17 hours ago
ቪድዮ፦ በፓወር ፓንክ (Power Bank) አማካኝነት የተነሳው እሳት የኢንዲጎ አውሮፕላንን በድንገት እንዲያርፍ አስገደደው።
በህንድ ሀገር፣ ከዲልሂ ወደ ቼናይ እየበረረ በነበረ የኢንዲጎ አየር መንገድ በረራ ቁጥሩ 6E 6115 ላይ ተሳፋሪ በቦርሳ ይዞት የነበረ የፓወር ባንክ ከላይ ባለው የዕቃ ማስቀመጫ (Overhead bin) ውስጥ ድንገተኛ እሳት አደጋ እንዲነሳ አድርጓል።
አውሮፕላኑ ውስጥ 180 የሚጠጉ ተሳፋሪዎች እና 7 የካቢን ሰራተኞች ነበሩ።
እሳቱ በተሳፋሪዎች ዘንድ ከፍተኛ ድንጋጤና ግርግር የፈጠረ ሲሆን የካቢን ሰራተኞቹ ወዲያውኑ የእሳት ማጥፊያ በመጠቀም እሳቱን ማጥፋት ችለዋል።
አብራሪዎች ባላቸው የደህንነት ፕሮቶኮል መሰረት በረራውን በማዞር ሃይደራባድ በምትሰኝ ትልቅ ከተማ በሚገኝ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በሰላም አርፈዋል።
በሂደቱ በሰው ላይ የደረሰ አንዳችም ጉዳት የለም፤ ተሳፋሪዎችም ወደ መድረሻቸው ቼናይ በሌላ አማራጭ አውሮፕላን እንዲጓዙ መደረጉ ተዘግቧል።
ፓወር ባንኮች ውስጥ የሚገኙት የLithium-ion ባትሪዎች ሲጎዱ፣ ጫና ሲያርፍባቸው፣ ከመጠን በላይ ሲሞቁ ወይም ውስጣዊ የኤሌክትሪክ ብልሽት ሲገጥማቸው (ሾርት ሲያደርግ)፣ ሲበላሹ ከቁጥጥር ውጪ የሆነ ከፍተኛ ሙቀት በመፍጠር እሳት ሊያስነሱ አልያም ሊፈነዱ ይችላሉ።
ከላይ በዕቃ ማስቀመጫ ውስጥ በቦርሳ ሲቀመጥ ቦርሳ ውስጥ ያሉ አልባሳትን ፣ ወረቀቶችን ወይም ሌሎች ተቀጣጣይ ነገሮችን በማያያዝ እሳቱ ወደ ሌሎች ቦርሳዎች ወይም ቁሶች በፍጥነት ይሰፋል።
ፓወር ባንክ ከላይ ባለየአውሮፕላን ዕቃ ማስቀመጫ (Overhead bin) ወይም በታሸገ የሻንጣ ክፍል ውስጥ ማድረግ አይፈቀድም ፤ ምክንያቱም እሳት ቢነሳ እንኳን ወዲያው ላይታወቅ ይችላል። ከዛ ይልቅ በትንሽ የእጅ ዕቃ መያዣ አልያም በእጃችን አጠገባችን ብንይዝ ድንገት እሳት ቢነሳ የካቢን ሰራተኞች በፍጥነት እንዲቆጣጠሩት ይረዳል።
የምንጠቀማቸው ፓወር ባንኮችም መሰል ድንገተኛ አደጋዎችን እንዳይፈጥሩ ጥራታቸውና ደረጃቸው የተሻለ መሆን አለበት።
Video : Sudhakar Udmula
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ጥቅምት 2 ቀን 2019 ዓ/ም
@tikvahethiopia

1 day ago
በተደጋጋሚ ጊዜ ጨለማን ተገን በማድረግ የስርቆት ወንጀል የፈፀመው ግለሰብ በ20 አመት ከ10 ወር ፅኑ እስራት ተቀጣ
ደሳለኝ ጭናሾ የተባለው ተከሳሽ የስርቆት ወንጀሉን የፈፀመው በኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ ወረዳ 9 ልዩ ቦታው ጦር ኃይሎች አካባቢ በተለያየ ቀናት ነው።
ተከሳሹ ጨለማን ተገን በማድረግና በአካባቢው ላይ ጥበቃዎች አለመኖራቸውን እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም የአንድ ግለሰብ የሞባይል ስልክ መሸጫ ሱቅ የሻተር በር ተንጠልጣይ ቁልፍን በብረት መቁረጫ መጋዝ ቆርጦ በመግባት፣ የተለያዩ ስማርት ስልኮች፣ የሞባይል ባትሪዎች፣ በሶላር የሚሰራ ሬዲዮ፣ የሞባይል ቻርጀር፣ የጆሮ ማዳመጫ ኤርፎን፣ የእጅ ሰዓቶችና የልብስ መተኮሻ ካውያ በአጠቃላይ 1 መቶ ሺህ 450 ብር የሚገመት ንብረት ሰርቆ ለመሰወር ሲሞክር በስራ ላይ ሲንቀሳቀሱ በነበሩ የአውጉስታ አካባቢ ፖሊስ መምሪያ አባላት እጅ ከፍንጂ መያዙን ፖሊስ መምሪያው አስታውቋል።
ግለሰቡ በቁጥጥር ስር ከዋለ በኃላ በተከናወነ ምርመራ የማስፋት ስራ በተጨማሪም በተጠቀሰው አካባቢ ከአንድ ምግብ ቤት ውስጥ የበር ቁልፍ ገንጥሎ በመግባት 18,000 ብር የሚገመቱ 3 የወንበር ዥንጥላዎችን እንደሰረቀና ከደበቀበት ቦታም መርቶ በማሳየት ንብረቱን ማስመለስ እንደተቻለ የገለፀው የአውጉስታ አካባቢ ፖሊስ መምሪያ ተገቢውን ምርመራ በማጣራት በተከሳሹ ላይ አቃቤ ህግ ክስ እንደመሰረተበትም አስታውቋል።
የተከሳሽ ደሳለኝ ጭናሾን ጉዳይ የተመለከተው የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ኮልፌ ቀራንዮ ምድብ 3ኛ የወንጀል ችሎት የክስ መዝገቡን ከመረመረና የሰው ማስረጃዎችን ከአሰማ በኃላ በተከሳሹ ላይ የጥፋተኝነት ብይን ሰጥቷል።
ፍርድ ቤቱ ተከሳሹን ያስተምራል፣ ሌሎች ወንጀል ፈፃሚዎችን ያስጠነቅቃል በማለት ግለሰቡ በፈፀመው ተደጋጋሚ የስርቆት ወንጀል በሁለት መዝገቦች በ20 አመት ከ10 ወር ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ውሳኔ አስተላልፎበታል።
ህብረተሰቡ መሰል ወንጀል እንዳይፈፀምበት በንግድ ቤቶች አካባቢ አስተማማኝ ጥበቃ መቅጠርና የደህንነት ካሜራ መግጠም እንዳለበት ያሳሰበው የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ወንጀል ከተፈፀመም በአፋጣኝ ለፖሊስ በማመልከት ወንጀል ፈፃሚዎች እንዲያዙና በህግ አግባብ እንዲጠየቁ የበኩሉን ድርሻ ሊወጣ እንደሚገባ መልዕክቱን አስተላልፏል።

2 days ago
የእስራኤል ድሮን በኤርትራ‼️
ዘ- ጆርዳን ታየምስ የተባለው የደህንነት ሚዲያ መነሻውን ከእስራኤል ያደረገ አንድ የስለላ ድሮን በኤርትርራ ላይ የብዙ ሰአት ቅኝት ሲያደርግ ማምሸቱን ዘግቧል።
የሰሜኑ ጦርነት ወደ ኤርትራ መሬት እየተጠጋ ነው ያለው ይህ ጋዜጣ፣ አዲስ አበባ እራስን ለመከላከል በምታደረርገው ውጊያ ላይ እስራኤል አስፈላጊ የሆኑ ወታደራዊ የሳተላይት መረጃዎችን በመስጠት ውጊያው የቀይባህር መስመርን ሳያውክ እንዲጠናቀቅ እስራኤል የዶናልድ ትራፕን አመራር እያሳመነች ነው ብሏል።
እስራኤል በአፍሪካ ቀንድ ላይ የምታደርገውን እንቅስቃሴ ሲቃወምና ሲያወግዝ የነበረው የ35 አመቱ የአስመራው አገዛዝ ላይ ለውጥ እንዲመጣ ከፍተኛ ስራን እየሰራች መሆኑን የጠቀሰው ይህ ጋዜጣ፣ ግብፅ ኤርትራን በመጠቀም በኢትዮጵያ ላይ የረጅም ግዜ ውጊያ እንዲፈጠር አቅዳ እየሰራች ቢሆንም እስራኤል የጦርነቱን ሁኔታ አይታ የሲና በረሀን ለመቆጣጠር አዲስ ውጊያ መክፈት አስፈላጊነቱን እያጤነችበት ነው ሲል ነው የዘገበው።
እስራኤል ዜጎቿ ወደግብፅ መሬት እንዳይሄድ ያሳሰበችው ትናት ነው።
ሱሌማን አብደላ
Seledadotio

የኢትዮጵያ ታዳሽ ኢነርጂ ዘርፍን የሚያጠናክረው የ«ኤ ቱ ዜድ ኢነርጂስ» እና «አልፕ ሶላር/ሊጎ» የጋራ ኩባንያ በይፋ ተመሠረተ።
የኢትዮጵያን ታዳሽ የኢነርጂስ ዘርፍ ይበልጥ ለማዘመንና አቅሙን ከፍ ለማድረግ ታላቅ መሰረት የሚጥል አዲስ የጋራ ኩባንያ (Joint Venture) የምረቃ መርሐ ግብር ተካሄዷል።
«ኤ ቱ ዜድ ኢነርጂስ » (A to Z Energies) ከተባለው አገር በቀል ድርጅት ጋር፣ ዓለም አቀፍ ዝናን ካተረፉት የቻይና የኢነርጂስ እና የባትሪ ማኔጅመንት ሲስተም (BMS) ግዙፍ ካምፓኒዎች ከሆኑት ከ«አልፕ ሶላር / ሊጎ» (AlpSolarr / Ligoo) ጋር በመተባበር በኢትዮጵያ የተመሰረተው ይህ አዲስ ኩባንያ በይፋ ስራ መጀመሩ ተበስሯል።
ኩባንያው በ50 ሚሊዮን ዶላር የሼር ማዕቀፍ የተቋቋመ ሲሆን፣ ዘመናዊ ምርቶችን በቀጥታ ለአገር ውስጥ ገበያ እና ለምስራቅ አፍሪካ ቀጣና ማቅረብ የኩባንያው ዕቅድ ነው። IATF16949፣ ISO26262 እና ASPICE CL2ን በርካታ ዓለም አቀፍ የደህንነት እና የጥራት ማረጋገጫ ሰርተፊኬቶች ያሉት አውቶሞቲቭ-ግሬድ (Vehicle-grade) ምርቶች በኩባንያው እንደሚቀርቡ ተገልጿል።
ዋና አጋር የሆነው «ሊጎ» (Ligoo) እጅግ ዘመናዊ የሆኑ የባትሪ ማኔጅመንት ሲስተሞችን (BMS) በማልማት የ15 ዓመታት ልምድ ያለው ሲሆን፣ ከዓለም አቀፍ አውቶሞቲቭ ግዙፎች ጋር በመስራት ከፍተኛ የገበያ ድርሻ አለው። ከእነዚህም መካከል BYD፣ ጂሊ (Geely)፣ ቼሪ (Chery)፣ ኤስ.ጂ.ኤም.ደብሊዩ (SGMW) እና ቴስላ (Tesla) ይገኙበታል፡፡
በድርጅቱ ከሚቀርቡ ዋና ዋና ዘመናዊ የኢነርጂ መፍትሄዎች መካከል የቤት ውስጥ (Residential) እና የንግድ/ኢንዱስትሪ (C&I) የኢነርጂስ ማከማቻ ሲስተሞች (ESS)፣ ሃይብሪድ ኢንቨርተሮች (Hybrid Inverters) እና የሃይል ፍላጎትን በዘላቂነት ለማስተናገድ የተዘጋጁ የየኢነርጂ አስተዳደር አማራጮች ስለመሆናቸው ተነግሯል።
የኤ ቱ ዜድ ኢነርጂስ መሥራች እና ዋና ስራ አስፈጻሚ ሙጂብ አስመራ በሰጡት አስተያየት፣ "ይህ ትብብር የኩባንያችን ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያ የዘመናዊ ቴክኖሎጂ እና የኢነርጂስ ተደራሽነት ጉዞ ትልቅ ምዕራፍ ነው። ከዓለም አቀፍ አጋሮቻችን ከሊጎ እና አልፕ ሶላር ጋር በመሆን ሀገራችንን በኢነርጂስ አስተዳደር ዘርፍ የተሻለ ደረጃ ላይ ለማድረስ ቁርጠኞች ነን" ብለዋል።
ይህ የምረቃ መርሐ ግብር የሀገራችንን የኢንቨስትመንት ከፍታ የሚያሳይ አበረታች ምዕራፍ መሆኑ ተመላክቷል። ድርጅቱ ጎተራ ፔፒሲ 300 ሜትር አለፍ ብሎ ወደ ቄራ መንገድ በሚገኘው ሾው ሩም ጥሪ የተደረገላቸው ከፍተኛ የመንግስት ስራ ኃላፊዎች የሶሻም ሚዲያ ተፅዕኖፈጣሪዎች ተገኝተዋል።

3 days ago
በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ያለ ኢንተርኔት የሚሰራ የኤአይ (AI) የሳይበር ደህንነት መጠበቂያ ይፋ ተደረገ
#ethiopia | ኤስ.አር.ኢ ማኑፋክቸሪንግ እና ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር የተባለው ሀገር በቀል ኩባንያ ያለ ኢንተርኔት አገልግሎት መስጠት የሚችል ''ኤ አይ ሳይበር ጋርድ'' የተሰኘ የሳይበር ደህንነት መጠበቂያ መተግበሪያ ለህዝብ ይፋ አደረገ።
ኩባንያው ዛሬ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳሳወቀው መተግበሪያው በሰው ሰራሽ አስተውሎት የታገዘና ከግል ስልኮች ጀምሮ የገንዘብ ተቋማትንና የተለያዩ ግዙፍ ተቋማትን ከሳይበር ጥቃት የመከላከል አቅም ያለው ነው።
አገልግሎቱ ድረ-ገጾችን፣ የተቋማት ኔትወርኮችን፣ የባንክና የገንዘብ ተቋማት ሲስተሞችን እንዲሁም የግል መሣሪያዎችን ሙሉ በሙሉ የመጠበቅ አቅም ያለው ሲሆን፣ ዋነኛ ልዩ ባህሪው ያለ ኢንተርኔት ኮኔክሽን መስራት መቻሉ ነው።
ይህም የኢንተርኔት መቆራረጥ በሚኖርበት ጊዜም እንኳ ጥበቃው ሳይቋረጥ እንዲቀጥል ያስችለዋል።
በተጨማሪም የጥቃት ምልክቶችን ቀድሞ መለየት፣ አደጋዎችን መከላከል፣ ፈጣን ምላሽ መስጠትና ለወንጀል ምርመራ ስራዎች አስፈላጊውን ዲጂታል መረጃ በማቅረብ ረገድ ከፍተኛ እገዛ ያደርጋል።
የሳይበር ጥቃት በሚከሰትበት ጊዜም ከፍተኛ የቴክኖሎጂ እውቀት ለሌላቸው ሰዎች በሚገባ ቀላል ቋንቋ የችግሩን ሁኔታ ያስረዳል።
የድርጅቱ ስራ አስኪያጅ አቶ ሳሙኤል ከፈለኝ በሰጡት ማብሪርያ ተቋማትና ግለሰቦች ወደ ዲጂታል አሰራር በሚሸጋገሩበት በዚህ ወቅት የመረጃ ምንተፋ፣ የማንነት ስርቆትና የድረ-ገጽ ጠለፋ አደጋዎች እየጨመሩ መምጣታቸውን ጠቁመዋል።
ይህንን አደጋ ለመግታትም የ24 ሰዓት ንቁ ክትትል የሚያደርግና ለጥቃት ተጋላጭ የሆኑ አሰራሮችን የሚቆጣጠር ዘመናዊ የኤአይ ጥበቃ አስፈላጊ በመሆኑ መተግበሪያውን ለማልማት መቻላቸውን ገልጸዋል።
በኢትዮጵያ የቅጅ መብት ህግ መሠረት ሙሉ የአዕምሯዊ ንብረት ጥበቃ ያገኘው ይህ ሀገር በቀል ፈጠራ፣ ተቋማት የደህንነት ስጋታቸውን በአንድ መድረክ ላይ ተከታትለው በጊዜው እርምጃ እንዲወስዱ ያስችላቸዋል።
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን) #getutemesgen #getu

4 days ago
(ዘ-ሐበሻ ዜና) ሱዳኑ አልሂላል ክለብ ወደኢትዮጵያ ለሚያደርገው ጉዞ ‹‹የደህንነት ዋስትና›› ጠየቀ፡፡ የሱዳኑ አል ሂላል ኦምድሩማን ክለብ በአፍሪካ ሻምፒዮንስ ሊግ የማጣሪያ ግጥሚያ ከሲዳማ ቡና ጋር የሚጫወት መሆኑ ይታወቃል፡፡
ይህ ግጥሚያ አንድ ሳምንት የቀረው መሆኑን ተከትሎ ክለቡ ለአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን(ካፍ) አስቸኳይ ደብዳቤ ፅፏል፡፡ ‹‹ይድረስ ለካፍ የደህንነትና ፀጥታ ሀላፊ›› በሚል የተፃፈው ይህ ደብዳቤ በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች ስላለው የፀጥታ ችግር ቀጥተኛና ቀጥተኛ ባልሆነ መንገድ ከሚገኙ መረጃዎች ለማወቅ እንደተቻለ ጠቅሶ ጉዳዩ እንዳሳሰበው ይገልፃል፡፡ በክለቡ ዳይሬክተሮች ቦርድ ዋና ፀሀፊ ዶክተር ሀሰን አሊ ኢሳ አማካኝነት የተፃፈው ይህ ደብዳቤ ሲቀጥልም ‹‹የአል ሂላል ቡድን አባላት ወደኢትዮጵያ ለመጓዝ ዝግጅት እያደረጉ በመሆኑ ለአባሎቻችን ደህንነትና ጥበቃ ቅድሚያ የምንሰጥ መሆኑን ለማስታወቅ እንወዳለን›› ካለ በኋላ ካፍ ከደህንነትና ሎጅስቲክስ ጉዳዮች ጋር በተያያዘ ለሚከተሉት ነጥቦች አስቸኳይ ማብራሪያ እንዲሰጠው ጠይቋል፡፡ ከእነዚህ ነጥቦች የመጀመሪያው የክለቡ አባላት ወደኢትዮጵያ ለሚያደርጉት የአውሮፕላን ጉዞ ደህንነት ምን አይነት ዋስትና ተዘጋጅቷል? የሚል ነው፡፡
ይህ ጥያቄም የቡድኑን አዲስ አበባ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ መድረስንና ከዚያም ጨዋታው ወደሚካሄድበት ድሬደዋ ከተማ የሚካሄደውን የአገር ውስጥ በረራ እንደሚያካትት አስረድቷል፡፡ ሁለተኛው ጥያቄ የአል ሂላል ቡድን አባላት አዲስ አበባ ከደረሱ በኋላ ድሬዳዋ እስከሚሄዱ ድረስ ደህንነታቸውን ለማረጋገጥ የሚያስችል ምን አይነት ዝግጅት ተደርጓል? የሚል ሲሆን ሶስተኛው ደግሞ ልኡካን ቡድኑ በድሬዳዋ ቆይታው በማረፊያውና ልምምድ በሚያደርግበት ቦታ ምን አይነት የደህንነት ጥበቃ ይደረጋል? የሚል ነው፡፡ በአራተኛነት ጨዋታው ከተጠናቀቀ በኋላ የክለቡ ተጨዋቾች፣ የቴክኒክና የአስተዳደር ቡድን አባላቱ በሰላም ወደኪጋሊ እንዲመለሱ ለማስቻል የተደረገው ዝግጅት እንዲገለፅለት ጠይቋል፡፡

ዛሬ ሹመታቸውን የተቀበሉት ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) ከተመድ ምክትል ዋና ጸሐፊ ጋር ውይይት አደረጉ
#ethiopia | የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) ምክትል ዋና ጸሐፊ አሚና ጄን መሐመድ ጋር ዛሬ ተወያይተዋል።
ሁለቱ ወገኖች በውይይታቸውም በአፍሪካ ቀንድ ወቅታዊ የፀጥታ እና የደህንነት ጉዳዮች ላይ ምክክር አድርገዋል፡፡
ለይፋዊ የስራ ጉብኝት አዲስ አበባ የገቡት ምክትል ዋና ፀሐፊዋ አሚና ጄን ሙሀመድ ኢትዮጵያ እና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ቅድሚያ በሚሰጧቸው የጋራ ጉዳዮች ላይ ትኩረት በማድረግ እንደሚመክሩ ተመላክቷል፡፡
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን) #getutemesgen #getu
#ethiopia | የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) ምክትል ዋና ጸሐፊ አሚና ጄን መሐመድ ጋር ዛሬ ተወያይተዋል።
ሁለቱ ወገኖች በውይይታቸውም በአፍሪካ ቀንድ ወቅታዊ የፀጥታ እና የደህንነት ጉዳዮች ላይ ምክክር አድርገዋል፡፡
ለይፋዊ የስራ ጉብኝት አዲስ አበባ የገቡት ምክትል ዋና ፀሐፊዋ አሚና ጄን ሙሀመድ ኢትዮጵያ እና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ቅድሚያ በሚሰጧቸው የጋራ ጉዳዮች ላይ ትኩረት በማድረግ እንደሚመክሩ ተመላክቷል፡፡
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን) #getutemesgen #getu
4 days ago
(ዘ-ሐበሻ ዜና) በኢራን የሚደገፈው የየመኑ የሁቲ አማፂ ቡድን ሐሙስ ዕለት ባወጣው መግለጫ በሳዑዲ ዓረቢያ ዋና ከተማ ሪያድ በሚገኘው ዋነኛ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ላይ የባሊስቲክ ሚሳኤል ጥቃት ማድረሱን ይፋ አድርጓል። ይህ ጥቃት ቡድኑ በሳዑዲ ዓረቢያ ግዛት ውስጥ ከፈጸማቸው ተከታታይ ጥቃቶች መካከል አዲሱ ነው።
የቡድኑ ወታደራዊ ቃል አቀባይ ያህያ ሳሬ በኤክስ ማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት መልዕክት፣ "የታጠቁ ኃይሎቻችን በሪያድ የሚገኘውን የኪንግ ካሊድ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በባሊስቲክ ሚሳኤል በተሳካ ሁኔታ ኢላማ አድርገዋል፤ ሚሳኤሉም ኢላማውን በትክክል በመምታት የአውሮፕላን ማረፊያውን መደበኛ እንቅስቃሴ አቋርጧል" ሲሉ ጥቃቱን በተመለከተ ማረጋገጫ ሰጥተዋል።
ይህ የሁቲዎች መግለጫ የሚያሳየው አማፂያኑ ከወታደራዊ ኢላማዎች አልፈው የሲቪል አቪዬሽን እና ከፍተኛ የኢኮኖሚ መሠረተ ልማቶችን ኢላማ የማድረግ ስልታቸውን አጠናክረው መቀጠላቸውን ነው። የኪንግ ካሊድ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በሳዑዲ ዓረቢያ እጅግ ሥራ ከሚበዛባቸው የሲቪል አየር ማረፊያዎች አንዱ በመሆኑ፣ ይህ ጥቃት የሀገሪቱን ዕለታዊ እንቅስቃሴ ከማስተጓጎል ባለፈ ዓለም አቀፍ መንገደኞች ላይ ከፍተኛ የደህንነት ስጋት የሚፈጥር ነው። የሳዑዲ መንግስት በአውሮፕላን ማረፊያው ላይ ስለደረሰው ጉዳት መጠን እስካሁን የሰጠው ይፋዊ መግለጫ ባይኖርም፣ የሁቲዎች የረጅም ርቀት ሚሳኤል የማስወንጨፍ አቅም የመካከለኛው ምሥራቅን የጸጥታ ቀውስ ይበልጥ ውስብስብ እያደረገው ይገኛል።
ይህ እየተባባሰ የመጣው የሁቲዎች የረጅም ርቀት ሚሳኤል ጥቃት በቀጠናው ሰላም ላይ ምን ዓይነት አዲስ ቀውስ ሊፈጥር ይችላል ብላችሁ ታስባላችሁ?

5 days ago
የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን የጥራት ጉድለት በታየባቸው ሰባት የመድኃኒት ምርቶች ላይ ማሳሰቢያ አወጣ
የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን የጥራት ጉድለት በታየባቸው እና ከገበያ እንዲሰበሰቡ በተወሰነባቸው ሰባት የመድኃኒት አይነቶች ላይ ህብረተሰቡ ጥንቃቄ እንዲያደርግ አሳስቧል።
ባለስልጣኑ ይህንን ማስጠንቀቂያ ያወጣው የኬንያ የመድኃኒት ተቆጣጣሪ አካል በሀገሪቱ በገበያ ላይ በተገኙ የተወሰኑ ምርቶች ላይ እርምጃ መውሰዱን መነሻ በማድረግ ነው።
ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የመድኃኒት ጥራት እና ደህንነት ክትትል ክፍል አማካሪ ዶ/ር ኤልሳቤት ወልደማርያም እንደተናገሩት ኢትዮጵያ እና ኬንያ ሰፊ ድንበር የሚጋሩ በመሆናቸው እነዚህ ምርቶች ወደ ኢትዮጵያ የመግባት ዕድል አላቸው።
በተለያዩ የጥራት እና የደህንነት ጉድለቶች ምክንያት ከገበያ እንዲሰበሰቡ ከተደረጉት ሰባት የመድኃኒት አይነቶች መካከል በህንድ የተለያዩ የመድኃኒት አምራች ኩባንያዎች የተመረቱት
👉ፍላዛርት ሽሮፕ
👉ሄፓካል 25000
👉ቱናክላቭ እና ክላክሲ 1.2 ግራም የተባሉ የመድኃኒት አይነቶች ይገኙበታል።
በተጨማሪም በቻይና ኩባንያ የተመረተው ሜታሚድ መርፌ እና በኬንያ አምራች የተመረተው ክሎክሳም ሽሮፕም ከተሰበሰቡት የመድኃኒት አይነቶች ውስጥ እንደሚገኙበት ተገልጿል።
በዚህም የክልል ተቆጣጣሪ አካላት የእነዚህን ምርቶች ስርጭት እና አጠቃቀም በቅርበት እንዲከታተሉ ያሳሰበው ባለስልጣኑ ህብረተሰቡም ምርቶቹ በእጁ የሚገኙ ከሆነ እንዳይጠቀምባቸው ጥብቅ ማሳሰቢያ ሰጥቷል።
በፋሲል አረጋይ

Sponsored by
Surafel
5 days ago
ኬንያ 109 የተደራጁ ወንጀለኛ ቡድኖችን ዝርዝር ይፋ አደረገች።
የኬንያ መንግሥት በሀገሪቱ 109 የተደራጁ የወንጀል ቡድኖችን ለይቶ ማውጣቱን አስታውቋል። ይህ ቁጥር በ2016 በGazette Notice No. 10427 ህገ-ወጥ ከተባሉ 89 ቡድኖች ጭማሪ ነው።
የተደራጁ የወጣት ቡድኖች ለፖለቲካ ማስፈራራት፣ ጥቃት እና ትንኮሳ ውስጥ መሳተፋቸው በስጋትነት ሲጠቀስ፥ ኬኒያ በ2027 ለምታካሂደው አጠቃላይ ምርጫ ከባድ የደህንነት ፈተና ሊሆን እንደሚችልም ተጠቁሟል።
«ጥቃት፣ ማስፈራራት እና የወንጀል ቡድኖችን ለፖለቲካ ጥቅም መጠቀም በዚህ ሂደት ውስጥ ቦታ የላቸውም» ብለዋል።
መንግሥት ባወጣው መረጃ መሰረት ምዕራብ ኬንያ 38 የሚሆኑ የተደራጁ ወንጀለኛ ቡድኖች የሚገኙባት ግዛት ስትሆን ሪፍት ቫሊ 22፤ እንዲሁም ናይሮቢ 20 የተመዘገቡባቸው ግዛቶች ሆነዋል።
በናይሮቢ የህዝብ ትራንስፖርት እና አነስተኛ ንግድ ላይ የሚደረግ ማስገደድ፣ በባህር ዳርቻ በቢላና በስለት የሚፈጸም ጥቃት፣ በሪፍት ቫሊና በድንበር ደግሞ የመሳሪያ ዝውውርና የከብት ዘረፋ የቆዩ መታወቂያዎች ሲሆኑ፣ እነዚህ ቡድኖች በፖለቲካ ውስጥ መሳተፍ መጀመራቸው ስጋት ሆኖ ተቀምጧል።
መንግሥት ምርመራውን ከግለሰብ ወንጀለኞች ባሻገር የቡድን መሪዎችን፣ ቅጥረኞችን እና ፋይናንስ አቅራቢዎችን እየተከታተለ መሆኑን ሲገልጽ፣ የተወሰኑ እንቅስቃሴዎች ድንበር ተሻጋሪ በመሆናቸው ከጎረቤት ሀገራት ጋር የሚደረግ ትብብርም እየተጠናከረ ነው ሲል አስታውቋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መስከረም 27 ቀን 2019 ዓ.ም
@TikvahethMagazine

መስከረም 27 ቀን 2019 ዓ.ም. (አሐዱ ሬድዮ) የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን የጥራት ጉድለት በታየባቸው እና ከገበያ እንዲሰበሰቡ በተወሰነባቸው ሰባት የመድኃኒት አይነቶች ላይ ህብረተሰቡ ጥንቃቄ እንዲያደርግ አሳስቧል።
ባለስልጣኑ ይህንን ማስጠንቀቂያ ያወጣው የኬንያ የመድኃኒት ተቆጣጣሪ አካል በሀገሪቱ በገበያ ላይ በተገኙ የተወሰኑ ምርቶች ላይ እርምጃ መውሰዱን መነሻ በማድረግ ነው።
ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የመድኃኒት ጥራት እና ደህንነት ክትትል ክፍል አማካሪ ዶ/ር ኤልሳቤት ወልደማርያም ለአሐዱ ሬዲዮ እንደተናገሩት ኢትዮጵያ እና ኬንያ ሰፊ ድንበር የሚጋሩ በመሆናቸው እነዚህ ምርቶች ወደ ኢትዮጵያ የመግባት ዕድል አላቸው።
በተለያዩ የጥራት እና የደህንነት ጉድለቶች ምክንያት ከገበያ እንዲሰበሰቡ ከተደረጉት ሰባት የመድኃኒት አይነቶች መካከል በህንድ የተለያዩ የመድኃኒት አምራች ኩባንያዎች የተመረቱት ፍላዛርት ሽሮፕ ፣ ሄፓካል 25000 ፣ ቱናክላቭ እና ክላክሲ 1.2 ግራም የተባሉ የመድኃኒት አይነቶች ይገኙበታል።
በተጨማሪም በቻይና ኩባንያ የተመረተው ሜታሚድ መርፌ እና በኬንያ አምራች የተመረተው ክሎክሳም ሽሮፕም ከተሰበሰቡት የመድኃኒት አይነቶች ውስጥ እንደሚገኙበት ተገልጿል።
በዚህም የክልል ተቆጣጣሪ አካላት የእነዚህን ምርቶች ስርጭት እና አጠቃቀም በቅርበት እንዲከታተሉ ያሳሰበው ባለስልጣኑ ህብረተሰቡም ምርቶቹ በእጁ የሚገኙ ከሆነ እንዳይጠቀምባቸው ጥብቅ ማሳሰቢያ ሰጥቷል።
በፋሲል አረጋይ
#አሐዱ_ሬዲዮ_94 .3
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

በማህበራዊ ሚዲያ በሚደረጉ የመኖሪያ ቤት ምግብ ሽያጮች ላይ የጤና ስጋት ጥቆማ ከደረሰ ህጋዊ እርምጃ እንደሚወሰድ ተገለጸ
መስከረም 27 ቀን 2019 ዓ.ም. (አሐዱ ሬድዮ) በአሁኑ ወቅት በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች አማካይነት የኦንላይን የምግብ ማዘዣዎችን በመቀበል፣ በግል መኖሪያ ቤቶችና በድብቅ ቦታዎች ተዘጋጅተው የሚቀርቡ የምግብ ምርቶች ላይ የጤናና የደህንነት ስጋት መኖሩ ከተጠቆመ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ህጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ የአዲስ አበባ ምግብና መድኃኒት ቁጥጥር ባለሥልጣን ለአሐዱ አስታውቋል።
ተቋሙ የብቃት ማረጋገጫ (ሰርተፊኬት) ሰጥቶ እውቅና ከሰጣቸው ህጋዊ የምግብና የጤና ተቋማት ውጭ በኦንላይንና በመኖሪያ ቤቶች ደረጃ በድብቅ የሚሰጡ አገልግሎቶችን ተቋሙ አስቀድሞ የማወቅና የመቆጣጠር አሰራር እንደሌለው ለአሐዱ የተናገሩት የባለሥልጣኑ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር ወ/ሮ ወርቅነሽ ብርቄ ናቸው
ነገር ግን በማህበራዊ ሚዲያ በሚደረጉ የቤት ለቤት የምግብ ዝግጅትና ሽያጮች ላይ በህብረተሰቡ በኩል የጥራት፣ የደህንነት ወይም የጤና ስጋት መኖሩን የሚያመላክቱ ጥቆማዎች ከደረሱ፣ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ጥቆማውን መሰረት በማድረግ የተገለጹትን ቦታዎች በመፈተሽና በመቆጣጠር አስፈላጊውን ህጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ ተናግረዋል።
ማንኛውም የምግብ ዝግጅትና ማቅረብ ስራ ላይ ለመሰማራት የሚፈልግ አካል አስቀድሞ ወደ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በመቅረብ የብቃት ማረጋገጫ መስፈርቶችን ማሟላት ይኖርበታል ብለዋል።
አስፈላጊውን ደረጃ አሟልተው የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ሳይይዙ ምግብ ማዘጋጀትና ማሰራጨት በራሱ ህገ-ወጥነት በመሆኑ፣ በጥቆማ በሚደረጉ ፍተሻዎች ጥፋተኛ ሆነው በተገኙ አካላት ላይ ተጠያቂነት እንደሚሰፍን አሳስበዋል።
አክለውም ፤የባለስልጣኑ ባለሞያዎች መስፈርቱን አሟልተው የተመዘገቡ ህጋዊ ተቋማትን በቀጣይነት በዓመት አራት ጊዜና እንደ አስፈላጊነቱ በየጊዜው የክትትልና የቁጥጥር ስራ እንደሚያከናውኑባቸው ገልጸዋል።
ህብረተሰቡም በጤናና በምግብ ደህንነት ላይ ስጋት የሚፈጥሩ መሰል ህገ-ወጥ አሰራሮችን ሲታዘብ ጥቆማ በመስጠት መተባበር እንዳለበት ጠቁመዋል።
በወልደሐዋርያት ዘነበ
#አሐዱ_ሬዲዮ_94 .3
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ Photo

ሼር
🚗 የቴስላ ሳይበር ካብ (Tesla Cybercab)፡ አለምን የሚቀይረው መኪና!
ከሰሞኑ በአካል ወደ ኦስቲን ሄጄ ይህንን የኢላን ማስክን አዲስና አስገራሚ ፈጠራ የሆነውን "የቴስላ ሳይበር ካብ" (Tesla Cybercab) በቅርበት የመጎብኘት እና ኤክስፒሪያንስ የማድረግ ልዩ እድል አግኝቻለሁ። ይህ ወርቃማው መኪና ዝም ብሎ ተራ መኪና አይደለም፤ የዓለምን የትራንስፖርት ታሪክ በአዲስ መልክ የሚጽፍ ተአምረኛ ቴክኖሎጂ እንጂ!
በአካል ስመለከተውና ስሞክረው የተሰማኝን ስሜት እንዲሁም የመኪናውን አስገራሚ ገጽታዎች በዝርዝር የሚያሳየውን ሙሉ ቪዲዮ በቅርቡ በቻናሌ የማጋራችሁ ይሆናል። ዛሬ ግን ይህ መኪና ለምን አለምን እንደሚቀይር እና ከዚህ ቀደም ከነበሩት እንዴት እንደሚለይ ላካፍላችሁ።
ከዚህ ቀደም የነበሩት እንደ ዙግስ (Zoox) ወይም ዌይሞ (Waymo) ያሉ ራሳቸውን የሚነዱ መኪኖች ውድ የሆነውን የ'ላይዳር' (LiDAR) ሴንሰር የሚጠቀሙ፣ በተወሰነ ክልል እና ካርታ (Geofenced) ብቻ የሚሰሩ እንዲሁም ለግለሰብ የማይሸጡ ነበሩ። የቴስላው ሳይበር ካብ ግን ከነዚህ ፈጽሞ የተለየ ነው! እጅግ ውድ የሆኑ ሴንሰሮችን ትቶ በካሜራ (Vision-only) እና በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) ብቻ የሚሰራ፣ ለግለሰብ ባለቤትነት የሚሸጥ እና ከሁሉ በላይ ደግሞ መሪም ሆነ የፍሬን ፔዳል ፈጽሞ የሌለው አብዮታዊ መኪና ነው።
የቴስላ ሳይበር ካብ አለምን የሚቀይርባቸው 10 ቁልፍ ምክንያቶች፦
1. መሪ እና ፔዳል አልባ ቴክኖሎጂ (No Steering Wheel & Pedals): ይህ መኪና ሙሉ በሙሉ በሰው አልባ ቴክኖሎጂ የሚመራ በመሆኑ የሰው ልጅ ጣልቃ ገብነት (መሪ መዘወርም ሆነ ፍሬን መርገጥ) አይፈልግም። ውስጡ ሲገባ ልክ እንደ ምቹ ሳሎን ዘና ብሎ መጓዝ ብቻ ነው።
2. የትራንስፖርት ዋጋን ከመሬት ማውረዱ:
በአሁኑ ሰዓት በኡበር ወይም በታክሲ ለመጓዝ ከምንከፍለው ዋጋ በተለየ መልኩ፣ ሳይበር ካብ የጉዞ ወጪን በከፍተኛ ሁኔታ (በአንድ ማይል እስከ 20 ሳንቲም) በመቀነስ ትራንስፖርትን እንደ አውቶቡስ ርካሽ ያደርገዋል።
3. እጅግ ተመጣጣኝ የሆነ የመሸጫ ዋጋ (Affordability):
አዳዲስ እና ዘመናዊ መኪኖች እጅግ ውድ በሆኑበት በዚህ ዘመን፣ ሳይበር ካብ ከ30 ሺህ ዶላር በታች በሆነ ዋጋ ለገበያ ስለሚቀርብ በርካታ ሰዎች በቀላሉ ሊገዙት ይችላሉ።
4. ገመድ አልባ ቻርጂንግ (Inductive Charging):
ልክ እንደ ስማርት ስልኮች ሁሉ፣ ይህ መኪና ቻርጅ ለማድረግ ገመድ መሰካት አይጠበቅበትም። ቻርጀሩ (ፓዱ) ላይ ራሱ ሄዶ ሲቆም ያለ ምንም ንክኪ ዋየርለስ (Wireless) ቻርጅ ያደርጋል።
5. አዲስ የገቢ ምንጭ መፍጠሩ (Airbnb for Cars):
ይህ መኪና አለምን ከሚቀይርባቸው ትልቁ መንገድ አንዱ ይሄ ነው። መኪናዎን በማይጠቀሙበት ሰዓት (ለምሳሌ ስራ ቦታ ሆነው ወይም ተኝተው) ልክ እንደ ኡበር ራሱ እየሰራ እና ሰዎችን እያመላለሰ ገንዘብ እንዲያስገባላችሁ ማድረግ ትችላላችሁ።
6. ለማንኛውም ግለሰብ በባለቤትነት መፈቀዱ:
ሌሎች ራሳቸውን የሚነዱ መኪኖች (እንደ Zoox) ለኩባንያ አገልግሎት ብቻ ሲውሉ፣ ሳይበር ካብን ግን ማንኛውም ግለሰብ ገዝቶ የግሉ ማድረግ ይችላል።
7. የላቀ የካሜራ እና AI ቴክኖሎጂ (End-to-End AI):
ውድ የሆኑ የሌዘር ሴንሰሮችን (LiDAR) ባለመጠቀም፣ በካሜራዎች እና በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ብቻ ልክ እንደ ሰው አይቶ በማሰብ እና በመተንተን ማሽከርከር መቻሉ ቴክኖሎጂውን ወደ አዲስ ምዕራፍ አሸጋግሮታል።
8. ከፍተኛ የደህንነት ጥበቃ (Superhuman Safety):
ኮምፒውተሮች ከሰው ልጅ ይልቅ እጅግ ፈጣን ውሳኔ ስለሚሰጡ፣ በስልክ ስለማይዘናጉ፣ እንቅልፍ ስለማይመጣባቸው እና ስለማይደክማቸው፤ ይህ መኪና የትራፊክ አደጋን በከፍተኛ ደረጃ በመቀነስ የሰዎችን ህይወት ይታደጋል።
9. የመኪና ማቆሚያ (Parking) ችግርን መፍታቱ:
መኪናው እርስዎን ከስራ ቦታዎ ወይም ከገበያ ማዕከል አድርሶ ሌላ ስራ ስለሚሄድ ወይም ራሱ ሄዶ ሩቅ ቦታ ስለሚያቆም፣ በከተሞች ላይ ያለውን የፓርኪንግ ቦታ መጨናነቅ ሙሉ በሙሉ ያስቀራል።
10. በጉዞ ላይ ጊዜን በአግባቡ መጠቀም:
መኪናው ራሱን ስለሚነዳ፣ ተሳፋሪዎች በጉዞ ሰዓት ትኩረታቸውን መንገድ ላይ ማድረግ አይጠበቅባቸውም። በምትኩ መተኛት፣ ፊልም ማየት፣ ማንበብ ወይም ስራቸውን በላፕቶፕ መስራት ይችላሉ።
ይህ ቴክኖሎጂ የሰው ልጅን የዕለት ተዕለት ኑሮ በእጅጉ የሚቀይር ነው። ቪዲዮው እስኪደርሳችሁ ድረስ ቻናሌን ሰብስክራይብ በማድረግ ጠብቁኝ! እናንተስ ስለዚህ አዲስ መኪና ምን ታስባላችሁ? ሀሳባችሁን ኮመንት ላይ አስቀምጡልኝ!

6 days ago
(ዘ-ሐበሻ ዜና) በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የኤርትራ አምባሳደር ሶፊያ ተስፋማርያም፣ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ለዘመናት በኢትዮጵያ ላይ ሲከተለው የቆየውን ፖለቲካዊ አካሄድ እና "የስትራቴጂካዊ መቻቻል" ፖሊሲን በጽኑ የሚተች ሰፋ ያለ ትንታኔ አውጥተዋል። አምባሳደሯ በትንታኔያቸው ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ "የኢትዮጵያን ችግር እንዴት እንፍታው?" የሚል የተሳሳተ ጥያቄ ከማንሳት ይልቅ፣ ለተከታታይ የኢትዮጵያ መንግሥታት ሲሰጥ የነበረውን ያለገደብ የፖለቲካ እና የደህንነት ድጋፍ ሊመረምር ይገባል ብለዋል። ዋናው ችግር የኢትዮጵያ ሕዝብ ሳይሆን፣ መንግሥታት የሀገሪቱን ጂኦ-ፖለቲካዊ አቀማመጥ በመጠቀም ከተጠያቂነት የሚያመልጡበት የውጭ ኃይሎች የድጋፍ ስልት መሆኑን አስረድተዋል።
ከቀዝቃዛው ጦርነት ጊዜ ጀምሮ እስከ አሁን ያለው የብልጽግና ፓርቲ መንግሥት ድረስ፣ ተከታታይ የኢትዮጵያ መሪዎች ሀገሪቱ ያላትን ስትራቴጂካዊ አስፈላጊነት በመጠቀም የውጭ ፖለቲካዊ፣ ወታደራዊ እና የገንዘብ ድጋፍን ማግኘት መቻላቸውን ትንታኔው ያብራራል። ይህ የውጭ ኃይሎች ስትራቴጂካዊ ትብብርም ለመንግሥታቱ እንደ ፖለቲካዊ ጋሻ በማገልገል፣ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እና የውስጥ ጭቆናዎች ተጠያቂነት እንዳይኖራቸው ማድረጉን አምባሳደሯ ተችተዋል። በዚህም ሳቢያ ተራው ዜጋ ከፍተኛ የሆነ ሰብዓዊ እና ኢኮኖሚያዊ ዋጋ እየከፈለ እንደሚገኝ አክለዋል።
በተጨማሪም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ጎልቶ የመጣውን የቀይ ባህር እና የባህር በር ጉዳይ በተመለከተ፣ አምባሳደር ሶፊያ የኢትዮጵያ ፍላጎት በድርድር፣ በንግድ ስምምነቶች እና በጋራ ተጠቃሚነት ላይ በተመሰረተ ቀጠናዊ ትስስር ሊፈታ እንደሚችል አመላክተዋል። ዓለም አቀፍ ሕግ ወደብ አልባ መሆንን የሌላን ሉዓላዊ አገር ግዛት ወይም የባህር ሃብት የመጠየቅ መብት አድርጎ እንደማይቀይረው በማስገንዘብ፣ የጂኦግራፊያዊ አቀማመጥ እጥረትን ለመፍታት ትብብር እንጂ አዲስ የሉዓላዊነት መብት መፍጠር መፍትሄ አይሆንም ሲሉ ሞግተዋል።
አምባሳደሯ "የኢትዮ-ኤርትራ ቀውስ" እየተባለ የሚራገበው ትርክት፣ የኢትዮጵያን ውስጣዊ የፖለቲካ መከፋፈል እና የትጥቅ ግጭቶች ለመሸፈን በፖለቲካ ልሂቃን እና በግጭት ነጋዴዎች ሆን ተብሎ የተፈበረከ መሆኑን አስታውቀዋል። ኤርትራ ለሚሰነዘሩ ትንኮሳዎች እና አነቃቂ ንግግሮች አጸፋዊ ምላሽ አለመስጠቷን እንደ መባባስ መቆጠር እንደሌለበት እና ይህ እራስን የመግታት እርምጃ ለቀጠናው መረጋጋት ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳለው አብራርተዋል። የኢትዮጵያን የውስጥ ችግሮች ውጫዊ በማድረግ ወደ ኤርትራ ማላከክ መፍትሄ እንደማያመጣ ጠቁመዋል።
አምባሳደር ሶፊያ ጽሁፋቸውን ሲቋጩም... ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ የኢትዮጵያን ሕዝብ መደገፍ ቢኖርበትም፣ ለመንግሥት ግን ያለገደብ ነጻ ፈቃድ (መስጠቱን ሊያቆም ይገባል ሲሉ አሳስበዋል። የውጭ አጋሮች ፖለቲካዊ መቻቻልን ከማስቀደም ይልቅ ተጠያቂነትን፣ የዓለም አቀፍ ሕግጋት መከበርን እና የጎረቤት አገራትን ሉዓላዊነት የሚያስከብር ጠንካራ የዲፕሎማሲ አካሄድ ሊከተሉ እንደሚገባ ጥሪ አቅርበዋል።

7 days ago
(ዘ-ሐበሻ ዜና) በመካከለኛው ምስራቅ የጂኦ-ፖለቲካ የቼዝ ጠረጴዛ ላይ፣ የየመኑ ጦርነት አዳዲስ እና ወሳኝ ወታደራዊ ክስተቶችን እያስተናገደ ይገኛል። የሁቲ አማፂያንን በመውጋት ላይ የሚገኘው ሳዑዲ መራሹ ጥምረት በሁዳይዳ ግዛት የባህር ኃይል ወታደራዊ ዘመቻ ማካሄዱን ሲያስታውቅ፤ በዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅና የተሰጠው የየመን መንግስት ጦር በበኩሉ፣ ከባብ አል-ማንደብ ስትሬት በስተደቡብ ካደረገው ውጊያ በኋላ የሞካ ከተማን ከሁቲዎች እጅ መልሶ መቆጣጠሩን አረጋግጧል።
ይሁን እንጂ፣ የሁቲ አማፂያን ይህንን ወታደራዊ ጫና በዝምታ አላለፉትም። የቡድኑ ወታደራዊ ቃል አቀባይ እንዳስታወቁት፣ ታጣቂዎቻቸው በሳዑዲ አረቢያ ዋና ከተማ ሪያድ በሚገኘው የኪንግ ካሊድ አውሮፕላን ማረፊያ እና በራቢግ ከተማ በሚገኘው ግዙፉ የአራምኮ የነዳጅ ማጣሪያ ላይ ጥቃት ሰንዝረዋል። ይህ የሁቲዎች የድፍረት እርምጃ በሳዑዲ አረቢያ ላይ የፈጠረው የደህንነት ስጋት፣ የቀጠናውን ኃያላን አዲስ ወታደራዊ ስምሪት እንዲያደርጉ አስገድዷቸዋል።
ጉዳዩን ተከትሎ በተጠራ አስቸኳይ ስብሰባ፣ ቱርክ እና ፓኪስታን የሳዑዲ አረቢያን ደህንነት ለማጠናከር እና አጋርነታቸውን ለማሳየት ወታደሮቻቸውን በፍጥነት ለማሰማራት ከስምምነት ላይ ደርሰዋል። ይህ የቱርክ እና ፓኪስታን ፈጣን ወታደራዊ ምላሽ፣ የየመኑ ግጭት ከውስጣዊ የእርስ በርስ ጦርነት አልፎ ሰፊ ቀጠናዊ እና ዓለም አቀፋዊ መልክ እየያዘ መምጣቱን ቁልጭ አድርጎ ያሳያል።
_____
🗣️ ይህ እየተወሳሰበ የመጣው የቀጠናው ውጥረት እና የኃያላኑ ጣልቃ ገብነት ወዴት ያመራ ይሆን? ሀሳባችሁን ኮመንት ላይ አጋሩን!

የታይዋን ፕሬዚዳንትን ልጅ ለመሰለል የተላከችው አሜሪካዊት ሰላይ ተያዘች
ነዋሪነቷ በካሊፎርኒያ የሆነችው የ 34 ዓመቷ ሴት ከቻይና ባለሥልጣናት መመሪያ ተቀብላ የታይዋን ፕሬዚዳንት ቺንግ-ቴ ልጅና ቤተሰቡን ለመሰለል ሞክራለች በሚል በኤፍቢአይ መያዟ ተሰምቷል; ዋንዪንግ “ሄዘር” ዣንግ የተባለችው ሴት የፕሬዚዳንቱን የቅርብ ዘመድ ቤት፣ መኪናና የቤተሰቡን ምስሎች እንድትሰበስብ መመሪያ እንደተሰጣት የአሜሪካ ባለሥልጣናት ገልጸዋል።
የፌዴራል ክስ ሰነድ እንደሚያሳየው ዣንግ በ2025 ከሌላ ሰው ጋር ወደ ሲያትል በመጓዝ የታይዋን ፕሬዚዳንት የቅርብ ዘመድ ቤት አካባቢ በኪራይ መኪና ውስጥ ተደብቀው ይጠባበቁ ነበር። ቤተሰቡ ወደ ቤቱ ሲደርስም ሁለቱ ስልኮቻቸውን አውጥተው ፎቶና ቪዲዮ ሲያነሱ በጎረቤት የደህንነት ካሜራ ተመዝግቧል።
የአሜሪካ ተመራማሪዎች የቤተሰቡ መኖሪያ፣ መኪናና ሌሎች መረጃዎች ቻይና በታይዋን ላይ በምታደርገው ጫና ሊጠቀምባቸው እንደምትችል ገልጸዋል። ዣንግ ለቻይና መንግሥት እየሠራች መሆኗን ለአሜሪካ መንግሥት ሳታሳውቅ መቅረቷም የተጠቀሰ ሲሆን፣ ክሱን እስካሁን መርምራ የሚያስተባብል የሕግ ጠበቃ መኖሩ አልታወቀም።
የታይዋን ፕሬዚዳንታዊ ጽሕፈት ቤት በበኩሉ ጉዳዩን “ድንበር ተሻጋሪ ጫና” በማለት አውግዟል። ቻይና ታይዋንን የራሷ ግዛት አካል እንደሆነች ስትገልጽ፣ ታይዋን ግን ራሷን በራሷ የምታስተዳድር ዴሞክራሲያዊ አገር ናት። ዣንግ በሎስ አንጀለስ የፌዴራል ፍርድ ቤት ቀርባ በክሱ ላይ የመጀመሪያ ችሎት እንደምታደርግ ተገልጿል።
በሚኪያስ ጸሐዬ
#ዳጉ_ጆርናል

" መረር ያለ እርምጃ እንወስዳለን "
ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሙስናን ፣ ሌብነትን ፣ የዘመድ አሰራርን እንዲሁም ወገንተኝነትን ለማስወገድ መንግስታቸው መረር ያለ እርምጃ እንደሚወስድ አሳውቀዋል።
በሌላ በኩል ከበጀት ጋር በተያያዘ " ጠንካራ ቁጥጥር እና ክትትል የሚደረግበት የበጀት አካሄድን እንከተላለን " ሲሉም አሳውቀዋል።
https://www.youtube.com/li...
መስከረም 25 ቀን 2019 ዓ/ም
@tikvahethiopia 🕊 በኢትዮጵያ የሰላም ሁኔታን የበለጠ ለማጽናት መንግስታቸው " የውይይት እና የይቅርታ መንገድ " እንደሚከተል ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገልጸዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባሰሙት ንግግር " በጫካ ያላችሁ ወገኖች ወደ ሰላማዊ መንገድ ኑ ፤ ያኮረፋችሁ ወገኖችም የይቅርታ መንፈስን ተላብሳችሁ በሀገር ግንባታ ተሳተፉ " ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል። በሌላ በኩል፤ በሀገሪቱ የተጠናከረ የጸጥታ እና የደህንነት ዝግጅትና…

🕊
በኢትዮጵያ የሰላም ሁኔታን የበለጠ ለማጽናት መንግስታቸው " የውይይት እና የይቅርታ መንገድ " እንደሚከተል ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገልጸዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባሰሙት ንግግር " በጫካ ያላችሁ ወገኖች ወደ ሰላማዊ መንገድ ኑ ፤ ያኮረፋችሁ ወገኖችም የይቅርታ መንፈስን ተላብሳችሁ በሀገር ግንባታ ተሳተፉ " ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።
በሌላ በኩል፤ በሀገሪቱ የተጠናከረ የጸጥታ እና የደህንነት ዝግጅትና ክትትል እንዲሁም ስምሪት እንደሚኖር አሳውቀዋል።
https://www.youtube.com/li...
መስከረም 25 ቀን 2019 ዓ/ም
@tikvahethiopia " ... በቀጠናው ጉዳይ ላይ የምትወስን መሆኗን በሰዎች ችሮታ ሳይሆን በጉልበቷ ታረጋግጣለች ! " - ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድና በቀጠናው ያላትን ሚና ማንም በሚሰጣት ችሮታ ሳይሆን በገዛ አቅሟና ጉልበቷ እንደምታረጋግጥ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ " ኢትዮጵያ በቀጠናው አንከር (መሰረት) ሀገር ብቻ ሳትሆን፣ በቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ…

በቀጣይ የህገመንግስት ማሻሻያ እንደሚኖር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ(ዶ/ር) አስታወቁ
የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ 7ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 1ኛ ዓመት የስራ ዘመን የምክር ቤቱ መመስረቻ 1ኛ መደበኛ ስብሰባውን በዛሬው ዕለት አካሂዷል።
በዚህ ወቅት ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር በመሆኑ ተሹመዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ (ዶ/ር) ለፓርላማው ባደረጉት ንግግር በሀገራዊ ምክክሩ ምክረ ሐሳቦች መሠረት የሕገመንግስት ማሻሻያ እንደሚደረግ አሳውቀዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚህ ወቅት ባደረጉት ንግግር ኢትዮጵያ የጠላቶቿን እኩይ ተግባርና የሚደቀኑባትን ተግዳሮቶች በብቃት ለመመከት አስፈላጊውን ዝግጅት ማድረጓን ገልጸዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በንግግራቸው በምርጫው ለተሳተፉ 54 ሚሊዮን ዜጎች ምስጋና ያቀረቡ ሲሆን ሂደቱም በብዙ መልኩ ትርጉም ያለው እንደነበር አስታውሰዋል።
"ወርቅ በእሳት እንደሚፈተነው ሁሉ የዴሞክራሲ ባህልም የሚፈተነው በምርጫ ወቅት ነው" ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሕዝቡ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ሆኖ ሕልውናውን ለማጽናት ድምፅ መስጠቱ የዴሞክራሲያዊ ባህላችን መሰረት እየጠነከረ መምጣቱን በግልጽ ያሳየ ነው ብለዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ አክለውም በማንኛውም ምርጫ የፖለቲካ ፓርቲዎች አሸናፊና ተሸናፊ ሊሆኑ ቢችሉም "ኢትዮጵያ ግን አሸናፊ እንጂ ተሸናፊ ዜጋ የላትም" ሲሉ አጽንኦት ሰጥተዋል።
ሀገራዊ ፣ ቀጣናዊ እና ዓለም አቀፋዊ ሁኔታዎች በፍጥነት እየተለዋወጡና ኢ ተገማች እየሆኑ መምጣታቸውን የጠቆሙት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለዚህም አስቀድሞ መዘጋጀት እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ በታሪክ አጋጣሚዎች ቀደም ሲል ዝግጁ ባለመሆኗ ከፍተኛ ዋጋ መክፈሏን አስታውሰው አሁን ግን ካለፉት ስህተቶቿ በመማር ተግዳሮቶችን ለመመከት የሚያስችል ዝግጅት ማድረጓን ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ በቀጠናው ላይ ውሳኔ ሰጪነቷን በጉልበቷ የምታረጋግጥ መሆኗንና ይህንንም ያለማንም እገዛ እንደምታከናውን በመግለጽ የተያዘውን መዳረሻ ለማሳካት በሚገጥሙ እንቅፋቶች ሳትወድቅ ጉዞዋን እንደምትቀጥል ጠቁመዋል።
በውጭ ተጽዕኖ ስር ሳይወድቁ በሀገር በቀል ጥበብ ለመመራት የሚከለክል ነገር እንደሌለ የጠቆሙት ጠ/ሚ ዐቢይ ሀገር ለዘመናት በመጤ ስልትና ባህል ማለፏንና ተጽዕኖዎችን ለመቆጣጠር አቋራጭ መንገዶች ሲወሰዱ መቆየታቸውን ተናግረዋል። ሆኖም ኢትዮጵያዊነት ሊቀጥል የቻለው በመደመር እሳቤ እንደነበርና አሁንም የሚያዋጣው መንገድ ይኸው መሆኑን ተናግረዋል።
አክለውም ለነገ የምንሻገርበት የታሪክ አተያይ መስተካከሉን ጠቅሰው የሀገሪቱ የኢኮኖሚ ስርዓት ከአንድ ዘርፍ ጥገኝነት ወጥቶ የብዝኃ-ዘርፍ ማቀናጀትና መተግበር ላይ ያተኮረ እንዲሆን መደረጉን ገልጸዋል።
ጠንካራ ቁጥጥርና ክትትል ያለበት የበጀት አካሄድን እንደሚከተሉም ያነሱ ሲሆን ለህብረ ብሔራዊ ሀገረ-መንግሥት ግንባታ ወሳኝ የሆነው የውል ትርክት ተገቢውን ትኩረት ያገኛል ብለዋል።
ምርታማነት ባህልና ሥርዓትም እንዲሆን የሚሰራ ሲሆን የሰላም ሁኔታዎችን የበለጠ ለማፅናት የውይይትንና የይቅርታን መንገድ እንደሚከተሉም ገልፀዋል።
በሌላ በኩል የተጠናከረ የፀጥታና የደህንነት ዝግጁነት፣ ክትትል እንዲሁም ስምሪት ይኖረናል ሲሉ ተናግረዋል።
ሙስናን፣ ሌብነትን፣ የዘመድ አሰራርንና ወገንተኝነትን ለማስወገድ መንግሥት መረር ያሉ እርምጃዎችን እንደሚወስድም አስታውቀዋል።
በስፍራሽ ደመላሽ

ኢትዮጵያ በዓባይ እና በቀይ ባሕር ላይ ያላትን ስትራቴጂካዊ ፍላጎት የሚያሳንስ ጥረት እንደማይሳካ ገለጸች
የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በቀጣናዊ የፖለቲካ እና የደህንነት እንቅስቃሴዎች ላይ ዛሬ መስከረም 25 ቀን 2019 ዓ/ም ባወጣው መግለጫ ሀገሪቱ በዓባይ ወንዝ እና በቀይ ባሕር አካባቢ ያላትን መልክዓ ምድራዊ እና ታሪካዊ እውነታዎች በማንኛውም ኃይል ወይም በውጭ ተላላኪ አካላት ሊቀየሩ እንደማይችሉ አስታውቋል።
ሚኒስቴሩ የቀጣናው ሀገራት ከአሸናፊና ተሸናፊ አስተሳሰብ በመውጣት በጋራ ተጠቃሚነት ላይ የተመሰረተ ትብብር እንዲያደርጉም ጥሪ አቅርቧል።
ሚኒስቴሩ ይፋ ባደረገው መግለጫ የኢትዮጵያ ቅርብ ድንበር ከቀይ ባሕር ዳርቻ የሚገኘው በ48 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ብቻ መሆኑን በማስታወስ በጊዜ ሂደት የፖለቲካ ድንበሮች ቢቀያየሩም ከቀይ ባሕር ጋር ያላት ጥብቅ መልክዓ ምድራዊና ታሪካዊ ትስስር አሁንም የጸና መሆኑን ገልጿል።
በመሆኑም በቀጣናው የባሕር ደህንነትና ስትራቴጂካዊ መዋቅር ላይ በሚደረግ ማንኛውም ውይይት የኢትዮጵያን ሕጋዊ ጥቅም እና ዘላቂ ሚና ማገለል እንደማይቻል አስታውቋል።
ከ85 በመቶ በላይ የሚሆነውን የናይል ውኃ የምታመነጨው ኢትዮጵያ መሆኗን የገለጸው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በዓባይ ወንዝ አጠቃቀምና አስተዳደር ዙሪያ የሚደረጉ ማናቸውም ውይይቶች ይህን መሰረታዊ የተፈጥሮ እውነታ ያገናዘቡ መሆን እንዳለባቸው ጠቁሟል።
የውኃውን መነሻና የሀገሪቱን ድርሻ ያላገናዘበ አካሄድ ተቀባይነት እንደሌለውም አስታውቋል።
በፖለቲካዊ ዲስኩር ፣ በማስገደድ እርምጃዎች ወይም በተላላኪ ኃይሎች አማካይነት የሚሰነዘሩ ጥቃቶችና ሀገርን የማተራመስ ሙከራዎች ኢትዮጵያ በቀጣናው ያላትን ሚና እና ሕጋዊ ጥቅም ከቶውንም ሊያሳንሱት እንደማይችሉ የጠቆመው መግለጫው ሀገሪቱ ሉዓላዊነቷን ፣ የግዛት አንድነቷን እና ብሔራዊ ጥቅሟን ለማስከበር በማንኛውም ጊዜ ዝግጁ መሆኗን አስታውቋል።
የቀጠናው ተዋናዮች የጋራ ፈተናዎችን በኃይልና በግጭት ከመፍታት ይልቅ በገንቢ ውይይት፣ በአጋርነትና በመልካም ጉርብትና መርሆች ላይ ተመሥርተው በጋራ እንዲሰሩ ጥሪ አቅርቧል።

(ዘ-ሐበሻ ዜና) የግብፅ፣ የኤርትራ፣ የሶማሊያ እና የሱዳን መሪዎች በግብፇ ኤል-አላሜይን ከተማ ያልተጠበቀ የአራትዮሽ ጉባኤ አካሂደዋል። መሪዎቹ በቀጠናው እየተባባሰ ለመጣው ግጭት፣ በተለይም በሱዳን እና በሰሜን ኢትዮጵያ ለሚያገረሸው ጦርነት ሰላማዊ መፍትሄ እንዲፈለግ ጥሪ ቢያቀርቡም፤ ከስብሰባው በኋላ ያወጡት የጋራ መግለጫ ግን በቀጥታ የኢትዮጵያን ብሔራዊ የውጭ ፖሊሲዎች የሚሞግት ሆኖ ተገኝቷል።
የጋራ መግለጫው "የቀይ ባህር አስተዳደር የባህር ዳርቻ ሀገራት ብቻ መብት ነው" በማለት የኢትዮጵያን የባህር በር ፍላጎት በግልፅ ሲቃወም፤ በናይል ወንዝ ላይ "የአንድ-ወገን እርምጃ የታችኛውን ተፋሰስ ሀገራት ይጎዳል" በማለት የታላቁን ህዳሴ ግድብን አጀንዳ በድጋሚ ኮንኗል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነቱ ዳግም አገርሽቶ የፌደራል መንግስት ኃይሎች የትግራይ ክልል ዋና ከተማ የሆነችውን መቀሌን ዳግም መቆጣጠራቸው ተዘግቧል። አዲስ አበባ ጎረቤቶቿን (ግብፅ፣ ሱዳን እና ኤርትራን) አማፂያንን በመደገፍ ብትከስምም፣ ሶስቱም ሀገራት ክሱን አስተባብለዋል። ይባስ ብሎ የኤርትራው የማስታወቂያ ሚኒስትር፣ "ኢትዮጵያ ኤርትራን ለማጥቃት የውሸት ሰበብ እየፈለገች ነው" ሲሉ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ከባድ ክስ ሰንዝረዋል።
የፖለቲካ ተንታኞች ይህንን ክስተት ሲያብራሩ፣ ግብፅ የኢትዮጵያን ታሪካዊ ጎረቤቶች በአንድ በማሰባሰብ ጠንካራ የዲፕሎማሲያዊ እና የደህንነት ከበባ እየፈጠረች መሆኑን ያሳያል ይላሉ። ኢትዮጵያ በአንድ ጊዜ ከምስራቅ በሶማሊያ፣ ከምዕራብ በሱዳን፣ እና ከሰሜን በኤርትራ በኩል በከፍተኛ ጫና ውስጥ ወድቃለች። አዲስ አበባ የውስጥ ጦርነቷን በአጭሩ ቋጭታ ይህንን የተናበበ የውጭ ጥምረት መቋቋም ካልቻለች፣ የቀንድ አፍሪካ ጂኦ-ፖለቲካ ወደ ባሰ የደህንነት ስጋት ሊያመራ እንደሚችል ተገምቷል።
_____
🗣️ ውድ የዘ-ሐበሻ ቤተሰቦች... እናንተስ ምን ታስባላችሁ?
ይህ አዲሱ በግብፅ አቀናባሪነት የተመሰረተው የአራቱ ሀገራት ጥምረት በኢትዮጵያ ላይ ምን ዓይነት ተፅዕኖ ያመጣል? የውስጥ አንድነታችንንስ ለማስጠበቅ ምን መደረግ አለበት? ሀሳባችሁን ኮመንት ላይ አጋሩን!

“ሕልሜ አውሮፕላኑን ቴል አቪቭ ላይ መከስከስ ነበር!”
የፍላይዱባይ ረዳት አብራሪ ሃማም አል-ሃማሚ ወደ እስራኤል የሚበር አውሮፕላን ለመጥለፍና ለመከስከስ አስቀድሞ በጥንቃቄ ያቀደ መሆኑን በምርመራ ወቅት ማመኑን የጄሩሳሌም ፖስት ዘገባ አመልክቷል።
የ30 ዓመቱ ኦማናዊ ረዳት አብራሪ ወደ ቴል አቪቭ የሚበሩ አየር መንገድ ኩባንያዎችን አስቀድሞ በማጥናት ፍላይዱባይን እንደመረጠ ገልጾ፣ "ትልቁ ሕልሜ አውሮፕላኑን በቤን ጉሪዮን አውሮፕላን ማረፊያ ወይም በቴል አቪቭ ረጅም ሕንፃዎች ላይ መከስከስ ነበር" ብሏል።
ለዚሁ ጥቃት መረጃ ለመሰብሰብም ቀደም ብሎ በሥራ አጋጣሚ ወደ እስራኤል ተደጋጋሚ ጉዞ ያደርግ ነበር።
የጥቃት ዕቅዱ የጦር ጄቶች ደርሰው ሳይከለክሉት በፍጥነት የሚፈጸም ነበር።
ረዳት አብራሪው ዋና አብራሪውን በምሳር መትቶ እጁን ከባድ አደጋ ካደረሰበት በኋላ፣ የአውሮፕላኑን ሞተሮች በማጥፋት ለመከስከስ ሞክሯል።
ሆኖም ዋና አብራሪው ከባድ ጉዳት ቢደርስበትም ከተሳፋሪዎች ጋር በመተባበር ረዳት አብራሪውን በቁጥጥር ስር በማዋል አውሮፕላኑን በሳዑዲ ዓረቢያ በሰላም ማሳረፍ ችለዋል።
የእስራኤል ባለስልጣናት ግለሰቡ ጥቃቱን የፈጸመው በራሱ ተነሳሽነት እንጂ ከሽብር ቡድን ታዝዞ እንዳልሆነ ገልጸዋል።
አል-ሃማሚ ቀደም ሲል በኦማን አየር መንገድ ይሰራ የነበረ ቢሆንም በአክራሪነት አስተሳሰቡ ምክንያት ከስራ የተባረረ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት የአውስትራሊያ ፖሊስና የደህንነት ተቋማት ግለሰቡ በአውስትራሊያ በነበረበት ወቅት እንዴት ወደ ፅንፈኝነት እንደገባ መረጃዎችን በማሰባሰብ ሰፊ ምርመራ እያደረጉበት ይገኛሉ።

8 days ago
"ኢራን ኤምሬትስን መቆጣጠር አለባት"
የኢራን የፓርላማ አባል ሁሴን-አሊ ሃጂ-ደሊጋኒ ኢራን የተባበሩት አረብ ኤምሬትስን እንድትቆጣጠር (እንድትወር) ጥሪ አቀረቡ።
የምክር ቤት አባሉ የኢራን ኃይሎች በዚያ እንዲሰፍሩ የጠየቁት በኢራን ላይ የሚሰነዘሩ ጥቃቶችን ለመከላከልና ከሆርሙዝ የባህር ወሽመጥ ጋር ተያይዘው የተነሱ የደህንነት ስጋቶችን ለመፍታት ነው ሲሉ ተናግረዋል።

(ዘ-ሐበሻ ዜና) የፌደራል መንግስት መቀሌን መቆጣጠሩን ተከትሎ የትግራይ ኃይሎች ወደ ኤርትራ ድንበር እያፈገፈጉ መሆናቸውንና ይህም ጦርነቱን ወደ አዲስ እና አደገኛ የቀጥታ የኢትዮ-ኤርትራ ግጭት ሊያሸጋግረው እንደሚችል አቶ ጃዋር መሐመድ ባወጡት አዲስ የፖለቲካ ትንታኔ አስጠነቀቁ።
አቶ ጃዋር ባወጡት ሰፊ ትንታኔ እንዳብራሩት የህወሓት አመራሮች እና የዕዝ ሰንሰለቱ ከመደበኛ የከተማ ውጊያ ወደ ተንቀሳቃሽ (ደፈጣ) ውጊያ ለመሸጋገር በማሰብ ወደ ኤርትራ ድንበር አካባቢ ማፈግፈጋቸውን ጠቁመዋል። ይህ የህወሓት እንቅስቃሴ በአዲስ አበባ እና በአስመራ መካከል ያለው ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ሙሉ በሙሉ በተቋረጠበት በአሁኑ ወቅት የሁለቱን አገራት መሪዎች ከባድ የፖለቲካ እና ወታደራዊ ፈተና ውስጥ እንደከተታቸው ትንታኔው ያብራራል።
በጥናቱ መሰረት የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ሁለት የተጣረሱ ምርጫዎች ተደቅነውባቸዋል። አንደኛው የህወሓት ኃይሎች ወደ ግዛታቸው ገብተው እንዲደራጁ መፍቀድ ሲሆን፣ ይህ እርምጃ በኢትዮጵያ መንግስት ላይ የሚፈልጉትን የተኪ ጦርነት (Proxy war) ግፊት ለማስቀጠል ይረዳቸዋል። ይሁን እንጂ ይህን ማድረጋቸው፣ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ድንበር ጥሰው ወደ ኤርትራ እንዲገቡ ህጋዊ እና የደህንነት ሽፋን ሊሰጣቸው ስለሚችል አስመራን በቀጥታ ወደ ጦርነት ያስገባታል።
በተመሳሳይ የኢትዮጵያ መንግስትም ከባድ የውሳኔ ማዕበል ውስጥ እንደሚገኝ አቶ ጃዋር ጠቁመዋል። የፌደራል መንግስቱ የህወሓት ኃይሎች ጊዜ አግኝተው ዳግም እንዳይደራጁ ድንበር ጥሶ ፈጣን እርምጃ መውሰድን ከመረጠ፣ ከኤርትራ መደበኛ ጦር ጋር በቀጥታ ጦርነት ውስጥ ከመግባቱም በላይ ዓለም አቀፉን ማህበረሰብ ሊያስቆጣ ይችላል።
በአንፃሩ እርምጃ ሳይወስድ መጠበቁ፣ ህወሓት ጊዜ አግኝቶ ከውጭ አጋሮቹ (በተለይም በድንበር እና በጂኦ-ፖለቲካ ውዝግብ ውስጥ ካሉት ሱዳን እና ግብፅ) ጋር በመቀናጀት ይበልጥ አደገኛ ሀይል ሆኖ እንዲወጣ እድል ሊሰጠው እንደሚችል ተንትነዋል።
ሲያጠቃልልም አቶ ጃዋር የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ተጨማሪ ክፍለ ጦሮችን እና ተንቀሳቃሽ ድልድዮችን ወደ ሰሜን ዕዝ እያንቀሳቀሰ መሆኑን ጠቁመው፤ አስቸኳይ ዲፕሎማሲያዊ መፍትሄ ተፈልጎ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ እና ፕሬዚዳንት ኢሳያስ ወደ ድርድር ጠረጴዛ ካልመጡ በቀር፣ ግጭቱ የትግራይን ድንበር አልፎ ወደ ኤርትራ ግዛት የሚሸጋገርበት እጅግ አደገኛ ምዕራፍ ላይ መድረሱን አጽንኦት ሰጥተዋል።

9 days ago
ቦይንግ 737 MAX 10 ምን ገጠመው?
#ethiopia | ቦይንግ አዲስ የሶፍትዌር ችግር ቢገጥመውም FAA በረራዎች እንዲቀጥሉ ፈቀደ።
የአሜሪካው የፌዴራል ሲቪል አቪዬሽን አስተዳደር (FAA) በቦይንግ 737 MAX የበረራ ኮምፒውተሮች ላይ የተገኘው የሶፍትዌር ችግር ምንም አይነት የደህንነት ስጋት እንደማያመጣ ገለጸ።
ይህ ውሳኔ ለዓመታት የፈቃድ መዘግየት ሲገጥመው ለቆየውና የ MAX ተቋም ትልቁ አውሮፕላን ለሆነው MAX 10 ይፋዊ ማረጋገጫ ለማግኘት መንገድ የከፈተ ሆኗል።
ተመሳሳይ ሶፍትዌር ለሚጠቀመው MAX 7 ተጠቃሚ አየር መንገዶችም እፎይታን ሰጥቷል ተብሏል።
አስተዳደሩ አብራሪዎች የአውሮፕላኑን ሙሉ ተቆጣጣሪነት የመያዝ ብቃት ስላላቸው እና የኮክፒት መረጃዎች ግልጽ በመሆናቸው ሶፍትዌሩ የበረራ አደጋ አያደርስም ብሏል።
ቦይንግ ለአብራሪዎች የማብራሪያ መመሪያ የሚያወጣ ሲሆን FAA ደግሞ ለአለም አቀፍ አቪዬሽን ተቆጣጣሪዎች ማብራሪያ እንደሚልክ ገልጻል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#ethiopia #getutemesgen #aviationnews #boeing #boeing737max

የኢሬቻ ሆራ ፊንፊኔ በዓል በሠላም መከበሩን የአዲስ አበባ የተቀናጀ የጸጥታ ግብረ ኃይል አስታወቀ
በአዲስ አበባ ከተማ የተከበረው የኢሬቻ ሆራ ፊንፊኔ በዓል የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ ልዩ ልዩ ብሔር ብሔረሰቦች፣ የውጭ ሀገር ዜጎችና ቱሪስቶች እንዲሁም በርካታ ታዳሚዎች በተገኙበት "ኢሬቻ ለብሔራዊ መግባባት " በሚል መሪ ቃል በደመቀና እሴቱን በጠበቀ መንገድ በሠላም መከበሩን የአዲስ አበባ የተቀናጀ የፀጥታ ግብረ ኃይል አስታወቀ፡፡
በዓሉ ባህላዊ ይዘቱን ጠብቆ በድምቀትና ፍፁም ሠላማዊ በሆነ መንገድ እንዲከበር አባገዳዎች፣ አደ ሲንቄዎች፣ ፎሌዎች፣ የመድናችን ነዋሪዎች እንዲሁም በየእርከኑ የሚገኙ የአስተዳደር አካላት ላደረጉት አስተዋፅኦ እና ኃላፊነታቸውን በአግባቡ ለተወጡ የፀጥታና የደህንነት ተቋማት አመራሮችና አባላት የፀጥታ ግብረ ኃይሉ ምስጋናውን አቅርቧል፡፡
በነገው ዕለትም በቢሾፍቱ ከተማ የሚከበረው የሆራ አርሰዴ የኢሬቻ በዓል በሠላም እንዲጠናቀቅ የፀጥታ ተቋማት ዝግጅታቸውን አጠናቀው ወደ ተግባር የገቡ ስለሆነ ህዝቡ የተለመደ ትብብሩን አጠናክሮ እንዲቀጥልም የአዲስ አበባ የተቀናጀ የጸጥታ ግብረ ኃይል አስታውቋል፡፡

10 days ago
(ዘ-ሐበሻ ዜና) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር እንዳሻው ጣሰው ከኃላፊነታቸው ሊነሱ መሆኑን እና በምትካቸው የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስትር ዴኤታው ዶ/ር የትምጌታ አሥራት እንደሚሾሙ የዘ-ሐበሻ ምንጮች ጠቁመዋል። ይህ የሹመት ለውጥ ክልሉ ከተመሰረተበት ከነሐሴ 2015 ዓ.ም ጀምሮ የታየውን የፖለቲካ አለመረጋጋት እና ተቃውሞ ለማርገብ ማዕከላዊ መንግስት የወሰደው የስትራቴጂ ለውጥ መሆኑ ይነገራል።
ይህ የስልጣን ሽግግር የአንድ ግለሰብ መነሳት እና መሾም ብቻ ሳይሆን መንግስት ለአዲሱ ክልል የሚሰጠውን የአመራር ዘይቤ ከ"ጸጥታ እና ደህንነት" ወደ "ቴክኖክራት እና ልማት" አቅጣጫ ለመቀየር ያደረገው ፖለቲካዊ ስሌት መሆኑን የሁለቱ አመራሮች የልምድ ዳራ በግልጽ ያሳያል።
የሁለቱ አመራሮች የልምድ እና የአመራር ዘይቤ ንጽጽር ሲታይ ትልቅ የስትራቴጂ ልዩነት ጎልቶ ይታያል። ተሰናባቹ ዶ/ር እንዳሻው ጣሰው የጸጥታ፣ የደህንነት እና የፖሊስ አመራር ዳራ ያላቸው ናቸው። ቀደም ሲል የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል እና የብሔራዊ መረጃና ደህንነት (NISS) ከፍተኛ አመራር በመሆን ያገለገሉት ዶ/ር እንዳሻው፣ ጥብቅ የጸጥታ ቁጥጥር እና የህግ ማስከበር ላይ ያተኮረ የአመራር ዘይቤን ይከተላሉ። ይሁን እንጂ የተለያዩ ብሄሮች የተጠቃለሉበትን ይህን ክልል በጸጥታ መዋቅር ብቻ ለማስተዳደር መሞከራቸው በተለይም ከጉራጌ እና ሀዲያ ዞኖች የሚነሱ የራስ-አስተዳደር ጥያቄዎችን እና ተቃውሞዎችን በቀላሉ ለማስተናገድ ፈተና ሆኖባቸው ቆይቷል።
በአንጻሩ ተተኪው (ተጠባቂው) ዶ/ር የትምጌታ አሥራት የኢኮኖሚክስ፣ የመሠረተ-ልማት እና የመንገድ ባለሙያ (ቴክኖክራት) ናቸው። እርሳቸው በአሁን ሰዓት የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስትር ዴኤታ ሲሆኑ፣ ቀደም ሲል ደግሞ የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር ሆነው ሰርተዋል። የዶ/ር የትምጌታ ዋና የአመራር ዘይቤ የፕሮጀክት አስተዳደር፣ የተቀናጀ የኮሪደር ልማት እና የኢኮኖሚ ትንተና ላይ ያተኮረ ነው። በዚህም መሰረት አዲሱ ሚናቸው በመሰረተ-ልማት እና በኢኮኖሚያዊ ፕሮጀክቶች ላይ ትኩረት በማድረግ የክልሉን ፖለቲካዊ ውጥረት ማርገብ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።
የዶ/ር የትምጌታ አሥራት ሹመት የሚያስተላልፈው ግልጽ መልዕክት፤ ማዕከላዊ መንግስት በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ያለውን የፖለቲካ ውጥረት በመሰረተ-ልማት፣ በመንገድ ግንባታ እና በኢኮኖሚያዊ ፕሮጀክቶች ለማብረድ መወሰኑን ነው። ህዝቡ የሚያነሳቸውን የፖለቲካ እና የራስ-አስተዳደር ጥያቄዎች፣ በመሰረተ ልማት ዝርጋታ እና በከተማ ልማት ስራዎች ለመመለስ የታለመ ስልታዊ እርምጃ መሆኑን የፖለቲካ ታዛቢዎች ይገልጻሉ።

የተማሪዎች ተቃውሞ ወደ ሁከት በመቀየሩ ምክኒያት በመቶዎች የሚቆጠሩ የፈረንሳይ ትምህርት ቤቶች ተዘጉ
ባለፈው ሳምንት በፓሪስ ውስጥ በሚገኙ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የተጀመረው የተማሪዎች ተቃውሞ ወደ ፈረንሳይ በመስፋፋቱ እና እየጨመረ በሄደው ሁከት ምክኒያት፣ 400 የሚጠጉ የፈረንሳይ ትምህርት ቤቶች ተዘግተው የቆዩ ሲሆን አሁንም በዕለተ ዓርብ ዝግ ሆነው እንደሚቀጥሉ ተገልጿል።
ተማሪዎቹ ተቃውሟቸውን እያሰሙ የሚገኙት የመምህራን እጥረት እና የትምህርት ቤት ህንፃዎች መበላሸትን ጨምሮ በተለያዩ ቅሬታዎች ሳቢያ ነው። መንግስት ግን እንቅስቃሴውን የጀመሩት አስተማሪዎቹ ሳይሆኑ ፅንፈኛ ፖለቲከኞች ናቸው ሲል ከሷል።
ለጠቅላይ ሚኒስትር ሴባስቲያን ሌኮርኑ ቅርብ የሆኑ አካላት እንደገለጹት፣ ሀሙስ ዕለት በተካሄደው የአስቸኳይ ጊዜ ስብሰባ ላይ የደህንነት መስሪያ ቤቶች የተቃውሞ እንቅስቃሴው የፍራንስ አንቦውድ አባላትን ጨምሮ በፅንፈኛ ፖለቲከኞች አነሳሽነት የተጀመረ መሆኑን ገልጸዋል።
ሰላማዊ ነጋሲ

የዛሬ ምሽት ዜና መፅሔት ጉዳዮች
👉 የኢሬቻን በዓል ስናከብር እንደ እሴቱ አንድነትን አጥብቀን፣ እጃችንን ለሰላምና ለዕርቅ ዘርግተን፣ ቀልባችንን ወደ ይቅርታ መልሰን ሊሆን ይገባል ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ባስተላለፉት መልዕክት፣ ሙሉውን አዘጋጅተነዋል ትሰሙታላችሁ፡፡
👉 በአዲስ አበባ የተለያዩ አቅጣጫዎች የበዓሉ ታዳሚዎች እየገቡ ነው፣፡ ከቦታዎቹ ላይ በቀጥታ የምናደርሳችሁ መረጃ ይኖረናል፡፡
👉 "ኢሬቻ ለሀገራዊ መግባባት" በሚል መሪ ሐሳብ 8ኛው የኢሬቻ ፎረም ዛሬ በአዲስ አበባ ተካሒዷል ።ምን ምን ጉዳዮች ተነሱ? በዝርዝር ያዘጋጀነው ጉዳይ አለ፡፡
👉ጀርመን የመከላከያ አቅሟን በፍጥነት እያሳደገች ነው ። ይህ ለውጥ በአውሮፓ የደህንነት ሁኔታ፣ በሩሲያ–ዩክሬን ጦርነት እና በአሜሪካ የወደፊት የአውሮፓ ተሳትፎ ላይ በርሊን ያላት ስጋት ጋር ይያያዛል። ታዲያ ጀርመንን ወደዚህ አቅጣጫ የገፋት ምንድን ነው? በትንታኔ ይዘነዋል፡፡
👉ስፖርት - አዳዲስ መረጃዎች ተዘጋጅተዋል ።
የዕለቱ አብይ ርእሰ ጉዳዮች በዝርዝር እና በትንታኔ ።
የዜና ክፍል ጋዜጠኞች እነዚህን ጨምሮ ሌሎች ዘገባዎችን አካተው በፋና የምሽቱ ዜና መፅሔት ሊያስደምጧችሁ ዝግጁ ናቸው ።
ጌታቸው አለሙ ይጠብቃችኋል ።
በኤፍ ኤም 98.1 እና በተለያዩ ክልሎች በሚገኙ ኤፍ ኤሞቻችን እንዲሁም በwww.fanamc.com (http://www.fanamc.com/) በመላው ሃገሪቱና በዓለም ዙሪያ ስርጭታችንን መከታተል ትችላላችሁ።
ከምሽቱ 1 ሰዓት ይጠብቁን ።

ሉዓላዊነትን የመጠበቅና የማጽናት ውሳኔ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 22፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ በትናንትናው ዕለት በአስመራ የሚገኘውን ኤምባሲዋን ለመዝጋት ወስናለች። ከዚህም በተጨማሪ 10 የኤርትራ ዲፕሎማቶች በ48 ሰዓታት ውስጥ ከኢትዮጵያ እንዲወጡም ተወስኗል።
ከዚህ ጋር በተያያዘም አንድ የግብጽ ዲፕሎማት በተመሳሳይ 48 ሰዓት ውስጥ ኢትዮጵያን ለቅቆ እንዲወጣ ትዕዛዝ ተሰጥቶታል።
ውሳኔው የተላለፈው በድንገት አይደለም። ለረጅም ጊዜ በአብሮ መኖር፣ በጋራ ልማትና በሰላማዊ ቀጣና ላይ የነበረው ትዕግስት ሲዳከም፣ የደህንነት ስጋቱም ሲጨምር የተወሰደ ጠንካራና ሉዓላዊ ርምጃ ነው።
ዓለም አቀፍ ህግ በግልጽ ይደነግጋል፡ ማንኛውም ሀገር የሉዓላዊነት ጥያቄ ሲፈጠርበት ራሱን የመከላከል ሙሉ መብት አለው።
ይህ መርህ በተባበሩት መንግሥታት ቻርተር ውስጥ የተካተተ፣ በዓለም አቀፍ ልማድ የተረጋገጠና በሉዓላዊ እኩልነት ላይ የተመሠረተ ነው።
የውጭ ኃይሎች በሀገር ውስጥ የሚያደርጉት ጣልቃ ገብነት፣ የዲፕሎማቶችን ሽፋን በመጠቀም የሚፈጽሙት ተግባር፣ የቪየና የዲፕሎማሲ ስምምነትን የሚጥስ እንቅስቃሴ የሉዓላዊነት ጥቃት ነው።
ኢትዮጵያም ይህን ጥቃት የመከላከል ህጋዊና ሥነ-ምግባራዊ መብት አላት። መብቷንም በተግባር አሳይታለች።
ፈርኦኖቹ አንገቷን ቀና ያደረገች፣ በራሷ ፍላጎት የምትመራ ኢትዮጵያን ማየት አይፈልጉም። የዓባይን ውሃ ለሕዝቧ ልማት መጠቀም የጀመረችን፣ የባሕር በር ጥያቄዋን በሰላማዊና ህጋዊ መንገድ የምታስቀርብን፣ በቀጣናው ውስጥ የራሷን ድምፅ የምትሰማ ኢትዮጵያን እንደ ስጋት ይቆጥሯታል።
ሻዕቢያ ደግሞ በዚህ አጀንዳ ላይ በርካሽ ዋጋ የሚሠራ ተላላኪ ሆኖ ቆይቷል። በሀገር ውስጥ ያሉ ሽፍቶችን እያቀናጀ፣ የጦር መሣሪያና የሎጂስቲክስ ድጋፍ እያደረገ፣ የሰላምና የደህንነት መሠረቶችን ለማናጋት እየሠራ ያለ ኃይል ነው።
ይህ እርምጃ የጥላቻ ወይም የበቀል አይደለም። የራስን ሕልውና የማረጋገጥ፣ የሕዝብን ሰላም የመጠበቅና የቀጣናውን መረጋጋት የማረጋገጥ ኃላፊነት ነው።
ኢትዮጵያ ከኤርትራ ሕዝብ ጋር ያላት ታሪካዊ፣ ባህላዊና የሕዝብ-ለሕዝብ ግንኙነት አይረሳም። ነገር ግን መንግሥታዊ ጠብ አጫሪነትና መንግሥታዊ ሽብርተኝነት ከሰላማዊ ግንኙነት ጋር አይጣጣምም።
ፈርኦኖችና ተላላኪዎቻቸው ኢትዮጵያን እንደደከመች፣ እንደተበታተነችና እንደተናጋች ለማሳየት ይጥራሉ። ግን ታሪክ እንደሚመሰክረው፣ ኢትዮጵያ በተፈተነችበት ጊዜ ሁሉ አንገቷን አቀናች። ዛሬም እንደዚያው ነው። የሉዓላዊነቷን ጥበቃ በጠንካራ ቃልና በተግባር ታረጋግጣለች።
#ኢትዮጵያ #ትልቅሀገር #ትልቅሕዝብ #ታላቅርዕይ

Comments