3 months ago
የኢራን የኒውክሌር ጣቢያ ተመታ
* ወታደራዊ እርምጃ በአስቸኳይ ይቁም!
#ethiopia | ዛሬ፣ ቅዳሜ መጋቢት 12 ቀን 2018 ዓ.ም. ጠዋት፣ ኢራን ከቁልፍ የኒውክሌር ተቋማቷ አንዱ በሆነው ናታንዝ (Natanz) ላይ ጥቃት መፈጸሙን አስታውቃለች።
ይህንን ተከትሎ የተባበሩት መንግሥታት የኒውክሌር ተቆጣጣሪ ተቋም (IAEA) ማንኛውንም የኒውክሌር አደጋ ስጋት ለማስወገድ ሲባል ወታደራዊ እርምጃ በአስቸኳይ እንዲቆም አሳስቧል።
ዓለም አቀፉ የአቶሚክ ኤነርጂ ኤጀንሲ ባወጣው መግለጫ፣ ከጣቢያው ውጭ ባለው የራዲዬሽን መጠን ላይ እስካሁን ምንም ዓይነት መጨመር እንዳልተመዘገበ ገልጾ መረጃዎችን እያጣራ መሆኑን አስታውቋል።
የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ራፋኤል ግሮሲ ማንኛውንም የኒውክሌር አደጋ ለማስወገድ ሲባል ሁሉም ወገኖች ወታደራዊ ተዓቅቦ እንዲያደርጉ በድጋሚ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።
ከመሬት በታች የሚገኘው ይህ የኢራን የኒውክሌር ጣቢያ፣ ባለፈው ሐምሌ ወር ላይም በአሜሪካ ተደብድቦ እንደነበር ይታወሳል።
ቴህራን የኒውክሌር ፕሮግራሟ ለሰላማዊ ጥቅም ብቻ የሚውል መሆኑን ብትገልጽም፣ የጥራት ደረጃው 60 በመቶ የደረሰ ዩራኒየም ማበልጸጓ ለጦር መሣሪያነት ከሚያስፈልገው 90 በመቶ ጋር የቀረበ መሆኑ ስጋትን ፈጥሯል።
ይህ ጥቃት የተፈጸመው ዋሽንግተንና ቴህራን ስለ ኒውክሌር ፕሮግራሙ ድርድር በጀመሩ በሁለተኛው ቀን መሆኑ፣ የሰላም ሂደቱን ይበልጥ አዳጋች ሊያደርገው እንደሚችል ተገምቷል።
#getu #ethiopia #breakingnews #iran #nuclearattack #iaea #natanz #globalsecurity #news #ሰበርዜና #ኢራን #ኒውክሌር #ተመድ #ጌጡተመስገን #getutemesgen

Comments