#mekelle
የታጠቁ የትግራይ ኃይሎች ዛሬ ከጥዋት አንስቶ በመቐለ የሚገኘውን የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት ፅ/ቤትን ከበው ሰራተኞች እና ተሽከርካሪዎች እንዳይገቡ ፣ በአካባቢው ተሽከርካሪዎች እንዳይንቀሳቀሱ አግደው እንደነበር ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለማወቅ ችሏል።
ብሬን ፣ ክላሽ የታጠቁት ኃይሎች ከጥዋት አንስተው ወደ ፅ/ቤቱ የሚወስደውን መንገድ በመዝጋት ፣ ዙሪያውን በመክበብ፣ የትራንስፖርት እንቅስቃሴ እንዳይኖር አድርገው አርፍደዋል።
ሰራተኞችና ተሽከርካሪዎች እንዳይገቡ ከውስጥም ሰው እንዳይወጣ፣ ወደ ስፍራው ሰው እንዳይጠጋ በመከልከላቸው የፅ/ቤቱ ሰራተኞች ውጭ ላይ ቆመው እንደነበር ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከአይን እማኞች ተረድቷል።
ቃላቸውን የሰጡን ነዋሪዎች እንቅስቃሴው የነበረው የፕሬዜዳንት ፅ/ቤት አካባቢ ብቻ እንደነበር ከዛ ውጭ ከተማው ሙሉ ሰላም እንደሆነ ገልጸዋል።
ከግማሽ ሰዓት በፊት ታጣቂዎቹ አካባቢውን ክፍት ማድረጋቸው፣ ሰራተኞችም ወደ ስራ መግባታቸው ፣ መንገዶች ለትራንስፖርት እንቅስቃሴ ክፍት መደረጋቸውን ለማወቅ ችለናል።
የታጣቂዎቹ እንቅስቃሴ ከዚህ ቀደም ከነበረው የደመወዝ እና ሌሎች ተያያዥ ጥያቄዎች ጋር የተገናኘ ነው።
ከሰዓት በኃላ የሚሰጥ መግለጫ ካለ ተከታትለን እናቀርባለን።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
@tikvahethiopia

10 months ago