ኳሷ አሁን በአሜሪካ ሜዳ ላይ ናት - ኢራን
********************
የኢራን ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ካዘም ጋሪባባዲ በሰጡት መግለጫ፣ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ጦርነት በዘላቂነት ለመቋጨት የሚያስችል አዲስና ሁሉን አቀፍ የሰላም ዕቅድ በመካከለኛዋ ፓኪስታን በኩል ለአሜሪካ ማቅረባቸውን አስታውቀዋል።
ጋሪባባዲ "አሁን ኳሷ በአሜሪካ ሜዳ ላይ ናት፤ ዋሽንግተን በዲፕሎማሲያዊ መፍትሔ እና በግጭት ቀጣይነት መካከል መምረጥ ይኖርባታል" ሲሉ ገልጸዋል።
የኢራን መገናኛ ብዙኃን እንደዘገቡት፣ ይህ ባለ 14 ነጥብ የሰላም ዕቅድ ቀደም ሲል አሜሪካ ላቀረበችው ባለ 9 ነጥብ ሰነድ እንደ አጸፋዊ ምላሽ የቀረበ ሲሆን፤ የደኅንነት ዋስትናን፣ የአሜሪካ ጦር ከቀጣናው እንዲወጣ፣ ማዕቀቦች እንዲነሱ እና በሊባኖስ ያለውን ጨምሮ ጦርነቱ በሁሉም ግንባሮች እንዲቆም የሚሉ ጥያቄዎችን አካትቷል።
በተጨማሪም ኢራን አሜሪካ ካሳ እንድትከፈላትና ለሆርሙዝ ሰርጥ አዲስ የሥራ ማዕቀፍ እንዲበጅ ፍላጎት እንዳላት ተገልጿል።
ይሁን እንጂ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በ"ትሩዝ ሶሻል" ገጻቸው ባሰፈሩት መልእክት፣ ዕቅዱን በቅርቡ እንደሚመለከቱት ቢገልጹም "ተቀባይነት ይኖረዋል ብዬ መገመት አልችልም" ሲሉ ጥርጣሬያቸውን አንጸባርቀዋል።
ትራምፕ ቀደም ሲል ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ በኢራን ውሎች እንዳልረኩና “በከባድ ወታደራዊ እርምጃ እናጠፋቸዋለን" ሲሉ ማስፈራራታቸው ይታወሳል።
አሜሪካ ኢራን የኒውክሌር መርሐ ግብሯን ሙሉ በሙሉ እንድታቆም ብትጠይቅም ቴህራን ግን “ፕሮግራሜ ለሰላማዊ ዓላማ ብቻ ነው” በማለት ጥያቄውን ውድቅ አድርጋዋለች።
ይህ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው አለመግባባት በሳምንቱ የነዳጅ ዋጋ ከ2022 ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ በአንድ በርሜል ከ120 ዶላር በላይ እንዲጨምር ምክንያት ሆኗል።
በጌቱ ላቀው
#iran #usa #peacetalks #donaldtrump #middleeast #geopolitics #hormuz #oilprices

1 month ago