24 days ago
የኢትዮጵያ የውጭ ምንዛሪ ክምችት ከሪፎርሙ በፊት ከነበረው በ20 እጥፍ አድጓል
**********************
የውጭ ምንዛሪ መጠባበቂያ ክምችት በ2018 በጀት ዓመት ከፍተኛ ጭማሪ በማሳየት መጠኑ ከማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው በፊት ከነበረው በ20 እጥፍ ማደጉን የገንዘብ ፖሊሲ ኮሚቴ አስታውቋል።
ኮሚቴው ከ7ኛ ስብሰባው በኋላ በሰጠው መግለጫ እንዳብራራው፥ በሐምሌ ወር 2016 ተግባራዊ ከተደረገው ሁሉን አቀፍ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ማግስት ሀገራችን በአጠቃላይ የውጭ ኢኮኖሚ ሚዛን ትርፍ ማስመዝገብ ችላለች።
ይህም ከሪፎርሙ በፊት ከነበረው ጉድለት አንፃር ሲታይ ዘርፉ ከፍተኛ መሻሻል ላይ መሆኑን ያመላክታል።
አጠቃላይ የማሻሻያ እርምጃዎቹ የውጭ ገበያ ተወዳዳሪነትን እና የውጭ ምንዛሪ ገቢን በማሳደግ የውጭ ኢኮኖሚ ዘርፉን ዘላቂነት እያረጋገጡ መሆኑ ተገልጿል።
በበጀት ዓመቱ የተመዘገበው የሸቀጦች ወጪ ንግድ ገቢ በሶስት እጥፍ ማደግ፣ እንዲሁም በግለሰቦች እና በመንግሥት የሃዋላ ፍሰት ላይ የታየው አበረታች መሻሻል የሸቀጦች ገቢ ንግድ መጨመርን በከፊል እንዲያካክስ ረድቶታል።
በዚህም የተነሳ በ2016 በጀት ዓመት 6.2 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ደርሶ የነበረው የሂሳብ ሚዛን ጉድለት በ2018 በጀት ዓመት ወደ 1.8 ቢሊዮን ዶላር በከፍተኛ ሁኔታ ሊቀንስ መቻሉ በመግለጫው ተጠቁሟል።
በተጨማሪም በበጀት ዓመቱ የተመዘገበው የካፒታል ሂሳብ ትርፍ ለአጠቃላይ የክፍያ ሚዛኑ መሻሻል የጎላ አስተዋፅዖ ማበርከቱ ተገልጿል።
ኮሚቴው የዓለም አቀፉን የገንዘብ ድርጅት (IMF) የሐምሌ 2018 ትንበያ ዋቢ በማድረግ እንደገመገመው፣ በመካከለኛው ምሥራቅ የተከሰተው ግጭት ቀደም ሲል ሲጠበቅ የነበረው የተረጋጋ የዓለም ኢኮኖሚ አቅጣጫ እንዲዛባ አድርጓል።
በመሆኑም ዓለም አቀፍ ዕድገት በ2026 ወደ 3.0 በመቶ እንደሚቀንስ እና በ2027 ደግሞ መጠነኛ መሻሻል በማሳየት 3.4 በመቶ እንደሚሆን ተተንብዮአል።
በተመሳሳይ፣ አጠቃላይ የዓለም የዋጋ ግሽበት በ2026 ወደ 4.7 በመቶ ጭማሪ ካሳየ በኋላ በ2027 ወደ 3.9 በመቶ ይቀንሳል ተብሎ የሚጠበቅ ቢሆንም፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ የአለመረጋጋት ስጋቶች አሁንም ድረስ መቀጠላቸውን ኮሚቴው አስገንዝቧል።
#ethiopia #ebc #nationalbankofethiopia #foreignexchange #economicreform #macroeconomics #exportgrowth #imf #globaleconomy

1 month ago
በታሪካችን ለመጀመሪያ ጊዜ፣ የኢንዱስትሪ ዘርፍ አጠቃላይ የሀገር ውስጥ ምርት ድርሻ ከግብርና እና ከአገልግሎት በልጧል - ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር)
**************************
የብሔራዊ ባንክ ገዢ ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) ኢትዮጵያ ታከናውናለች በሚል መሪ ቃል በተደረገው መድረክ ላይ፣ የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ማሻሻያ በፋይናንስ፣ በወጪ ንግድ እና በኢንዱስትሪ ዘርፎች ያመጣውን አስደናቂ ሀገራዊ ለውጥ በዝርዝር አቅርበዋል።
የኢኮኖሚ ዕድገቱ ወደ ተከታታይ የሥራ ዕድል ፈጠራ መሸጋገሩን የገለፁት ዶ/ር ኢዮብ፣ ዘንድሮ ብቻ በተለያዩ ዘርፎች 4.9 ሚሊዮን አዳዲስ የሥራ ዕድሎች መፈጠራቸውን ጠቅሰዋል።
ከዚህም ጋር ተያይዞ የኢንዱስትሪው አቅም አጠቃቀም ከ49 በመቶ ወደ 66.3 በመቶ ማደጉን፣ ይህም በኢትዮጵያ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የኢንዱስትሪው ዘርፍ አጠቃላይ የሀገር ውስጥ ምርት (GDP) ድርሻ ከግብርና እና ከአገልግሎት ዘርፎች መብለጡን አብስረዋል።
የተደረገው የውጭ ምንዛሬ ተመን ማሻሻያም በወጪ ንግድ ዘርፍ የኢትዮጵያን ተወዳዳሪነት በከፍተኛ ደረጃ እንዳሳደገው ዶ/ር ኢዮብ አብራርተዋል።
በዚህም፣ የወጪ ንግድ በ2010 ዓ.ም ከነበረበት 2.83 ቢሊዮን ዶላር ባለፈው ዓመት ወደ 8.33 ቢሊዮን ዶላር ማደጉንና ዘንድሮ ደግሞ 11 ቢሊዮን ዶላር ይደርሳል ተብሎ እንደሚጠበቅ አስታውቀዋል።
ይህ የወጪ ንግድ ዕድገት የዓለም አቀፍ ዋጋ መጨመር ውጤት ብቻ ሳይሆን፣ በፖሊሲ ለውጡ የመጣ መዋቅራዊ የኢኮኖሚ ሽግግር መሆኑንም ገልጸዋል።
የፋይናንስ ዘርፉን በተመለከተም፣ የባንክ ኢንዱስትሪው አጠቃላይ ሀብት ባለፉት 8 ዓመታት ውስጥ በ680 በመቶ፣ ተቀማጭ ገንዘብ ደግሞ በ654 በመቶ ማደጉን ተናግረዋል።
ይህን ተከትሎም 93.8 በመቶ የሚሆነው ብድር ለግል ዘርፉ እየቀረበ መሆኑ ሌላው ትልቅ ስኬት ነው ብለዋል።
ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለመንግሥት የልማት ድርጅቶች በሰጠው ብድር ምክንያት 845 ቢሊዮን ብር የማይመለስ ዕዳ ተሸክሞ ለቀውስ ተጋልጦ እንደነበር ያስታወሱት ዶ/ር ኢዮብ፣ መንግሥት በወሰደው እርምጃ ዕዳውን ወደ ሰነድ በማዞር እና ካፒታሉን በ3 እጥፍ በማሳደግ ባንኩን መታደግ መቻሉን አስረድተዋል።
በአሁኑ ሰዓት የባንክ ኢንዱስትሪው የተበላሸ ብድር ምጣኔ 3.07 በመቶ ብቻ ሲሆን፣ ይህም ብሔራዊ ባንክ ካስቀመጠው የ5 በመቶ ጣሪያ በታች መሆኑን አብራርተዋል።
የተደራረቡ ዓለም አቀፍ እና የሀገር ውስጥ ፈተናዎች ቢኖሩም፣ ኢኮኖሚው የመቋቋም አቅሙን የገነባ በመሆኑ ሀገራችን የአፍሪካ የብልጽግና ተምሳሌት ለመሆን በተገቢው መንገድ ላይ መሆኗን አረጋግጣለች ሲሉ ዶ/ር ኢዮብ ገልጸዋል።
በለሚ ታደሰ
#ethiopia #economicreform #industrialgrowth #exportgrowth #financesector #banking #ebc

2 months ago
ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን ከመተካት ባለፈ የወጪ ንግድ ገቢን እያሳደገ ያለው የኢትዮጵያ የግብርና ኢንቨስትመንት
*************
ኢትዮጵያ በአስር ዓመቱ የግብርና መሪ ዕቅድ ውስጥ በትኩረት እንዲሰራባቸው ካስቀመጠቻቸው ስትራቴጂካዊ ዘርፎች መካከል አንዱ የሆነው የግብርና ኢንቨስትመንት የምግብ ዋስትናን የማረጋገጥ፣ ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ የመተካት እና የውጪ ምንዛሪን የማሳደግ ሀገራዊ ግቦችን በላቀ ስኬት እያሳካ ይገኛል።
የሀገራችንን ሰፊ የግብርና አቅም በመጠቀም በርካታ የሀገር ውስጥና የውጭ ባለሃብቶች በስፋት ተሰማርተው ወደ ልማት ገብተዋል።
በአሁኑ ወቅት በሀገር አቀፍ ደረጃ በእርሻ ኢንቨስትመንት ብቻ ከ2 ነጥብ 3 ሚሊዮን ሄክታር በላይ መሬት በ8 ሺህ 904 ባለሀብቶች እጅ ላይ እንደሚገኝ የግብርና ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።
መንግሥት ይህንን ዘርፍ ይበልጥ ለማሳደግ በመሬት አቅርቦት፣ የፋይናንስ አገልግሎትን ተደራሽ በማድረግ፣ በውል እርሻ እና በመሰረተ-ልማት ማመቻቸት ረገድ በርካታ ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል።
ከዚህ በተጨማሪም የግብርናውን ዘርፍ ሽግግር የሚያፋጥኑ የሀገር በቀል ቴክኖሎጂዎችን ለባለሀብቶች የማስተዋወቅ ስራ በትኩረት እየተከናወነ ሲሆን ሀገራዊ ለውጡን ተከትሎ በተተገበሩ ዘመናዊ አሰራሮች፣ በኮንትራት እርሻ፣ በምርጥ ዘር ብዜት እንዲሁም በአካታች የሕግ ማዕቀፎች ምክንያት አመርቂ ውጤቶች እየተመዘገቡ ነው።
በአሁኑ ወቅት አበባ፣ አትክልት፣ ፍራፍሬ፣ ሰብል እና እንስሳት በኢንቨስትመንት ደረጃ በስፋት እየለሙ ለሀገር ውስጥ ፍጆታና ለወጪ ንግድ በከፍተኛ ደረጃ እየቀረቡ ይገኛሉ።
ለአብነትም የአበባ፣ የአትክልት እና የፍራፍሬ የወጪ ንግድ አፈፃፀምን ስንመለከት በ2013 ዓ.ም ከ309 ሺህ 866 ነጥብ 8 ቶን ምርት 531 ሺህ 480 ዶላር ተገኝቷል።
ይህ ቁጥር በ2017 ዓ.ም እጅግ ከፍተኛ ዕድገት በማሳየት ከተላከው 395 ሺህ 911 ነጥብ 9 ቶን ምርት 670 ሺህ 627 ነጥብ 4 ዶላር ገቢ ለማግኘት ተችሏል።
የዘንድሮውን የ10 ወራት አፈፃፀም ስንመለከት ደግሞ ከ236 ሺህ 415 ነጥብ 3 ቶን ምርት 408 ነጥብ 2 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ማግኘት መቻሉን የሚኒስቴሩ መረጃ ያረጋግጣል።
በሌላ በኩል ለሀገራዊ ኢኮኖሚ፣ ለስራ እድል ፈጠራ እና ለእውቀት ሽግግር ከፍተኛ አስተዋፅዖ ያለው የእንስሳት ኢንቨስትመንትም ሌላው ትኩረት የተሰጠው ዘርፍ ነው።
ባለፉት አምስት ዓመታት ብቻ በእንስሳት ኢንቨስትመንት ለተሰማሩ ባለሀብቶች 112 ሺህ ሄክታር መሬት፣ በእርሻና ሆርቲከልቸር ኢንቨስትምንት ደግሞ 643 ሺህ ሄክታር መሬት በድምሩ ከ750 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት ተላልፎ ለልማት እንዲውል ተደርጓል።
#agricultureinvestment #ethiopianeconomy #importsubstitution #exportgrowth #ethiopianbroadcastingcorporation

Comments