12 hours ago
በበጀት አመት ከ118 ቢሊዮን ብር በላይ ማግኘት ተችሏል
#eghiopia | የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በተጠናቀቀው የ2018 በጀት አመት 118 ነጥብ 91 ቢሊየን ብር ገቢ ማግኘቱን ገለፀ።
የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ጌቱ ገረመው (ኢ/ር) በሰጡት መግለጫ ገቢው ከኢነርጂ ሽያጭ ከአዲስ ደንበኞች መስተንግዶ፣ ከማያገለግሉ ንብረቶች ሽያጭ እና ከሌሎች ልዩ ልዩ የገቢ ምንጮች መገኘቱን ተናግረዋል፡፡
በዚህ መሰረትም ከኢነርጂ ሽያጭ 75 ነጥብ 17 ቢሊየን ብር ለማግኘት ታቅዶ የውጭ ሀገር ሽያጭን ጨምሮ 76 ነጥብ 53 ቢሊየን ብር ገቢ መገኘቱን አስረድተዋል፡፡
በተጨማሪም ከአዲስ ደንበኞች መስተንግዶ 37 ነጥብ 74 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ 39 ነጥብ 23 ቢሊየን ብር መገኘቱን ነው የገለጹት፡፡
የማያገለግሉ ንብረቶችን በመሸጥ 275 ሚሊየን ብር የተገኘ ሲሆን ከልዩ ልዩ ገቢዎች ደግሞ 2 ነጥብ 68 ቢሊየን ብር መገኘቱን አስረድተዋል፡፡
የገቢ አፈጻጸሙ 103 በመቶ መሆኑንና ከ2017 በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ88 ነጥብ 4 በመቶ እድገት ማሳየቱን አመልክተዋል፡፡
የዲጂታል ክፍያ አማራጭ የሚጠቀሙ ደንበኞች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መጥቶ በአሁን ወቅት 95 ነጥብ 3 በመቶ መደረሱን ተናግረዋል፡፡
በተጨማሪም የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ቻርጅ ማድረጊያ ጣቢያዎች ገንብቶ ወደ ስራ በማስገባትና ስራ በማስጀመር 14 ነጥብ 25 ሚሊየን ብር ገቢ ተገኝቷል ብለዋል፡፡
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#ethiopia #getutemesgen #getunews #የኢትዮጵያ #ኤሌክትሪክአገልግሎት #ኤነርጂ #ገበያ #ትርፍ

1 month ago
የ5ቱ ዓመታት ገፆች፤ ታሪክ ተሰርቷል!
***************
የዘመናት ታሪክ ገፆች ሲገለጡ የአንድ ሀገር ዕጣ ፈንታ በአጭር ጊዜ ውስጥ ከስር መሰረቱ ተነቅንቆ አዲስ መልክ የሚይዝበት አጋጣሚ እጅግ ጥቂት ነው።
ላለፉት አምስት ዓመታት በኢትዮጵያ የተዘረጉትን የልማትና የለውጥ ገፆች ስናነብ፣ የተካሄደው ጉዞ "ለውጥ" ወይም "ሪፎርም" በሚሉ ቃላት ብቻ የሚገለፅ አይደለም።
ይልቁንም ከሪፎርም ባሻገር ወደ አብዮት የተጠጋ፣ የኢትዮጵያን አጠቃላይ ገፅታ የለወጠና ሥር ነቀል መዋቅራዊ ሽግግርን ያረጋገጠ ታላቅ ብሔራዊ ንቅናቄ ነው።
በዓለም የኢኮኖሚ ታሪክ ውስጥ፣ ጥቂት ሀገራት ብቻ ናቸው በፈጣን ጊዜ ውስጥ አስደናቂ የሚባል የዕድገት ዝላይ (Leapfrogging) ማሳየት የቻሉት።
ቻይና በሰላሳ ዓመታት ያመጣችው መዋቅራዊ ለውጥ፣ ደቡብ ኮሪያ በጄኔራል ፓርክ ቹንግ ሂ ቆራጥ መሪነት የተጓዘችው የኢንዱስትሪ ሽግግር፣ እንዲሁም ታይዋን ያስመዘገበችው የቴክኖሎጂ ስኬት ሁሌም በምሳሌነት ይነሳሉ።
ነገር ግን፣ ኢትዮጵያ በአምስት ዓመታት ውስጥ ብቻ እያስመዘገበች ያለው የለውጥ ፍጥነትና ስፋት እጅግ አስደናቂ ሆኖ እናገኘዋለን። በጠንካራና ቁርጠኛ አመራር እየተመራች፣ ኢትዮጵያ በሁሉም መስክ ወደ ታላቅነት የምታደርገው ሽግግር ከግምት በላይ የሆነ ጉዞ ነው።
ይህ ተአምራዊ የሚባል ዝላይ በገሃድ ከሚታይባቸው መስኮች አንዱ ግብርና ነው። ለዘመናት በልመናና በስንዴ ዕርዳታ ጥገኝነት ስትታወቅ የነበረችው ሀገር፣ በአምስት ዓመት ጊዜ ውስጥ የምግብ ሉዓላዊነቷን አረጋግጣ ወደ ስንዴ ላኪነት መሸጋገሯ እውነተኛ የኢኮኖሚ "ሉዓላዊነት" ማረጋገጫ ነው።
በተጠናከረ የኩታገጠም እና የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት፣ የስንዴ ምርት በ2017 በጀት ዓመት 280 ሚሊዮን ኩንታል መድረሱ የዚህ ፈጣን ስኬት ማሳያ ነው። ኢኮኖሚው ከአንድ ወጥ ጥገኝነት ወጥቶ ወደ ብዝሃ-ዘርፍ ልማት በማደግ ፈጣን የኢኮኖሚ ዕድገት ማስመዝገቡ በጥቂት ሀገራት ብቻ የሚሳካ ታላቅ ድል ነው።
የለውጡ ጅረት በግብርና ብቻ አልተገታም። በአረንጓዴ ኢኮኖሚው ዘርፍ፣ እስከ ኮፕ ጉባኤ ድረስ ከ65 ቢሊዮን በላይ ችግኞችን በመትከል በእስካሁኑ ጉዞ የሀገራችንን የደን ሽፋን ከ17 በመቶ ወደ 23.6 በመቶ ከፍ በማድረግ ኢትዮጵያ የዓለም የአየር ንብረት ለውጥ መከላከያ ተምሳሌት ሆናለች።
በውሃና ኃይል (ኤነርጂ) ሽግግር፣ ታላቁን የሕዳሴ ግድብን ጨምሮ በርካታ ፕሮጀክቶችን በማጠናቀቅ የኃይል ማመንጨት አቅምን ወደ 9,554 ሜጋ ዋት አሳድጋለች።
በተለይም የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን (EV) በመጠቀም የነዳጅ ጥገኝነትን መቀነስና የኢኮኖሚ ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ ሌላው የዘርፉ ስኬት ነው።
በከተማ ልማት ዘርፍም የኮሪደር ልማት ፕሮጀክቶች ከተሞቻችንን የውበት፣ የንፅህናና የሥልጣኔ ማዕከል አድርገዋቸዋል።
በኢንዱስትሪና በዲጂታል ዘርፍ፣ "ኢትዮጵያ ታምርት" ንቅናቄንና የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂን በመተግበር፣ እንዲሁም ከ58 ሚሊዮን በላይ የቴሌብር ተጠቃሚዎችን በማፍራትና የኢንዱስትሪ ፓርኮችን ቁጥር በማስፋፋት ዘመኑን የዋጀ የቴክኖሎጂ አብዮት ተካሂዷል።
በማዕድን ዘርፍ የተከናወኑት የሪፎርም ስራዎችም እንዲሁ እጅግ አስደናቂ ናቸው። የኮንትሮባንድ ንግድን በመግታትና የወርቅ ምርትን ከ3.3 ቶን ወደ 38.8 ቶን በማሳደግ፣ ዘርፉ የውጭ ምንዛሬ ግኝታችንን ወደ ላቀ ደረጃ አሸጋግሯል።
የቱሪዝም ዘርፉም በተመሳሳይ በገበታ ለሀገርና በሌሎች የቱሪዝም መዳረሻዎች ልማት፣ የውጭ ቱሪስት ፍሰትን ወደ 1.3 ሚሊዮን በማድረስ ሀገራችንን ወደ ተፈጥሯዊ የቱሪዝም መዳረሻነት ቀይሯታል።
በዲፕሎማሲውና በፖለቲካው መስክም የተመዘገበው ስኬት የሚያስደምም ነው። ኢትዮጵያ የነበሩባትን ውስብስብ ጫናዎች በብልሃት ተቋቁማ፣ የውጭ ፖሊሲዋን ሚዛናዊ በማድረግ ወደ ብሪክስ (BRICS) አባልነት መቀላቀሏ ዓለም አቀፍ ተደማጭነቷን አረጋግጧል።
በድምሩ ሲታይ እነዚህ ሁሉ ስኬቶች በአንድ ላይ ሲገመገሙ ኢትዮጵያ በእርግጥም ተአምራዊ በሚባል የለውጥ ጎዳና ላይ ትገኛለች። ይህን ሁሉ ውስብስብ ሀገራዊ፣ ቀጠናዊና ዓለም አቀፍ ጫና ተቋቁሞ ማሳካት የቻለው "መፍጠር፣ መፍጠንና መዝለል" በሚል መርህ የተቃኘው የፖለቲካ ኢኮኖሚ ሥርዓትና ቆራጥ አመራር በመኖሩ ነው።
ይህ እንደ አዲስ የጀመረው የለውጥና የዝላይ ጉዞ በአጭር ጊዜ ከግብ ሲደርስ፣ ኢትዮጵያ በብልፅግና ማማ ላይ ደምቃ በመውጣት የአፍሪካዊ ተምሳሌትነትን አልፋ የዓለም የብልፅግና ተምሳሌት እንደምትሆን አያጠራጥርም።
የ5ቱ ዓመታት ገፆች፣ የዚህችን ታላቅ ሀገር አይበገሬነትና ትንሣኤ በደማቁ የፃፉ ህያው የድል ድርሳናት ናቸው!
በአዶኒያስ ወ/አረጋይ
#ethiopiarising #historyinthemakinget #foodsovereigntyet #greenlegacyethiopia #ethiopiainbrics

የሊቢያው ኦላ ኢነርጂ የቶታልኤነርጂስን የኢትዮጵያ ንብረቶች በሙሉ ጠቀለለ
የሊቢያው ኦላ ኢነርጂ ግሩፕ በኢትዮጵያ የሚገኙትን የፈረንሳዩ ቶታልኤነርጂስ ንብረቶች በሙሉ ለመጠቅለል የሚያስችለውን የግዢ ስምምነት በፓሪስ ተፈራረመ።
ይህ ስምምነት ኦላ ኢነርጂ በኢትዮጵያ የነዳጅ ማከፋፈል ገበያ ውስጥ ትልቁ የውጭ ኩባንያ ያደርገዋል።
ይህ ግዙፍ የአክሲዮን ግዢ በኢትዮጵያ የሚገኙ ወደ 120 የሚጠጉ የነዳጅ ማደያዎችን፣ የ13 ሺህ ሜትር ኩብ አቅም ያለውን የነዳጅ ማከማቻ ተርሚናል እና ተያያዥ የንግድ እንቅስቃሴዎችን ያጠቃልላል።
በስምምነቱ ላይ የሊቢያ ዘይትና ጋዝ ሚኒስትር ከሊፋ አብዱልሳዲቅ እና የቶታልኤነርጂስ ዋና ስራ አስፈፃሚ ፓትሪክ ፑያን ጨምሮ የሁለቱም ወገኖች ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።
ግዢው ሊቢያ በአፍሪካ አህጉር ያላትን የኢኮኖሚ ተፅዕኖ እና የውጭ ኢንቨስትመንት ለማስፋፋት የምታደርገውን ጥረት የሚያጠናክር መሆኑ ተገልጿል።
Seledadotio

2 months ago
አሜሪካ በኢራን ነዳጅ ላይ የጣለችውን ማዕቀብ አላላች
ዋሽንግተን ከአስርት ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የኢራን ነዳጅ በአሜሪካ ዶላር እንዲሸጥ በመፍቀድ ቴህራን ላይ የጣለችውን ማዕቀብ በጊዜያዊነት አነሳች።
ለ60 ቀናት የሚቆየውን የማዕቀብ ማላላት እርምጃ ሰኞ ምሽት ይፋ ያደረገው የአሜሪካ ግምጃ ቤት ነው። ይህ እርምጃ የኢራንን ኢኮኖሚ አንቆ የያዘው እና ለረጅም ጊዜ የቆየው የአሜሪካ ማዕቀብ ዋነኛ ምሰሶዎች እንዲወገዱ ያደርጋል።
በዚህ የአስቸኳይ ጊዜ ፈቃድ መሠረት ኢራን እስከ ነሐሴ ወር ድረስ ድፍድፍ ነዳጅ እንዲሁም የፔትሮኬሚካል ምርቶችን ማምረት፣ መሸጥ እና መላክ ትችላለች። ይህ የማዕቀብ እፎይታ የኢራን ነዳጅ በቀጥታ ወደ አሜሪካ እንዲገባም ያስችላል።
በተጨማሪም የኢራን የባንክ ዝውውር፣ ኢንሹራስ እና ትራንስፖርት ዘርፍ ላይ የተጣለው ማዕቀብ መነሳቱ ቴህራን ከዚህ ቀደም ድፍድፍ ነዳጇን ለመሸጥ ስትከተል የነበረውን ውስብስብ አሰራር ያስቀራል።
የግምጃ ቤት ኃላፊው ስኮት ቤንሰንት እንደተናገሩት ለ60 ቀናት የሚቆይ የማዕቀብ እፎይታ የተሰጣት ኢራን በምላሹ ወሳኙ የባሕር መተላለፊያ የሆነውን የሆርሙዝ ወሽመጥ ለመክፈት ቃል ገብታለች።
የዓለም አቀፉ አቶሚክ ኤነርጂ ኤጀንሲ የኒውክሌር ተቆጣጣሪዎችም ወደ አገሪቱ እንዲገቡ ትፈቅዳለች ብለዋል።
ኢራን ግን ይህ ተቆጣጣሪዎች ወደ አገሪቱ እንዲገቡ ልትፈቅድ ነው መባሉን አስተባብላለች።
አሜሪካ የማዕቀብ ማላላት እርምጃውን የወሰደችው ስዊዘርላንድ ውስጥ ሁለቱን አገራት ሲያደራድሩ የነበሩት አሸማጋዮች ጥሩ መሻሻል መታየቱን ከገለጹ በኋላ ነው።
ኳታር እና ፓኪስታን ሰኞ ዕለት ባወጡት መግለጫ አሜሪካ እና ኢራን “በ60 ቀናት ውስጥ የመጨረሻ ስምምነት ላይ ለመድረስ የሚያስችል ፍኖተ ካርታ” ላይ መስማማታቸውን አስታውቀዋል።
የአሜሪካው ምክትል ፕሬዝዳንት ጄዲ ቫንስም የፎቶው ባለመብት የመጀመሪያው ዙር ንግግር “በጣም ጥሩ መሠረት” መጣሉን ተናግረዋል።
BBC

3 months ago
የዩክሬን ግጭት 'እየተጠናቀቀ ነው' ብለው እንደሚያስቡ ፑቲን ተናገሩ
ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን አገራቸው ከዩክሬን ጋር እያካሄደች ያለችው ጦርነት እያበቃ ነው ብለው እንደሚያስቡ ተናገሩ።
ፕሬዚዳንቱ ይህንን ያሉት ሶቪየት ኅብረት ናዚ ጀርመንን ድል ያደረገችበትን በዓል ካከበረች በኋላ ከጋዜጠኞች ጋር በነበራቸው ቆይታ ወቅት ነው።
"ጉዳዩ እየተጠናቀቀ ነው ብዬ አስባለሁ" ሲሉ በዩክሬን እየተካሄደ ስለሚገኘው "ልዩ ወታደራዊ ዘመቻ" ተናግረው ምዕራባውያን ለኪዬቭ መንግሥትን የሚያደርጉትን ድጋፍ ኮንነዋል።
የሩሲያ ዓመታዊ የድል በዓል ዩክሬን በቀዩ አደባባይ በድሮኖች ጥቃት ልታደርስ ትችላለች በሚል ስጋት የተለመደውን የታንክ እና የሚሳኤል ሠልፍ አላካሄዱም።
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በመጨረሻ ደቂቃ ባደራደሩት እና በሞስኮ እና በኪየቭ መካከል በተደረገ የተኩስ አቁም ስምምነት የጥቃት ስጋቱ ቀንሶ ሠልፉ ያለ ምንም አደጋ ተጠናቋል።
ፑቲን አስተያየትቱን የሰጡት የድል ቀን ንግግራቸውን ጦርነቱን ምክንያታዊነት ለማረጋገጥ ከተጠቀሙ ከጥቂት ሰዓታት በኋላ ነው።
በንግግራቸውም ሩሲያ "ፍትሃዊ" ጦርነት እየተዋጋች እንደሆነ እና ዩክሬንን "በኔቶ የሚታጠቀ እና የሚደገፍ ጠበኛ ኃይል" ብለው ጠርተዋታል።
ምዕራባውያን ዩክሬንን ስለመርዳታቸው በተመለከተ በጋዜጣዊ መግለጫ ወቅት የተጠየቁት ፑቲን "እርዳታ ቃል ገብተው እስከ ዛሬ ድረስም ከሩሲያ ጋር ግጭቱን ማቀጣጠል ጀመሩ። ጉዳዩ እያበቃ ነው ብዬ ባስብም ግን ከባድ ጉዳይ ነው" ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል።
የሩሲያ ኃይሎች በ2014 ክሬሚያን እና የምሥራቅ ዩክሬን ክፍሎችን የተቆጣጠሩ ሲሆን እአአ በየካቲት 2022 የዩክሬን ሙሉ ወረራን ጀመሩ።
ፑቲን የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዜሌንስኪን የሚያገኙት ዘላቂ የሰላም ስምምነት ከተደረሰ በኋላ ብቻ እንደሆነ ተናግረዋል።
"በሦስተኛ አገር መገናኘትም ቢቻልም ግን በዚህ ዝግጅት ላይ ለመሳተፍ እና ለመፈረም የረዥም ጊዜ ታሪካዊ እይታን ለመፍጠር የሰላም ስምምነት ላይ የመጨረሻ ስምምነቶች ከተደረሱ በኋላ ብቻ ነው። ይህም የመጨረሻ እርምጃ መሆን አለበት" ሲሉ አክለዋል።
ዜሌንስኪ በግል ሊያገኟቸው ዝግጁ መሆናቸውን ቢሰሙም "እንዲህ አይነት መግለጫዎችን ስንሰማ ይህ የመጀመሪያ ጊዜ አይደለም" ብለዋል ፑቲን።
ፑቲን ለአውሮፓ አዲስ የደህንነት ስምምነቶችን ለመደራደር ፈቃደኛ እንደሆኑ እና የሚመርጡት የድርድር አጋር የጀርመን የቀድሞ ቻንስለር ጄርሃርድ ሽሮደር እንደሆኑ ጠቅሰዋል።
የቀድሞው ቻንስለር የፑቲን የረዠም ጊዜ ወዳጅ ሲሆኑ በሩሲያ መንግሥት ባለቤትነት ስር ላሉ የኤነርጂ ኩባንያዎች ላይ በመሥራታቸው ምክንያት አወዛጋቢ ናቸው።
ባለፈው ሳምንት የአውሮፓ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት አንቶኒዮ ኮስታ የአውሮፓ ኅብረት ከሩሲያ ጋር ለመደራደር "ተስፋ" እንዳለው እና ዜሌንስኪ እንዲህ ዓይነት እርምጃን እንደሚደግፉ እንደሚያምኑ ተናግረዋል።
በፋይናንሺያል ታይምስ በተጠቀሰው የኮስታ ንግግር መሠረት የአውሮፓ ኅብረት መሪዎች "ይህንን ለማድረግ ትክክለኛው ጊዜ ሲመጣ ከሩሲያ ጋር በብቃት ለመወያየት ምን እንደሚያስፈልገን" እየተማከሩ እንደሆነ ጠቅሰዋል።
በአሜሪካ በተመራው የተኩስ አቁም ስምምነት መሠረት ኪዬቭ እና ሞስኮ አንድ ሺህ እስረኞችን ለመለዋወጥም ተስማምተዋል። ፑቲን ቅዳሜ ዕለት ሩሲያ ስለልውውጡ ምንም ዓይነት መረጃ ከዩክሬን በኩል እስካሁን እንዳልሰማች ተናግረዋል።
በሁለት አስርት ዓመታት ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ በ'ቀዩ አደባባይ' ሠልፍ ላይ ምንም ዓይነት ወታደራዊ መሳሪያ ያልታየ ሲሆን ክሪምሊን በተለምዶ የሩሲያን ወታደራዊ ኃይል ለዓለም አቀፍ መድረክ የምታሳይበት ሰልፍ ነው።
በዝግጅቱ ላይ የተሳተፉት ጋዜጠኞች በጣም ጥቂት የነበሩ ሲሆን ብዙ ዓለም አቀፍ የሚዲያ ተቋማት ፈቃድ አልተሰጣቸውም።

4 months ago
አሜሪካ እና ኢራን የሆርሙዝ ወሽመጥን ለመክፈት ከተስማሙ በኋላ የነዳጅ ዋጋ ቀነሰ
#fastmereja I አሜሪካ እና ኢራን የሆርሙዝ ወሽመጥ እንዲከፈት የሚያደርግ የሁለት ሳምንት ተኩስ አቁም ለማድረግ መስማማታቸውን ተከትሎ ዓለም አቀፉ የነዳጅ ዋጋ ከፍተኛ ቅናሽ አሳየ።
ዓለም አቀፍ የነዳጅ ዋጋን ለመለካት ጥቅም ላይ የሚውለው የብሬንት ድፍድፍ ነዳጅ የአንድ በርሜል ዋጋ በ13 በመቶ ገደማ ቀንሶ 94.80 ዶላር ገብቷል። በአሜሪካ የሚሸጠው ነዳጅ ደግሞ የ15 በመቶ ቅናሽ በማሳየት ዋጋው 96.75 ዶላር ደርሷል።
አሁንም ቢሆን ግን የነዳጅ ዋጋ የኢራን ጦርነት ከመጀመሩ አስቀድሞ ሲሸጥ ከነበረበት በበርሜል 70 ዶላር ገደማ ዋና የጨመረ ሆኖ ቀጥሏል።
በአሜሪካ እና ኢራን ጥቃት ተከፈተባት ኢራን በሆርሙዝ ወሽመጥ በኩል የሚያልፉ መርከቦች ላይ ጥቃት እንደምትፈጽም ከዛተች በኋላ የመካከለኛው ምሥራቅ ነዳጅ እና ጋዝ አቅርቦች የተስተጓጎለ፣ ሲሆን የኤነርጂ ዋጋም በከፍተኛ መጠን ጨምሯል።
ወሽመጡ መዘጋቱን ተከትሎ ለረጅም ጊዜ ባሕር ላይ የቆዩ በርካታ ነዳጅ ጫኝ መርከቦች በአሁኑ ስምምነት እንዲያልፉ እንደሚፈቀድላቸው ይጠበቃል። የመርከቦቹ ማለፍ ለዓለም አቀፍ የነዳጅ ገበያ ላይ ትልቅ እፎይታ እንደሚሆን ባለሙያዎች እየተናገሩ ነው።
ዘገባው የቢቢሲ አማርኛ ነው

5 months ago
ኢራን የኒውክሌር ኃይል ማመንጫዋ በድጋሚ ጥቃት እንደተፈጸመበት አስታወቀች
የኢራን አውቶሚክ ኤነርጂ ድርጅት ‘ቡሼህር’ የተባለው የኒውክሌር ኃይል ማመንጫ ተቋም በትናንትናው ዕለት በድጋሚ ጥቃት እንደተፈጸበት አስታወቀ።
ዓለም አቀፉ የአውቶሚክ ኤነርጂ ተቋም በበኩሉ በኢራን የኒውክሌር ኃይል ማመንጫ ላይ የተሰነዘረ ጥቃት “ግቢውን ስለመምታቱን” በቴህራን እንደተነገረው ገልጿል።
የኒውክሌር ስፍራው የተመታው አሜሪካ እና እስራኤል የከፈቱት “ቀጣይነት ያለው” ጥቃት እንደሆነ የኢራኑ አውቶሚክ ኤነርጂ ድርጅት ተግሯል።
ይሁን እንጂ በጥቃቶቹ “የፋይናንስም ሆነ ቴክኒካል እንዲሁም በሰው ላይ ጉዳት” አለመድረሱን አስታውቋል። “የተቋሙ የትኛውም ክፍል” አልተመታም ብሏል።
እንደ አውቶሚክ ኢነርጂ ድርጅቱ ገለጻ፤ ይኸው የኒውክሌር ኃይል ማመንጫ ከሳምንት በፊት ጥቃት ደርሶበት የነበረ ቢሆንም የመጀመሪያው ጥቃትም በሰው እና በንብረት ላይ ጉዳት አላደረሰም።
“በሰላማዊ የኒውክሌር ተቋማት ላይ” የተፈጸሙትን ጥቃቶች ያወገዘው ድርጅቱ፤ ይህ ዓይነት እርምጃዎች ለቀጣናው በተለይም በባሕረ ሰላጤው “ለሚገኙ አገራት” ደኅንነት “አደገኛ እና ሊቀለበስ የማይችል መዘዝ ያመጣሉ” ሲል አስጠንቅቋል።
ዓለም አቀፉ የአውቶሚክ ኤነርጂ ተቋም ባወጣው መግለጫ ስለ ጥቃቱ ከኢራን መረጃ እንደደረሰው ገልጿል። “እንደ ኢራን ገለጻ በራሱ የኒውክሌር ኃይል ማመንጫው ላይ ወይም ሠራተኞች ላይ የደረሰ ጉዳት የለም፤ የማመንጫው ሁኔታ ጥሩ ነው” ብሏል።
የተቋሙ ኃላፊ ራፋኤል ግሮሲ “በግጭቱ የኒውክሌር ደኅንነት ስጋትን ለማስወገድ ሲባል” ተሳታፊ አገራት ወታደራዊ እርምጃ ከመውሰድ “በከፍተኛ መጠን እንዲታቀቡ” በድጋሚ ጠይቀዋል።
በደቡባዊዋ ኢራን ከተማ ቡሼህር የሚገኘው እና በሥራ ላይ ያለው ብቸኛው የኒውክሌር ኃይል ማመንጫ የተጠናቀቀው በሩሲያ እገዛ ነበር።
አከራካሪው የኢራን ኒውክሌር ፕሮግራም አገሪቱ ዓለም አቀፍ ማዕቀብ እንዲጣልባት ምክንያት ሆኗል። አሜሪካ እና እስራኤል ኢራን ላይ ጥቃት የከፈቱት ዋሽንግተን እን ቴህራም ጄኔቫ ውስጥ ቀጥተኛ ባልሆነ መንገድ ሦስተኛ ዙር የኒውክሌር ድርድር ካደረጉ ከሁለት ቀናት በኋላ ነበር።

Sponsored by
Surafel
5 months ago
የኢራን የኒውክሌር ጣቢያ ተመታ
* ወታደራዊ እርምጃ በአስቸኳይ ይቁም!
#ethiopia | ዛሬ፣ ቅዳሜ መጋቢት 12 ቀን 2018 ዓ.ም. ጠዋት፣ ኢራን ከቁልፍ የኒውክሌር ተቋማቷ አንዱ በሆነው ናታንዝ (Natanz) ላይ ጥቃት መፈጸሙን አስታውቃለች።
ይህንን ተከትሎ የተባበሩት መንግሥታት የኒውክሌር ተቆጣጣሪ ተቋም (IAEA) ማንኛውንም የኒውክሌር አደጋ ስጋት ለማስወገድ ሲባል ወታደራዊ እርምጃ በአስቸኳይ እንዲቆም አሳስቧል።
ዓለም አቀፉ የአቶሚክ ኤነርጂ ኤጀንሲ ባወጣው መግለጫ፣ ከጣቢያው ውጭ ባለው የራዲዬሽን መጠን ላይ እስካሁን ምንም ዓይነት መጨመር እንዳልተመዘገበ ገልጾ መረጃዎችን እያጣራ መሆኑን አስታውቋል።
የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ራፋኤል ግሮሲ ማንኛውንም የኒውክሌር አደጋ ለማስወገድ ሲባል ሁሉም ወገኖች ወታደራዊ ተዓቅቦ እንዲያደርጉ በድጋሚ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።
ከመሬት በታች የሚገኘው ይህ የኢራን የኒውክሌር ጣቢያ፣ ባለፈው ሐምሌ ወር ላይም በአሜሪካ ተደብድቦ እንደነበር ይታወሳል።
ቴህራን የኒውክሌር ፕሮግራሟ ለሰላማዊ ጥቅም ብቻ የሚውል መሆኑን ብትገልጽም፣ የጥራት ደረጃው 60 በመቶ የደረሰ ዩራኒየም ማበልጸጓ ለጦር መሣሪያነት ከሚያስፈልገው 90 በመቶ ጋር የቀረበ መሆኑ ስጋትን ፈጥሯል።
ይህ ጥቃት የተፈጸመው ዋሽንግተንና ቴህራን ስለ ኒውክሌር ፕሮግራሙ ድርድር በጀመሩ በሁለተኛው ቀን መሆኑ፣ የሰላም ሂደቱን ይበልጥ አዳጋች ሊያደርገው እንደሚችል ተገምቷል።
#getu #ethiopia #breakingnews #iran #nuclearattack #iaea #natanz #globalsecurity #news #ሰበርዜና #ኢራን #ኒውክሌር #ተመድ #ጌጡተመስገን #getutemesgen

8 months ago
600 ሚሊዮን አፍሪካዊያን አሁን ድረስ የኤሌክትሪክ ብርሃን ማየት እንዳልቻሉ የአፍሪካ ህብረት ተናገረ
#ethiopia | ባለው የተደራሽነት ችግር ምክንያት 1 ቢሊዮን ገደማ አፍሪካዊያን ምግባቸውን የሚያበስሉት ንፅህናውን ባልጠበቀ እና ባህላዊ በሆነ መንገድ ነውም ተብሏል።
ይህ የተባለው ፊታችን ታህሳስ 1 እና 2 2018 ዓ.ም የሚካሄደውን የአፍሪካ ኢነርጂ ብቃት ጉባኤን በተመለከተ ለጋዜጠኞች መግለጫ በተሰጠበት ወቅት ነው።
መግለጫውን የሰጡት በአፍሪካ ህብረት የመሰረተ ልማትና ኢነርጂ ኮሚሽነር የሆኑት ሌራቶ ማታቦጌ፤ አፍሪካ ኤሌክትሪክን ለህዝቧ ለማዳረስ ገና ብዙ ስራዎች ይጠብቋታል ብለዋል።
የጉባኤው አላማ የህብረቱ አባል ሃገራት በኤነርጂው ዘርፍ ያላቸውን ተሞክሮ የሚጋሩበት፣ በየሃገራቱ ያሉ የኤነርጂ ብቃትና ቁጠባ ስትራቴጂዎች አተገባበር፣ያሉ ችግሮች ላይ በመነጋገር በዘርፉ የተሻለ ውጤት ካላቸው ልምድ ሚወሰድበት ነውም ብለዋል።
በኤነርጂው ዘርፍ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው የሚካሄደው በተባለው በዚህ ጉባኤ ኢትዮጵያም በኤነርጂ መሰረተ ልማት የተሻለ የፋይናንስ ሞዴል ካላቸው የአፍሪካ ሃገራት ልምድ በመውሰድ በዘርፉ የምትከተለውን ፖሊሲ እንድትፈትሽ እድል ይፈጥርላታል ያሉት የኢትዮጵያ ነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር ኢንጅነር ባህሩ ኦልጂራ ናቸው።
ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ፤ በኢትዮጵያ ብሔራዊ የኤሌክትሪክ ተደራሽነት ፕሮግራም ተቀርጾ እየተሰራ መሆኑን ተናግረው፤ ኢትዮጵያ የታዳሽ ኃይል አቅም እንዳላትና በምስራቅ አፍሪካ የታዳሽ ኃይል ማዕከል ለመሆን እየሰራች እንደምትገኝም ጠቁመዋል።
በሚቀጥለው ሳምንት በሚካሄደው በዚህ የኤነርጂ ብቃት ላይ ባተኮረው ጉባኤ ከ400 በላይ የዘርፉ ተዋንያን ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃል መባሉን ሰምተናል ያለው ሸገር ኤፍ ኤም ነው።

1 year ago
የመስከረሙ ሙሽራ
#ethiopia | ክረምት አልፎ ብርሃን ሲወጣ በወርሃ መስከረም ዓለም ሁሉ ሊያየው የሚጓጓለት ሰርግ በኢትዮጵያውያን እየተደገሰ ነው፡፡ ይኸ ሰርግ ከዚህ በፊት ዓለም የሚያውቀውን ሰርግ ዓይነት አይደለም፡፡
ልዩ የሚያደርገውም ደጋሹ ግለሰብ ሳይሆን ኢትዮጵያ የምትባል ትልቅ እና ታሪካዊ ሀገር፤ ሙሽራውም ሰው ሳይሆን ትርፋቱ ከኢትዮጵያ አልፎ ለዓለም የሚተርፍ ታላቅ ግድብ መሆኑ ነው፡፡
ኢትዮጵያ ይህንን ታላቅ ሰርግ ስታሰናዳም ለግብዣው የጎረቤት እና የዓባይ ተፋሰስ ሀገራትን በተለይም ግብጽና ሱዳንን በፍጹም አልዘነጋችም፡፡
ይልቁኑ በሀገሪቱ መሪ በኤ.ፌ.ዴ.ሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ ዐሕመድ በኩል በዚሁ ታላቅ ድግስ እንዲታደሙ የአክብሮት ግብዣ አቅርባለች፡፡
የመስከረሙሙሽራ ኢትዮጵያውያን ያለምንም የብሄር፣ የሃይማኖት፣ የጾታ እና የዕድሜ ልዩነት በጋራ የቆሙለት እና በማህጸን ካለ ጽንስ እና በመቃብር ካለ አስክሬን በስተቀር ሁሉም የአቅሙን ያህል ከተረፈው ሳይሆን ከጉድለቱ አስተዋጽኦ ያደረገበት ታላቁ የዓባይ ግድብ ነው፡፡
አዎን ይህን ታላቅ ግድብ ያለምንም የውጭ ኃይሎች ድጋፍ ኢትዮጵያውያን ለ14 ዓመት ተንከባክበው፤ የውስጥ እና የውጭ ተግዳሮቶችንም ተቋቁመው አሳድገው ለጎጆ ሊያበቁት ድግሷ እንዳመረላት እመቤት ሽር ጉድ እያሉ ነው፡፡
ስለሆነም ክረምቱ አልፎ ጨለማው ሲገፍፍ እና ብርሃን ሲወጣ ታላቁ የዓባይ ግደብም ለዓለም ሁሉ ብርሃን ሆኖና ተሞሽሮ ይገለጣል፡፡
በዚሁ ጉዳይ ዙሪያ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሰኔ 26/2017 ዓ/ም ለሕዘብ ተወካዮች ምክር ቤት ባደረጉት ማብራሪያ “የህዳሴ ግድብ አልቋል እናስመርቀዋለን፤ ከመመረቁ በፊት ብንረብሽ ብለው የሚያስቡ ሰዎች አሉ፤ ነገር ግን ክረምቱ ሲያልቅ እናስመርቀዋለን።
ለታችኛው ተፋሰስ ሀገራት ያለኝ መልዕክት ለግብፅና ለሱዳን ህዳሴ በረከት ነው። የሚመጣው ልማትና ኤነርጂ ለሁሉም ሀገራት የሚተርፍም ነው።
በህዳሴ ግድብ ምክንያት የግብጽ አስዋን ግድብ አንድ ሊትር ውሃ አልቀነሰም።
ኢትዮጵያ እስከበለጸገችና እስካደገች ድረስ የግብፅ እና የሱዳን ወንድሞቻችንን ጉዳት አንፈልግም።
ኤነርጂውንና ውሃውን በጋራ እንጠቀማለን፤ ልማትና ዕድገትም ይመጣል። ኢትዮጵያ ከታችኛው ተፋሰስ ሀገራት ጋር ለመነጋገር፤ ለመደራደርና፤ ለመሥራት አሁንም ዝግጁ ናት።
ለግብፅና ለሱዳን እንዲሁም ለተፋሰሱ ሀገራት መንግሥታት በሙሉ መስከረም ላይ ህዳሴን ስናስመርቅ የደስታችን ተካፋይ እንዲሆኑ በይፋ እንጋብዛለን” ብለዋል፡፡
የጠቅላይ ሚኒስትሩ መልዕክት በጥቅሉ ሲታይ የታላቁ ዓባይ ግድብ የግንባታ ሥራ በሴራ እንዳልተደናቀፈው ሁሉ ምረቃውንም በባዳም ሆነ በባንዳ ማደናቀፍ አይታሰብም የሚል ነው፡፡
የሚያዋጣው ጉዳይም የሰርጉም የትሩፋቱም ተቋዳሽ መሆን እና በጋራ አብሮ መልማት ብቻ ይሆናል።
#fikadu_ketema

Comments