2 months ago
የአውሮፓ ረጅሙ የድንግል ማርያም ሐውልት ሊመረቅ ነው
#eghiopia | በአንድ የፖላንድ ቢሊየነር ወጪው የተሸፈነው 182 ጫማ ቁመት ያለው የድንግል ማርያም ሐውልት ግንባታ ተጠናቆ በነሐሴ ወር መጨረሻ ለምረቃ እንደሚበቃ ተገለፀ።
ይህ ሐውልት በአውሮፓ አህጉር ትልቁና ረጅሙ የድንግል ማርያም ሐውልት ያደርገዋል።
የግንባታውን ወጪ ሙሉ በሙሉ የሸፈኑት ታዋቂው የፖላንድ ባለሀብት ሮማን ካርኮሲክ እና ባለቤታቸው ግራዚና መሆናቸው ታውቋል።
ፕሮጀክቱ ላለፉት አራት ዓመታት ሲያከናውኑ መቆየታቸው ነው የተገለፀው።
ይህ መንፈሳዊ ሀውልት በሀብትና በስልጣን ላይ ትኩረት በሚደረግበት በዚህ አለም ውስጥ የሰዎችን አእምሮ ወደ ላቀ መንፈሳዊ እሴትና እምነት የሚያነሳሳ አርማ እንደሆነ አስተያየት ሰጪዎች ገልጸዋል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#ethiopia #getutemesgen #poland #spiritual #statue #virginmary

በበጀት አመት ከ118 ቢሊዮን ብር በላይ ማግኘት ተችሏል
#eghiopia | የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በተጠናቀቀው የ2018 በጀት አመት 118 ነጥብ 91 ቢሊየን ብር ገቢ ማግኘቱን ገለፀ።
የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ጌቱ ገረመው (ኢ/ር) በሰጡት መግለጫ ገቢው ከኢነርጂ ሽያጭ ከአዲስ ደንበኞች መስተንግዶ፣ ከማያገለግሉ ንብረቶች ሽያጭ እና ከሌሎች ልዩ ልዩ የገቢ ምንጮች መገኘቱን ተናግረዋል፡፡
በዚህ መሰረትም ከኢነርጂ ሽያጭ 75 ነጥብ 17 ቢሊየን ብር ለማግኘት ታቅዶ የውጭ ሀገር ሽያጭን ጨምሮ 76 ነጥብ 53 ቢሊየን ብር ገቢ መገኘቱን አስረድተዋል፡፡
በተጨማሪም ከአዲስ ደንበኞች መስተንግዶ 37 ነጥብ 74 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ 39 ነጥብ 23 ቢሊየን ብር መገኘቱን ነው የገለጹት፡፡
የማያገለግሉ ንብረቶችን በመሸጥ 275 ሚሊየን ብር የተገኘ ሲሆን ከልዩ ልዩ ገቢዎች ደግሞ 2 ነጥብ 68 ቢሊየን ብር መገኘቱን አስረድተዋል፡፡
የገቢ አፈጻጸሙ 103 በመቶ መሆኑንና ከ2017 በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ88 ነጥብ 4 በመቶ እድገት ማሳየቱን አመልክተዋል፡፡
የዲጂታል ክፍያ አማራጭ የሚጠቀሙ ደንበኞች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መጥቶ በአሁን ወቅት 95 ነጥብ 3 በመቶ መደረሱን ተናግረዋል፡፡
በተጨማሪም የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ቻርጅ ማድረጊያ ጣቢያዎች ገንብቶ ወደ ስራ በማስገባትና ስራ በማስጀመር 14 ነጥብ 25 ሚሊየን ብር ገቢ ተገኝቷል ብለዋል፡፡
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#ethiopia #getutemesgen #getunews #የኢትዮጵያ #ኤሌክትሪክአገልግሎት #ኤነርጂ #ገበያ #ትርፍ

3 months ago
ወልዋሎ ዓ/ዩ የ2018 የኢትዮጵያ ዋንጫ አሸናፊ ሆነ
#eghiopia | አዲስ አበባ – ወልዋሎ ዓ/ዩ በ2018 የኢትዮጵያ ዋንጫ ፍጻሜ ላይ ሲዳማ ቡናን 2ለ0 በማሸነፍ የውድድሩ ቻምፒዮን ሆኗል።
ዛሬ ሐምሌ 2 ቀን 2018 ዓ.ም. ከጠዋቱ 5፡00 ሰዓት ጀምሮ በአዲስ አበባ ስታዲየም በተካሄደው የፍጻሜ ጨዋታ፣ ወልዋሎ ዓ/ዩ በኮንኮኒ ሀፊዝ እና በየነ ባንጃ ያስቆጠሯቸው ግቦች ሲዳማ ቡናን 2ለ0 በማሸነፍ የ2018 የኢትዮጵያ ዋንጫን አንስቷል።
ሲዳማ ቡና የ2018 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮን በመሆኑ፣ ወልዋሎ ዓ/ዩ የኢትዮጵያ ዋንጫ ፍጻሜ መድረሱን ተከትሎ ኢትዮጵያን በቀጣዩ የካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ውድድር እንደሚወክል አስቀድሞ ተረጋግጦ ነበር።
የዋንጫ ድሉም ለቡድኑ ታሪካዊ ስኬት ሆኖ ተመዝግቧል።
#ethiopia #ethiopiancup #wolwalo #sidamabunna #cafconfederationcup #getu

ንብረት ገዝተው የስም ዝውውር ያላደረጉ ዜጎች በአስቸኳይ እንዲያጠናቅቁ ታዘዘ
#eghiopia | ከሪል እስቴት አልሚዎችም ሆነ ከግለሰቦች በሰነዶች ማረጋገጫ ንብረት ገዝተው፣ እስካሁን ወደ መሬት ተቋማት በመቅረብ የስም ዝውውር ያላደረጉ እና የይዞታ ባለቤትነት ማረጋገጫ (ካርታ) ያልያዙ ባለንብረቶች ሂደቱን በአጭር ጊዜ ውስጥ እንዲያጠናቅቁ ጥሪ ቀረበ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ አቶ መኮንን ያኢ ከኤ ኤም ኤን ጋር ባደረጉት ቆይታ እንደገለጹት፤ የስመ-ንብረት ዝውውር በወቅቱ አለመደረጉ ንብረት ገዝተው የባለቤትነት ማረጋገጫ ያልያዙ ዜጎችን ለተለያዩ ከፍተኛ ጉዳቶች እና ለአደጋ እየዳረገ ይገኛል።
የስመ-ንብረት ዝውውር የመጨረሻ ግቡ ገዥው አካል ህጋዊ የይዞታ ባለቤትነት ማረጋገጫን እንዲይዝ ማድረግ ቢሆንም፣ በተለያዩ ምክንያቶች ይህንን ሳያደርጉ የቀሩ በርካታ አካላት መኖራቸውን ቢሮው ጠቁሟል።
በመሆኑም ቀደም ባሉ ጊዜያት የመኖሪያ ቤትም ሆነ ማንኛውንም በመሬት ላይ ያረፈ ንብረት ገዝተው የስም ዝውውር ያላደረጉ ባለንብረቶች፣ መብታቸውን ለማስከበርና ለከፋ አደጋ እንዳይጋለጡ ሲባል መንግስት በአስቸኳይ እና በአጭር ጊዜ ውስጥ ሂደቱን እንዲያጠናቅቁ ጥብቅ ማሳሰቢያ ሰጥቷል።
#ethiopia #addisababa #realestateethiopia #landmanagement #amn #propertylawyerthailand

Sponsored by
Surafel
Comments