Logo
Getu Temesgen
ባቡርና ሲኖትራክ መካከል አደጋ ተከሰተ!
#ethiopia | ​ዛሬ መጋቢት 23 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 5፡55 ሰዓት ላይ በየካ ክፍለ ከተማ ሰዓሊተ ምህረት አካባቢ በሚገኘው የባቡር መስመር ላይ የትራፊክ አደጋ ደርሷል።

​የኢትዮ-ጅቡቲ ምድር ባቡር ንብረት የሆነ ሲኖትራክ (ታርጋ ቁጥር 5-82D11-2) እና የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር (ኮድ 111)።

​ሲኖትራኩ ከላምበረት ወደ ጃክሮስ በሚጓዝበት ወቅት፣ ከአያት ወደ መገናኛ ይጓዝ ከነበረው ባቡር ጋር ተጋጭቷል።

​በባቡሩ ውስጥ ተሳፍረው በነበሩ ሁለት ሰዎች ላይ ቀላል የአካል ጉዳት ደርሷል።

​ፖሊስ በአሁኑ ወቅት የአደጋውን መንስኤ እያጣራ ሲሆን፣ በሲኖትራኩ ላይ ያለውን ከባድ ጭነት በማንሳት መንገዱን ለትራፊክ ክፍት ለማድረግ ጥረት እያደረገ ይገኛል።

​አሽከርካሪዎች ፍጥነታቸውን እንዲቆጣጠሩና ለመንገዱ አቀማመጥ ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አሳስቧል።

​#getu #addisababa #trafficaccident #lightrail #yeka #roadsafety #breakingnews #ethiopia #አዲስአበባ #ትራፊክአደጋ #ቀላልባቡር #ሰዓሊተምህረት #ጥንቃቄ #ጌጡተመስገን #getutemesgen

2 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.