Logo
Getu Temesgen
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ማስጠንቀቂያ
ፈቃድ በሌላቸው ድርጅቶች ገንዘብ መላክ ወንጀል ነው!
#ethiopia | ​የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በሕጋዊ መንገድ የገንዘብ ማስተላለፍ ፈቃድ ያላቸውን 23 ድርጅቶች ዝርዝር ዛሬ ይፋ አድርጓል።

ባንኩ ፈቃድ በሌላቸው መንገዶች ገንዘብ መላክም ሆነ መቀበል በሕግ እንደሚያስጠይቅ ጥብቅ ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል።

​ፈቃድ ያላቸው ዋና ዋና ድርጅቶች ዝርዝር፦

✅ አቢሲኒያ ረሚት (Abyssinia Remit)
✅ አፍሪካ ኤክስቼንጅ (Africa Exchange)
✅ አላንሳሪ ኤክስቼንጅ (Alansari Exchange)
✅ አሪፍ ረሚት (Arif Remit)
✅ ብር-ሊንክ ረሚታንስ (Birr-Link Remittance)
✅ ቦሌ አትላንቲክ ኢንተርናሽናል (Bole Atlantic)
✅ ቦቲም መኒ ቴክኖሎጂ (Botim Money Technology)
✅ ካሽ ኤክስፕረስ (Cash Express)
✅ ደሃብሽል (Dahabshiil)
✅ ኢትዮ ሶሊሽንስ (Ethio Solutions) ... እና ሌሎችም (በድምሩ 23 ድርጅቶች)።
​
ፈቃድ በሌላቸው ድርጅቶች ገንዘብ መላክ በ "ሕገ-ወጥ መንገድ በተገኘ ገንዘብ" (Money Laundering) እንደመሳተፍ የሚቆጠር ከባድ ወንጀል ነው።

​ በሕገ-ወጥ ዝውውር ላይ የሚገኙ ገንዘቦች በመንግሥት የመወረስ ዕድላቸው ከፍተኛ ነው።
​
ሕገ-ወጥ ዝውውር የሀገሪቱን የውጭ ምንዛሬ ክምችት በማዳከም የኑሮ ውድነት እንዲባባስ ያደርጋል።
​
በውጭ የምትኖሩ ወገኖቻችንም ሆናችሁ እዚህ ሀገር ውስጥ ገንዘብ የምትቀበሉ፣ ራሳችሁን ከሕግ ተጠያቂነት ለመጠበቅና ለሀገራችሁ ዕድገት የበኩላችሁን ለመወጣት ሁልጊዜም ሕጋዊ የገንዘብ ማስተላለፊያ መንገዶችን ብቻ ተጠቀሙ።

​#getu #nationalbankofethiopia #remittanceethiopia #legalmoneytransfer #moneylaunderingawareness #ethiopiaeconomy #dahabshiil #abyssiniaremit #arifremit #financeethiopia #ብሔራዊባንክ #ገንዘብዝውውር #ሕጋዊ #ኢትዮጵያ #ጌጡተመስገን #getutemesgen

6 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.