2 months ago
በአሜሪካ እና በኢራን መካከል ያለው የሰላም ስምምነት የመጨረሻ ውል ላይ ደረሰ
*************
በአሜሪካ እና በኢራን መካከል የሚደረገው የሰላም ስምምነት የመጨረሻ ሰነድ መጽደቁን በሂደቱ ላይ ቁልፍ አስታራቂ የሆኑት የፓኪስታን ጠቅላይ ሚኒስትር ሸህባዝ ሸሪፍ አስታውቀዋል።
በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ጦርነት ለማቆም እና ወሳኙን የሆርሙዝ ወሽመጥ ድጋሚ ለመክፈት ያለመውን ይህንን ስምምነት አስመልክቶ ጠቅላይ ሚኒስትሩ “ሰላም እንደ አሁኑ ቀርቦ አያውቅም” ብለዋል።
ሂደቱን ለማደናቀፍ የሚነዙ የሀሰት መረጃዎችን ወደ ጎን በመተው ፓኪስታን ቀጣይ እርምጃዎችን ለማጠናቀቅ ከሁለቱም ወገኖች ጋር በቅርበት እየሰራች መሆኑን ገልጸዋል።
የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራጊቺም በበኩላቸው የጦርነቱ ማክተሚያ መቃረቡን አረጋግጠዋል።
ከሁለቱም ወገኖች ተስፋ ሰጪ መግለጫዎች ቢሰሙም፣ በአደባባይ ያላቸው የድርድር አቋም አሁንም የተራራቀ መሆኑ ይስተዋላል።
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በኢራን መገናኛ ብዙኃን የተናፈሰው የስምምነቱ ይዘት ከእውነታው የራቀ ነው ያሉ ሲሆን፣ ኢራናውያንን “በቅንነት ለመደራደር የማይመቹ” ሲሉ ተችተዋል።
በሌላ በኩል ኢራን አሜሪካ በዲፕሎማሲያዊ ሂደቱ ላይ በተደጋጋሚ ክህደት ፈጽማለች ስትል በመውቀስ፣ በዋሽንግተን ባህሪ ምክንያት የተገኘው መሻሻል ወደኋላ እየተመለሰ መሆኑን ገልጻለች።
ይሁን እንጂ ኢራን በአብዛኛዎቹ ጉዳዮች ላይ ስምምነት ላይ መደረሱንና በመጨረሻው የውስጥ ግምገማ ደረጃ ላይ እንደምትገኝ አስታውቃለች።
ፕሬዝዳንት ትራምፕ ስምምነቱ በመጪው እሁድ መጀመሪያ ላይ ሊፈረም እንደሚችል የገለጹ ሲሆን፣ ቴህራን በበኩሏ በጊዜ ሰሌዳው ላይ ጥርጣሬ ቢኖራትም ፊርማው “በሚቀጥሉት ቀናት” ሊከናወን እንደሚችል ፍንጭ ሰጥታለች።
ስምምነቱ ከተፈረመ በኋላ የሆርሙዝ ወሽመጥ ለሁሉም ክፍት እንደሚሆንና አሜሪካም በመጨረሻ የኢራንን የኑክሌር ቁሳቁስ እንደምታገኝ ተጠቅሷል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ ኢራን ማንኛውም የተኩስ አቁም ስምምነት እስከ ሊባኖስ ድረስ መዘርጋት አለበት ብላ ብታስረግጥም፣ የእስራኤል ጦር ጥቃቱን በመቀጠሉ በደቡብ ሊባኖስ በርካታ ፍንዳታዎች እየተከሰቱ ይገኛሉ ሲሉ ዘ ቴሌግራፍ እና አልጀዚራ በዘገባቸው ጠቅሰዋል።
በመሐመድ ፊጣሞ
#usiranpeacetalks #straitofhormuz #middleeastpeace #ethiopianbroadcastingcorporation

3 months ago
ኢራን የአየር ክልሏን ክፍት አደረገች!
* የመጀመሪያው በረራ ተከናወነ
ከእስራኤልና አሜሪካ ጋር በነበረው ጦርነት ምክንያት ተቋርጦ የቆየው የኢራን የበረራ አገልግሎት ዛሬ ሚያዚያ 17 ቀን 2018 ዓ.ም በይፋ መጀመሩ ተበሰረ። በቴህራን የሚገኘው ኢማም ኾሚኒ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ከሁለት ወራት ዝምታ በኋላ በድጋሚ ስራ ጀምሯል።
በዛሬው ዕለት ከቴህራን ተነስተው ወደ ቱርክ (ኢስታንቡል)፣ ኦማን (ሙስካት) እና ሳዑዲ አረቢያ (መዲና) በረራዎች ተከናውነዋል።
በኢራንና አሜሪካ መካከል የተደረሰውን ጊዜያዊ የተኩስ አቁም ተከትሎ፣ ዲፕሎማሲያዊ ጥረቶች በከፍተኛ ሁኔታ ቀጥለዋል።
የኢራን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግቺ በፓኪስታን ከከፍተኛ አመራሮች ጋር የመከሩ ሲሆን፣ ሁለተኛ ዙር ከአሜሪካ ጋር የሚደረግ ውይይትም ይጠበቃል።
የአሜሪካ ልዑክ፦ የፕሬዝዳንት ትራምፕ አማች ያሬድ ኩሽነር እና ልዩ መልዕክተኛው ስቲቭ ዊትኮፍ ወደ ኢስላማባድ በማቅናት በድርድሩ ላይ እንደሚሳተፉ ተገልጿል።
"በረራ መጀመር የሰላም የመጀመሪያው ምልክት ነው። ኢራንና አሜሪካ በፓኪስታን በኩል እያደረጉት ያለው ድርድር ውጤት ካመጣ፣ በመካከለኛው ምስራቅ ለወራት የቆየው ስጋት ሊቆም ይችላል። በተለይ ያሬድ ኩሽነር በድርድሩ ውስጥ መኖራቸው የትራምፕ አስተዳደር ለጉዳዩ የሰጠውን ትኩረት ያሳያል።"
ሰማዩ ለሰላም ክፍት ሆኗል!
#getu #irannews #middleeastpeace #aviationnews #tehranflight #jaredkushner #diplomacy #breakingnews #ኢራን #አሜሪካ #ሰበርመረጃ #በረራ #ጌጡተመስገን #getutemesgen

4 months ago
ትራምፕ በኢራን ሊገደሉ የነበሩ 8 ሴቶችን ከሞት ታደጉ
#ethiopia | ዓለምን ያስደመመ ዲፕሎማሲ! ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በኢራን የሞት ፍርድ ተፈርዶባቸው የነበሩ ስምንት ሴት ተቃዋሚዎች በእርሳቸው ቀጥተኛ ጣልቃ ገብነትና ጥያቄ ከሞት ቅጣት መትረፋቸውን በይፋ አስታወቁ።
ከስምንቱ ሴቶች መካከል አራቱ ወዲያውኑ እንዲፈቱ፣ ቀሪዎቹ አራቱ ደግሞ የአንድ ወር እስራት ብቻ ተፈርዶባቸው እንዲቆዩ ከኢራን መሪዎች ጋር ስምምነት ላይ ተደርሷል።
ትራምፕ በ"ትሩዝ ሶሻል" ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፣ የኢራን መሪዎች የአሜሪካ ፕሬዝዳንት በመሆናቸው ያቀረቡትን ጥያቄ በማክበራቸው "ከፍተኛ ምስጋና" እንዳላቸው ገልጸዋል።
ይህ እርምጃ በሁለቱ ሀገራት መካከል ባለው ከፍተኛ ውጥረት ውስጥ ለሰላም ድርድር አዲስ በር ሊከፍት እንደሚችል ተስፋ ተጥሎበታል።
ትራምፕ በምርጫ ቅስቀሳ ወቅት "እኔ ከመጣሁ ጦርነት ይቆማል" ያሉትን ቃል በተግባር እያሳዩ ይመስላል። የኢራን መሪዎች ለትራምፕ ጥያቄ እንዲህ ያለ አዎንታዊ ምላሽ መስጠታቸው፣ ከትራምፕ ጋር በጠረጴዛ ዙሪያ ለመደራደር ያላቸውን ፍላጎት ያሳያል። ይህ "የድርድር ጥበብ" (Art of the Deal) ውጤት ይሆን?
ዲፕሎማሲው ከጦርነቱ ድምጽ ይልቅ እያየለ ነው!
#getu #breakingnews #trumpiran #hostagerelease #diplomacy #humanrights #artofthedeal #middleeastpeace #trumpnews #ትራምፕ #ኢራን #ዲፕሎማሲ #ሰበርዜና #ጌጡተመስገን #getutemesgen

ጦርነቱ በሰከንድ ልዩነት ቆመ!
አሜሪካና ኢራን ለሁለት ሳምንት ተኩስ አቆሙ!
* የሆርሙዝ ወሽመጥ ተከፈተ
#ethiopia | ዓለም እስትንፋሷን ይዛ በጠበቀችበት በዚያው የመጨረሻ ሰዓት፣ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በፓኪስታን ጠቅላይ ሚኒስትር ሸህባዝ ሻሪፍ ጥያቄ መሰረት በኢራን ላይ ሊሰነዝሩት የነበረውን "ሥልጣኔ አጥፊ" ጥቃት ለሁለት ሳምንት አግደዋል።
የሆርሙዝ ወሽመጥ ተከፈተ
ኢራን ወሳኙን የሆርሙዝ ወሽመጥ ለሁለት ሳምንት ክፍት ለማድረግ ተስማምታለች። ይሁን እንጂ በወሽመጡ ለሚያልፉ መርከቦች ለእያንዳንዳቸው 2 ሚሊዮን ዶላር "የማለፊያ ታሪፍ" (Transit Fee) ከኦማን ጋር በመሆን እንደምታስከፍልና ገንዘቡንም ለሀገር መልሶ ግንባታ እንደምትጠቀም ተገልጿል።
የእስላማባድ ንግግር (The Islamabad Talks)፦ በመጪው አርብ (ሚያዝያ 10) በፓኪስታን መዲና እስላማባድ የአሜሪካና የኢራን ልዑካን ፊት ለፊት ተገናኝተው ዘላቂ ሰላም ላይ ይደራደራሉ። በንግግሩ ላይ የትራምፕ ልዩ መልዕክተኞችና ምናልባትም ቪፒ ጄዲ ቫንስ ሊገኙ እንደሚችሉ ተገምቷል።
የሁለቱ ወገኖች ፉክክር፦ ዋይት ሃውስ "ይህ የአሜሪካ ድል ነው" ሲል፣ ኢራን በበኩሏ "አሜሪካን የ10 ነጥብ የሰላም እቅዳችንን እንዲቀበል አስገዳጅ ድል ተቀዳጅተናል" በማለት ደስታቸውን በቴህራን አደባባይ እየገለጹ ነው።
ያልተፈታው ስጋት፦r
ምንም እንኳ አሜሪካና ኢራን ተኩስ ቢያቆሙም፣ እስራኤል ግን በኢራን ላይ የምታደርገውን ጥቃት አሁንም እንደቀጠለች መሆኑ ተሰምቷል። "ጥቃቴን የምቀጥልባቸው ተጨማሪ ኢላማዎች አሉኝ" በማለት ፍጥጫው ገና እንዳልበረደ አመልክታለች።
#getu #breakingnews #usiranceasefire #trump #hormuzstrait #islamabadtalks #middleeastpeace #oilprices #globalsecurity #አሜሪካ #ኢራን #ሰበርዜና #ተኩስአቁም #ትራምፕ #ጌጡተመስገን #getutemesgen

6 months ago
"ከጦርነት የሚያተርፍ ሰይጣን ብቻ ነው"
#ethiopia | የኢራኑ ፕሬዚዳንት መሱድ ፓዜሽኪያን የገልፍ ሀገራት ችግሮቻቸውን በጋራና በውይይት እንዲፈቱ ጥሪ አቀረቡ። ፕሬዚዳንቱ ይህን ያሉት አሜሪካ ሁለተኛ የጦር አውሮፕላን ተሸካሚ መርከቧን ወደ ቀጠናው እንደምትልክ ይፋ ባደረገች ማግስት መሆኑ ልዩ ትኩረት ሰጥቶታል።
በኢራን በተካሄደ የኢንቨስትመንት ኮንፈረንስ ላይ ንግግር ያደረጉት ፓዜሽኪያን፣ በቀጠናው የውጭ ሀገራት ጣልቃ ገብነት እንደማያስፈልግ በአጽንኦት ተናግረዋል።
የንግግሩ ዋና ዋና ነጥቦች፦
* የሰላም አስፈላጊነት፦ "የትኛውም ሀገር ከጦርነት አያተርፍም" ያሉት ፕሬዚዳንቱ፣ ጦርነትና ግጭትን በማስወገድ ሰላምና መረጋጋትን ማስፈን እንደሚገባ አሳስበዋል።
* አብሮ መስራት፦ ዓለም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጠበበች መምጣቷን በመጥቀስ፣ ሀገራት በጋራ መስራትና ችግሮችን በምክክር መፍታት እንዳለባቸው ገልጸዋል።
* የውጭ ጣልቃ ገብነት፦ በቀጠናው የሚከሰቱ አለመግባባቶች በራሳቸው በገልፍ ሀገራት እንጂ በውጭ ኃይሎች መፈታት እንደሌለባቸው ጠቁመዋል።
የፕሬዚዳንቱ ንግግር ኢራን በቀጠናው ያለውን ወታደራዊ ውጥረት ለማርገብና ዲፕሎማሲያዊ አማራጮችን ለመጠቀም ያላትን ፍላጎት የሚያሳይ ነው ተብሏል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #ኢራን #መሱድፓዜሽኪያን #የገልፍሀገራት #ሰላም #ዲፕሎማሲ #middleeastpeace #iran #internationalnews #አውሮፓ

Comments