Logo
FastMereja
አሜሪካ እና ኢራን የሆርሙዝ ወሽመጥን ለመክፈት ከተስማሙ በኋላ የነዳጅ ዋጋ ቀነሰ
#fastmereja I አሜሪካ እና ኢራን የሆርሙዝ ወሽመጥ እንዲከፈት የሚያደርግ የሁለት ሳምንት ተኩስ አቁም ለማድረግ መስማማታቸውን ተከትሎ ዓለም አቀፉ የነዳጅ ዋጋ ከፍተኛ ቅናሽ አሳየ።

ዓለም አቀፍ የነዳጅ ዋጋን ለመለካት ጥቅም ላይ የሚውለው የብሬንት ድፍድፍ ነዳጅ የአንድ በርሜል ዋጋ በ13 በመቶ ገደማ ቀንሶ 94.80 ዶላር ገብቷል። በአሜሪካ የሚሸጠው ነዳጅ ደግሞ የ15 በመቶ ቅናሽ በማሳየት ዋጋው 96.75 ዶላር ደርሷል።

አሁንም ቢሆን ግን የነዳጅ ዋጋ የኢራን ጦርነት ከመጀመሩ አስቀድሞ ሲሸጥ ከነበረበት በበርሜል 70 ዶላር ገደማ ዋና የጨመረ ሆኖ ቀጥሏል።

በአሜሪካ እና ኢራን ጥቃት ተከፈተባት ኢራን በሆርሙዝ ወሽመጥ በኩል የሚያልፉ መርከቦች ላይ ጥቃት እንደምትፈጽም ከዛተች በኋላ የመካከለኛው ምሥራቅ ነዳጅ እና ጋዝ አቅርቦች የተስተጓጎለ፣ ሲሆን የኤነርጂ ዋጋም በከፍተኛ መጠን ጨምሯል።

ወሽመጡ መዘጋቱን ተከትሎ ለረጅም ጊዜ ባሕር ላይ የቆዩ በርካታ ነዳጅ ጫኝ መርከቦች በአሁኑ ስምምነት እንዲያልፉ እንደሚፈቀድላቸው ይጠበቃል። የመርከቦቹ ማለፍ ለዓለም አቀፍ የነዳጅ ገበያ ላይ ትልቅ እፎይታ እንደሚሆን ባለሙያዎች እየተናገሩ ነው።

ዘገባው የቢቢሲ አማርኛ ነው

4 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.