግባር የእምነቱን ተቋም ያናጋ ሆኗል፤ ብሏል የቢቢሲ ዘገባ፡፡ #addis_admas

11 months ago