3 months ago
ኳሷ አሁን በአሜሪካ ሜዳ ላይ ናት - ኢራን
********************
የኢራን ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ካዘም ጋሪባባዲ በሰጡት መግለጫ፣ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ጦርነት በዘላቂነት ለመቋጨት የሚያስችል አዲስና ሁሉን አቀፍ የሰላም ዕቅድ በመካከለኛዋ ፓኪስታን በኩል ለአሜሪካ ማቅረባቸውን አስታውቀዋል።
ጋሪባባዲ "አሁን ኳሷ በአሜሪካ ሜዳ ላይ ናት፤ ዋሽንግተን በዲፕሎማሲያዊ መፍትሔ እና በግጭት ቀጣይነት መካከል መምረጥ ይኖርባታል" ሲሉ ገልጸዋል።
የኢራን መገናኛ ብዙኃን እንደዘገቡት፣ ይህ ባለ 14 ነጥብ የሰላም ዕቅድ ቀደም ሲል አሜሪካ ላቀረበችው ባለ 9 ነጥብ ሰነድ እንደ አጸፋዊ ምላሽ የቀረበ ሲሆን፤ የደኅንነት ዋስትናን፣ የአሜሪካ ጦር ከቀጣናው እንዲወጣ፣ ማዕቀቦች እንዲነሱ እና በሊባኖስ ያለውን ጨምሮ ጦርነቱ በሁሉም ግንባሮች እንዲቆም የሚሉ ጥያቄዎችን አካትቷል።
በተጨማሪም ኢራን አሜሪካ ካሳ እንድትከፈላትና ለሆርሙዝ ሰርጥ አዲስ የሥራ ማዕቀፍ እንዲበጅ ፍላጎት እንዳላት ተገልጿል።
ይሁን እንጂ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በ"ትሩዝ ሶሻል" ገጻቸው ባሰፈሩት መልእክት፣ ዕቅዱን በቅርቡ እንደሚመለከቱት ቢገልጹም "ተቀባይነት ይኖረዋል ብዬ መገመት አልችልም" ሲሉ ጥርጣሬያቸውን አንጸባርቀዋል።
ትራምፕ ቀደም ሲል ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ በኢራን ውሎች እንዳልረኩና “በከባድ ወታደራዊ እርምጃ እናጠፋቸዋለን" ሲሉ ማስፈራራታቸው ይታወሳል።
አሜሪካ ኢራን የኒውክሌር መርሐ ግብሯን ሙሉ በሙሉ እንድታቆም ብትጠይቅም ቴህራን ግን “ፕሮግራሜ ለሰላማዊ ዓላማ ብቻ ነው” በማለት ጥያቄውን ውድቅ አድርጋዋለች።
ይህ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው አለመግባባት በሳምንቱ የነዳጅ ዋጋ ከ2022 ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ በአንድ በርሜል ከ120 ዶላር በላይ እንዲጨምር ምክንያት ሆኗል።
በጌቱ ላቀው
#iran #usa #peacetalks #donaldtrump #middleeast #geopolitics #hormuz #oilprices

የናፍጣ አቅርቦት ቀድሞ ወደ ነበረበት ተመለሰ
********************
በኢትዮጵያ የአንድ ቀን የናፍጣ አቅርቦት ከመካከለኛው ምሥራቅ ግጭት በፊት ወደ ነበረበት 9 ሚሊዮን ሊትር እንዲመለስ መወሰኑን የገንዘብ ሚኒስትሩ አሕመድ ሽዴ ዛሬ በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል።
በመካከለኛው ምሥራቅ ግጭት ምክንያት የዓለም አቀፍ የነዳጅ ዋጋ መጨመር እና አቅርቦት ላይ መስተጓጎል መፈጠሩ ይታወቃል። ይህን ተከትሎም በኢትዮጵያ የአንድ ቀን የናፍጣ አቅርቦት ወደ 4.5 ሚሊዮን ሊትር ወርዶ ነበር።
አሁን የአንድ ቀን የናፍጣ አቅርቦት ወደ ቀደመው 9 ሚሊዮን ሊትር እንዲመለስ መወሰኑን ተከትሎ ከዛሬ ጀምሮ ከጅቡቲ ወደ አዲስ አበባ መጓጓዝ እንደሚጀመር የገለጹት የገንዘብ ሚኒስትሩ አሕመድ ሽዴ ወደ ክልሎች ደግሞ ከነገ ጀምሮ መጓጓዝ ይጀምራል ብለዋል።
እስካሁን የቤንዚን እና የአውሮፕላን ነዳጅ ሙሉ በሙሉ ቀድሞ በነበረው መጠን እየቀረበ መሆኑንም የገንዘብ ሚኒስትሩ ገልጸዋል።
በዓለም አቀፍ ደረጃ የተከሰተው የነዳጅ አቅርቦት መስተጓጎል ኢኮኖሚው ላይ የሚያደርሰውን ጫና ለመከላከል መንግሥት በልዩ ግዢ በከፍተኛ ዋጋ ነዳጅ ገዝቶ እያቀረበ መሆኑንም ሚኒስትሩ አሕመድ ሽዴ አስረድተዋል።
በዚህም ምክንያት በአሁኑ ወቅት መንግሥት በየወሩ ቀድሞ ከነበረው በተጨማሪ 20 ቢሊዮን ብር እየደጎመ ነዳጅ እያቀረበ መሆኑን ነው የገለፁት።
በጌታቸው ባልቻ
#ebc #ethiopia #oilprices

4 months ago
ጦርነቱ በሰከንድ ልዩነት ቆመ!
አሜሪካና ኢራን ለሁለት ሳምንት ተኩስ አቆሙ!
* የሆርሙዝ ወሽመጥ ተከፈተ
#ethiopia | ዓለም እስትንፋሷን ይዛ በጠበቀችበት በዚያው የመጨረሻ ሰዓት፣ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በፓኪስታን ጠቅላይ ሚኒስትር ሸህባዝ ሻሪፍ ጥያቄ መሰረት በኢራን ላይ ሊሰነዝሩት የነበረውን "ሥልጣኔ አጥፊ" ጥቃት ለሁለት ሳምንት አግደዋል።
የሆርሙዝ ወሽመጥ ተከፈተ
ኢራን ወሳኙን የሆርሙዝ ወሽመጥ ለሁለት ሳምንት ክፍት ለማድረግ ተስማምታለች። ይሁን እንጂ በወሽመጡ ለሚያልፉ መርከቦች ለእያንዳንዳቸው 2 ሚሊዮን ዶላር "የማለፊያ ታሪፍ" (Transit Fee) ከኦማን ጋር በመሆን እንደምታስከፍልና ገንዘቡንም ለሀገር መልሶ ግንባታ እንደምትጠቀም ተገልጿል።
የእስላማባድ ንግግር (The Islamabad Talks)፦ በመጪው አርብ (ሚያዝያ 10) በፓኪስታን መዲና እስላማባድ የአሜሪካና የኢራን ልዑካን ፊት ለፊት ተገናኝተው ዘላቂ ሰላም ላይ ይደራደራሉ። በንግግሩ ላይ የትራምፕ ልዩ መልዕክተኞችና ምናልባትም ቪፒ ጄዲ ቫንስ ሊገኙ እንደሚችሉ ተገምቷል።
የሁለቱ ወገኖች ፉክክር፦ ዋይት ሃውስ "ይህ የአሜሪካ ድል ነው" ሲል፣ ኢራን በበኩሏ "አሜሪካን የ10 ነጥብ የሰላም እቅዳችንን እንዲቀበል አስገዳጅ ድል ተቀዳጅተናል" በማለት ደስታቸውን በቴህራን አደባባይ እየገለጹ ነው።
ያልተፈታው ስጋት፦r
ምንም እንኳ አሜሪካና ኢራን ተኩስ ቢያቆሙም፣ እስራኤል ግን በኢራን ላይ የምታደርገውን ጥቃት አሁንም እንደቀጠለች መሆኑ ተሰምቷል። "ጥቃቴን የምቀጥልባቸው ተጨማሪ ኢላማዎች አሉኝ" በማለት ፍጥጫው ገና እንዳልበረደ አመልክታለች።
#getu #breakingnews #usiranceasefire #trump #hormuzstrait #islamabadtalks #middleeastpeace #oilprices #globalsecurity #አሜሪካ #ኢራን #ሰበርዜና #ተኩስአቁም #ትራምፕ #ጌጡተመስገን #getutemesgen

48 ሰዓታት
ኢራን፣ የሆርሙዝ ሰርጥ እና የትራምፕ ማስጠንቀቂያ!
#ethiopia | ባለፉት 48 ሰዓታት በመካከለኛው ምስራቅ የታዩት ክስተቶች ዓለምን በስጋት አይን እንድትመለከት አድርገዋል።
በኢራንና በአሜሪካ መካከል ያለው ፍጥጫ ወደ አዲስ ምዕራፍ ተሸጋግሯል።
ኢራን የዓለም የነዳጅ ንግድ የደም ሥር የሆነውን የሆርሙዝ ሰርጥን ልትዘጋ ትችላለች የሚለው ስጋት አይሏል። ይህም በዓለም አቀፍ የነዳጅ ዋጋ ላይ ከፍተኛ መናር ሊያስከትል እንደሚችል ተገምቷል።
ፕሬዝዳንት ትራምፕ የአሜሪካ ጦር "በጣም በቅርብ ጊዜ" ከኢራን እንደሚወጣ ቢገልጹም፣ በሌላ በኩል ግን ማንኛውም ጥቃት ቢሰነዘር አሜሪካ "የማያዳግም ምላሽ" እንደምትሰጥ አስጠንቅቀዋል።
የኢራን ግማሽ ያህሉ የሚሳኤልና የድሮን አቅም ጥቃት ሳይደርስበት አሁንም ዝግጁ መሆኑ መገለጹ፣ አሜሪካ ጦሯን በምታወጣበት ወቅት ኢራን የበላይነቱን ለመያዝ እንድትሞክር በር ሊከፍት ይችላል ተብሏል።
የሆርሙዝ ሰርጥ መዘጋት ማለት የኢትዮጵያን ጨምሮ የበርካታ ሀገራት ኢኮኖሚ ላይ ቀጥተኛ ጫና ይፈጥራል። የነዳጅ ዋጋ መናር የኑሮ ውድነትን ይበልጥ ሊያባብሰው ይችላል።
#getu #irantension #straitofhormuz #trump #middleeastcrisis #oilprices #globalsecurity #usmilitary #geopolitics #ኢራን #ሆርሙዝሰርጥ #ትራምፕ #ነዳጅ #ኢኮኖሚ #ጌጡተመስገን #getutemesgen

Sponsored by
Surafel
Comments