የመስከረሙ ሙሽራ
#ethiopia | ክረምት አልፎ ብርሃን ሲወጣ በወርሃ መስከረም ዓለም ሁሉ ሊያየው የሚጓጓለት ሰርግ በኢትዮጵያውያን እየተደገሰ ነው፡፡ ይኸ ሰርግ ከዚህ በፊት ዓለም የሚያውቀውን ሰርግ ዓይነት አይደለም፡፡
ልዩ የሚያደርገውም ደጋሹ ግለሰብ ሳይሆን ኢትዮጵያ የምትባል ትልቅ እና ታሪካዊ ሀገር፤ ሙሽራውም ሰው ሳይሆን ትርፋቱ ከኢትዮጵያ አልፎ ለዓለም የሚተርፍ ታላቅ ግድብ መሆኑ ነው፡፡
ኢትዮጵያ ይህንን ታላቅ ሰርግ ስታሰናዳም ለግብዣው የጎረቤት እና የዓባይ ተፋሰስ ሀገራትን በተለይም ግብጽና ሱዳንን በፍጹም አልዘነጋችም፡፡
ይልቁኑ በሀገሪቱ መሪ በኤ.ፌ.ዴ.ሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ ዐሕመድ በኩል በዚሁ ታላቅ ድግስ እንዲታደሙ የአክብሮት ግብዣ አቅርባለች፡፡
የመስከረሙሙሽራ ኢትዮጵያውያን ያለምንም የብሄር፣ የሃይማኖት፣ የጾታ እና የዕድሜ ልዩነት በጋራ የቆሙለት እና በማህጸን ካለ ጽንስ እና በመቃብር ካለ አስክሬን በስተቀር ሁሉም የአቅሙን ያህል ከተረፈው ሳይሆን ከጉድለቱ አስተዋጽኦ ያደረገበት ታላቁ የዓባይ ግድብ ነው፡፡
አዎን ይህን ታላቅ ግድብ ያለምንም የውጭ ኃይሎች ድጋፍ ኢትዮጵያውያን ለ14 ዓመት ተንከባክበው፤ የውስጥ እና የውጭ ተግዳሮቶችንም ተቋቁመው አሳድገው ለጎጆ ሊያበቁት ድግሷ እንዳመረላት እመቤት ሽር ጉድ እያሉ ነው፡፡
ስለሆነም ክረምቱ አልፎ ጨለማው ሲገፍፍ እና ብርሃን ሲወጣ ታላቁ የዓባይ ግደብም ለዓለም ሁሉ ብርሃን ሆኖና ተሞሽሮ ይገለጣል፡፡
በዚሁ ጉዳይ ዙሪያ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሰኔ 26/2017 ዓ/ም ለሕዘብ ተወካዮች ምክር ቤት ባደረጉት ማብራሪያ “የህዳሴ ግድብ አልቋል እናስመርቀዋለን፤ ከመመረቁ በፊት ብንረብሽ ብለው የሚያስቡ ሰዎች አሉ፤ ነገር ግን ክረምቱ ሲያልቅ እናስመርቀዋለን።
ለታችኛው ተፋሰስ ሀገራት ያለኝ መልዕክት ለግብፅና ለሱዳን ህዳሴ በረከት ነው። የሚመጣው ልማትና ኤነርጂ ለሁሉም ሀገራት የሚተርፍም ነው።
በህዳሴ ግድብ ምክንያት የግብጽ አስዋን ግድብ አንድ ሊትር ውሃ አልቀነሰም።
ኢትዮጵያ እስከበለጸገችና እስካደገች ድረስ የግብፅ እና የሱዳን ወንድሞቻችንን ጉዳት አንፈልግም።
ኤነርጂውንና ውሃውን በጋራ እንጠቀማለን፤ ልማትና ዕድገትም ይመጣል። ኢትዮጵያ ከታችኛው ተፋሰስ ሀገራት ጋር ለመነጋገር፤ ለመደራደርና፤ ለመሥራት አሁንም ዝግጁ ናት።
ለግብፅና ለሱዳን እንዲሁም ለተፋሰሱ ሀገራት መንግሥታት በሙሉ መስከረም ላይ ህዳሴን ስናስመርቅ የደስታችን ተካፋይ እንዲሆኑ በይፋ እንጋብዛለን” ብለዋል፡፡
የጠቅላይ ሚኒስትሩ መልዕክት በጥቅሉ ሲታይ የታላቁ ዓባይ ግድብ የግንባታ ሥራ በሴራ እንዳልተደናቀፈው ሁሉ ምረቃውንም በባዳም ሆነ በባንዳ ማደናቀፍ አይታሰብም የሚል ነው፡፡
የሚያዋጣው ጉዳይም የሰርጉም የትሩፋቱም ተቋዳሽ መሆን እና በጋራ አብሮ መልማት ብቻ ይሆናል።
#fikadu_ketema

1 year ago