1 month ago
የሰው ልጅ ይሞታል እነሱ ግን "የማይሞቱ" ሰዎቻችን ናቸው!
#ethiopia | ጣሊያኖች አንድ ሰው ለሀገሩ እና ለዓለም ባበረከተው ድንቅ ስራ ምክንያት አሻራው ትውልድ ተሻጋሪ ሲሆን “የማይሞት ሰው” በማለት ያከብሩታል።
በጣሊያን ባህልና ታሪክ ውስጥ ለሀገራቸው እንዲሁም ለዓለም ታላቅ ውርስ ጥበብ እና እውቀት አበርክተው ያለፉ ታላላቅ ሰዎች “የማይሞቱ” ተብለው በክብር ስም ይጠራሉ።
እነዚህ ሰዎች በስጋ ቢለዩም፣ ያከናወኗቸው አስደናቂ ስራዎች ትውልድ ተሻጋሪ በመሆናቸው እስከዛሬ ድረስ ስማቸው ሳይደብዝዝ ህያው ሆኖ ይኖራል።
በዓለም እና በጣሊያን ታሪክ ውስጥ ይህንን “የማይሞት” የሚል የክብር ስም ካተረፉ ታላላቅ ሰዎች መካከል እነዚህ ይገኙበታል።
የሞናሊዛ (Mona Lisa) ስዕል ፈጣሪ፣ ድንቅ መሃንዲስ እና የህክምና ሳይንስ አቅኚ የነበረው ሊዮናርዶ ዳቪንቺ በጥበቡ ዓለምን ያሰደመመ ምሁር ይህንን የክብር ስም የተሰጠው ሰው ነው።
የዘመናዊው የጣሊያን ቋንቋ አባት እና የዓለም የስነ ጽሁፍ ሀብት የሆነው “ዲቫይን ኮሜዲ” ደራሲ ዳንቴ አሊጊየር ሌላኛው ነው።
የቫቲካኑን ሲስቲን ቻፔል ድንቅ ስዕሎች እና የዳዊትን ሀውልት ያነጸው ወደር የሌለው የቅርጻ ቅርጽ ባለሙያው ሚካኤል አንጀሎ የክብር ስሙን ከተቀዳጁት ሰዎች መካከል ይገኝበታል።
የዘመናዊ ኮስሞሎጂ እና የፊዚክስ አባት የሰማይ አካላትን በቴሌስኮፕ በመመርመር የዓለምን አስተሳሰብ የለወጠው ታላቁ ሳይንቲስት ጋሊሊዮ ጋሊሊም የክብር ስሙ የተሰጠው ሰው ነው።
እንደዚሁም በጣሊያን እግር ኳስ ታሪክ ውስጥ እጅግ ስኬታማ የነበረውን የ1980ዎቹ መጨረሻ እና የ1990ዎቹ መጀመሪያ የኤሲ ሚላን ቡድን አሰልጣኝ አሪጎ ሳኪ እና ተጫዋቾቹን እንደ ማልዲኒ ባሬሲና ቫን ባስተን ያሉ ተጫዋቾችም ጣሊያኖች "የማይሞቱት"ሰዎች ብለው ይጠሯቸዋል።
“ሰው ይሞታል፤ ስራ እና አሻራ ግን ለዘላለም ህያው ሆኖ ይኖራል!”
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#ethiopia #getutemesgen #italian #scientists #gliimmortali #history #inspiration #knowledge

"የፕሪሚየር ሊጉ ክለቦች አራቱን የአውሮፓ ታላላቅ ሊጎች በድምር በለጡ!"
#ethiopia | የዝውውር መስኮቱ የፕሪሚየር ሊጉ ክለቦች 4.5 ቢሊዮን ዶላር ያፈሰሱበት የታሪክ ውዱ የዝውውር መስኮት ሆኖ ተጠናቀቀ።
የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ2026 የክረምት የተጫዋቾች ዝውውር መስኮት በይፋ ሲጠናቀቅ የሊጉ ክለቦች በታሪክ ታይቶ የማይታወቅ ከፍተኛ የገንዘብ ወጪ በማድረግ አዲስ ሪከርድ አስመዝግበዋል።
የፕሪሚየር ሊጉ 20 ክለቦች በአጠቃላይ ወደ 4.5 ቢሊዮን ዶላር ለተጫዋቾች ዝውውር ፈሰስ አድርገዋል።
የዝውውር መስኮቱ በተዘጋበት የመጨረሻ ዕለት ብቻ ክለቦች 627 ሚሊዮን ዶላር ወጪ አድርገዋል።
ክለቦቹ በ2025 የውድድር ዓመት ለተጫዋቾች ዝውውር ያወጡት አጠቃላይ የገንዘብ መጠን 4.1 ቢሊዮን ዶላር እንደነበረ ቢቢሲ ገልጿል።
በዝውውር መስኮቱ ማንችስተር ሲቲ ከ600 ሚሊዮን ዶላር በላይ በማውጣት በሊጉ ከፍተኛ ወጪ ያወጣ ክለብ ሆኗል።
ቶተንሀም 400 ሚሊዮን ዶላር በማውጣት ከሲቲ በመቀጠል በሊጉ ከፍተኛ ወጪ ያወጣ ክለብ ነው።
ሊቨርፑል 280 ሚሊዮን ዶላር እንዲሁም አርሰናል 270 ሚሊዮን ዶላር በማውጣት በቅደም ተከተል በዝውውሩ ከፍተኛ ወጪ ያወጡ ክለቦች ሆነዋል።
ኤንዞ ፈርናንዴዝ ከቼልሲ ወደ ማንችስተር ሲቲ በ125 ሚሊዮን ዮሮ ያደረገው ዝውውር የመስኮቱ ውዱ ዝውውር ተብሏል።
የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ክለቦች ያወጡት አጠቃላይ ወጪ ከሌሎቹ አራት የአውሮፓ ታላላቅ ሊጎች (ስፔን፣ ጣሊያን፣ ጀርመን እና ፈረንሳይ) በድምር ካወጡት ወጪ ይበልጣል ተብሏል።
እነዚህ አራቱ ሊጎች በዝውውሩ ያወጡት አጠቃላይ ወጪ 3.8 ቢሊዮን ዶላር ነው።
ይህ አሀዝ አሁንም የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የፋይናንስ የበላይነት በድጋሚ የተረጋገጠበት የዝውውር መስኮት ሆኖ ተጠናቋል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#ethiopia #getutemesgen #english #spain #germany #italian #premierleague #summer #transfer #clubs #financial #history #record

3 months ago
በኢትዮጵያ እና በጣሊያን መካከል ያለውን የንግድ፣ የኢንቨስትመንት እና የዲዛይን ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር ያለመው ከፍተኛ የቢዝነስ እና የዲዛይን ኹነት በኢትዮጵያ ሳይንስ ሙዚየም ሊካሄድ ዝግጅቱ ተጠናቋል።
📅 የሁነቱ መርሃ-ግብር
ቀን፦ከሰኔ 30 እስከ ሐምሌ 2 ቀን 2018 ዓ.ም (እ.ኤ.አ ከጁላይ 7 እስከ 9 ቀን 2026
*ቦታ፦በአዲስ አበባ፣ የኢትዮጵያ ሳይንስ ሙዚየም
✨ በሁነቱ ላይ ምን ምን ይጠበቃል?
🛍️ ልዩ ኤግዚቢሽን እና የB2B ትስስር
ከፍተኛ ጥራት ያላቸው የጣሊያን የቤት ዕቃዎች (Furniture)፣ የሥነ-ሕንጻ ብርሃን ቴክኖሎጂዎች፣ ሴራሚክስ እና እብነበረድ የሚቀርቡበት ሲሆን፤ የሁለቱን ሀገራት ኩባንያዎች በቀጥታ የሚያገናኝ የንግድ ትስስር መድረክ ተዘጋጅቷል።
🏗️ ሙያዊ ሴሚናሮች፦
በዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅና ባለው ‘Interni Magazine’ አወያይነት በዘላቂ የከተማ ልማት፣ በሃይል ቆጣቢ ህንፃዎች እና በኢትዮጵያ የሪል ስቴት ኢንቨስትመንት እድሎች ዙሪያ የሀገር ውስጥ፣ የጣሊያንና የቀጣናው (ሩዋንዳ እና ኡጋንዳ) ምሁራንና ጋዜጠኞች የሚሳተፉበት ውይይት ይደረጋል።
🎓 የዲዛይን ማስተር ክላስ እና ልዩ ውድድር፦
በታዋቂው አርክቴክት ዱቺዮ ግራሲ (Arch. Duccio Grassi) የሚመራ ልዩ የስልጠና መርሃ-ግብር የሚሰጥ ሲሆን፤ በታሪካዊው የመርካቶ የንግድ ቀጠና ላይ ያተኮረ የመርካቶ ከተማ መልሶ ማልማት ውድድር (Merkato Urban Regeneration Competition) በይፋ ይጀመራል።
🏛️ የMade in Italy” ታሪክ ትዕይንት
በአለም አቀፍ የ“Made in Italy” ቀን ምክንያት በማድረግ በጣሊያን የምርት መለያዎች ሙዚየም አማካኝነት ታዋቂ ብራንዶች ያለፉበትን የዲዛይን እድገት የሚያሳይ ልዩ ኤግዚቢሽን ለዕይታ ይቀርባል።
📌 ለተደራሲያን የቀረበ ማሳሰቢያ
ሁነቱ ለመጀመሪያዎቹ ቀናት ለባለሙያዎችና ለቢዝነስ ተቋማት (B2B) ብቻ ክፍት የሚሆን ሲሆን፤ በመጨረሻው ቀን ማለትም በሐምሌ 2 ቀን 2018 ዓ.ም (እ.ኤ.አ ጁላይ 9) ለማንኛውም ፍላጎት ላለው የህዝብ ክፍል እና ለዲዛይን አፍቃሪዎች ሙሉ በሙሉ ነፃ ሆኖ ክፍት ይደረጋል።
#italiansmart Living2026 #addisababa #ethiopia #italy #business #design #architecture #innovation
4 months ago
ቤተ ጉራጌ
እዣ : የኢንቨስትመንት ፀሐይ እየወጣላት ነው
#ethiopia | በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከ600 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገነባው አዲስ የብረት ማምረቻ ፋብሪካ በይፋ ተመረቀ
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በጉራጌ ዞን እዣ ወረዳ የቪታ ሳሉቲ ማኑፋክቸሪንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር የብረት ማምረቻ ፋብሪካ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ ባለሀብቶችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በድምቀት ተመርቋል።
የሀሮት ሪልስቴት እህት ኩባንያ የሆነው ቪታ ሳሉቲ ማኑፋክቸሪንግ ኃ/የተ/የግል ማኅበር መሥራችና ባለቤት አቶ ሰኢድ ኑሩ እንደተናገሩት "ቪታ ሳሉቲ የጣልያንኛ ቃል ሲሆን ሰላማዊ ሕይወት የሚል ትርጉም ይዟል። ሰላማዊ ሕይወት በቤተ ጉራጌ - ሰሜን፣ ደቡብ፣ ምዕራብና ምሥራቅ ኢትዮጵያ መልካም ምኞት ለመግለጥ ነው። የቤተ ጉራጌ አኗኗርም ለማመላከት ነው ብለዋል።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) በጉራጌ ዞን እዣ ወረዳ የሚገኘውንና የሀሮት ሪል ስቴት እህት ኩባንያ የሆነውን ቪታ ሳሉቲ ማኑፋክቸሪንግ ኃ/የተ/የግል ማህበር ፋብሪካን በዛሬው ዕለት በይፋ መርቀው ሥራ አስጀምረዋል።
አያይዘውም "ኢንቨስትመንትን በማስፋፋት ለዜጎች የሥራ ዕድል በመፍጠር ረገድ የግል ባለሀብቱ ሚና የላቀ ነው!" ሲሉ አወድሰዋል።
የቪታ ሳሉቲ ማኑፋክቸሪንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ፋብሪካ ከ600 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ የካፒታል ወጪ የተገነባ ሲሆን፣ ዘመናዊ ቴክኖሎጂን በመጠቀም የተለያዩ መጠንና ቅርጽ ያላቸው የትቦላሬና የላሜራ ብረት 22 ምርቶችን በከፍተኛ ጥራት የማምረት አቅም አለው።
አቶ ሰኢድ ኑሩ ንግግር "ይህ ፕሮጀክት ከህልም ወደ እውነት፣ ከሀሳብ ወደ ተግባር የተቀየረ ነው። ሀገራት የሚበለጽጉት በተፈጥሮ ሀብታቸው ብቻ ሳይሆን ራዕይን ወደ ተግባር በሚቀይሩ ባለሀብቶችና በሥራ ፈጣሪ ዜጎች ነው!" ብለዋል።
አቶ ሰኢድ አያይዘውም የቪታ ሳሉቲ ማኑፋክቸሪንግ ከህልም ወደ እውነት ከሀሳብ ወደ ተግባር የተቀየረ ለክልሉ ብሎም ለሀገሪቱ ኢኮኖሚ የሚኖረው ድርሻ የላቀ ነው። ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በመተካት የሀገርን የውጭ ምንዛሬ ያድናል ሲሉ አብስረዋል።
ኢንጂነር ናሆም መገርሣ በ5,000 ካሬ ላይ የሚገኘው ፋብሪካ በአሁኑ ወቅት ለ123 ዜጎች ቋሚ የስራ ዕድል የፈጠረ ሲሆን፣ ለበርካታ የአካባቢው ነዋሪዎችም ተዘዋዋሪ የስራ ዕድሎችን በማመቻቸት ለቀጣናው የኢኮኖሚ እድገት የጎላ አስተዋጽኦ ያበረክታል ብለዋል።
የቪታ ሳሉቲ ማኒፋክቸሪንግ ሥራ አስኪያጅ አቶ ዮሴፍ ፋብሪካው በዞኑ የመጀመሪያው የብረት ፋብሪካ መሆኑን አስረድተዋል።
ቪታ ሳሉቲ ማኑፋክቸሪንግ በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ አካባቢዎች ጥራታቸውን የጠበቁ የመኖሪያ አፓርትመንቶችን በመገንባትና በማስረከብ ከሚታወቀው የሀሮት ሪል እስቴት ጋር እህት ኩባንያ ነው።
ሀሮት ሪል እስቴት በተመጣጣኝ ዋጋ ጥራት ያላቸውን ቤቶች ለህብረተሰቡ በማቅረቡ የኢትዮ ህይ 2025 የሪል እስቴት አዋርድ አሸናፊ መሆኑ ይታወሳል።
የፋብሪካው አመራሮች ለዚህ ስኬት መገኘት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ላበረከቱት የክልልና የዞን የስራ ኃላፊዎች፣ ለወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ፣ ለኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት፣ ለቲናው አበባ ልማት አክሲዮን ማህበር፣ ለባለሙያዎች እንዲሁም ለቤተሰቦቻቸው ከልብ የመነጨ ምስጋና አቅርበዋል።
የሀሮት ሪል ስቴት የማርኬቲንግ ኃላፊ ፋንትሽ ሸዋ እንደገለጹት፤ ቪታ ሳሉቲ ማኑፋክቸሪንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር የሀሮት ሪል ስቴት እህት ኩባንያ ነው። ተቋሙ ከተመሰረተ 4ኛ ዓመቱን እያከበረ መሆኑን የጠቆሙት ኃላፊዋ፤ ድርጅቱ ለደንበኞቹ በገባው ቃል መሠረት በቦሌ ቡልቡላ ያስገነባቸውን የመኖሪያ ቤቶች በይፋ አስረክቧል።
በተጨማሪም ከሁለት ወር እስከ አንድ ዓመት ባለው አጭር ጊዜ ውስጥ በመስቀል ፍላወር፣ በሀያት ፈረስ ቤት እና በቦሌ ቡልቡላ አካባቢዎች የሚገነቡ ተጨማሪ ቤቶችን ለተጠቃሚዎች እንደሚያስረክብ አስታውቀዋል።
ሀሮት ሪል ስቴት በተመጣጣኝ ዋጋ ጥራት ያላቸውን ቤቶች ለገበያ በማቅረቡ በፈረንጆቹ 2025 በተካሄደው የኢትዮ ሪል ስቴት ሽልማት መርሃ ግብር ላይ በጥራትና በዋጋ አቅርቦት የአሸናፊነት ክብርን ያገኘ ድርጅት መሆኑ አብራርታለች።
ቪታ ሳሉቲ ማኑፋክቸሪንግ ኃ/የተ/የግል ማኅበር በኢንዱስትሪ፣ በኮንስትራክሽን፣ በሆቴልና በሌሎች የልማት ዘርፎች ላይ ኢንቨስትመንቱን ይበልጥ በማስፋፋት የሀገሪቱን የኢኮኖሚ ጉዞ ለመደገፍ ቁርጠኛ መሆኑን ገልጿል።
ባለሃብቱ አቶ ሰኢድ ይህ ስኬት የአንድ ሰው ጥረትና ውጤት ብቻ አይደለም። ከጀርባው ብዙ እጆች፣ ብዙ ዱአዎች እና ጸሎቶች፣ ብዙ ምክሮች ያሉበት ነው። በዚህ መሠረት ለማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት፣ ለኢንቨስትመንት ቢሮ፣ ለጉራጌ ዞን አስተዳደር፣ ለወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ፣ ለኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ለቲናው አበባ ልማት አ/ማሀበር ለሁሉም ባለድርሻ አካላት፣ ለባለሙያዎች እና ለሠራተኞቻችን ከልብ የመነጨ ምስጋና አቅርበዋል።
አቶ ሰኢድ የትምህርት ሕይወታቸውን እንዳጠናቀቁ በቀጥታ የተቀላቀሉት የንግዱን ዓለም ሲሆን፣ መጀመሪያ ላይ በመኪና መለዋወጫ ንግድ በመሰማራትና በመቀጠልም ወደ አስመጪና ላኪነት ዘርፍ በመሸጋገር ረጅም ዓመታትን አሳልፈዋል። በሂደትም የንግድ ሥራቸውን በማስፋት የጀመሩት የሪል ስቴት ኢንቨስትመንት ገና በጅማሮው ከፍተኛ የምስጋና ሽልማትና ዕውቅናን ሊያጎናጽፋቸው ችሏል። ባለሀብቱ በአሁኑ ወቅት ወደ ማኑፋክቸሪንግና ኢንዱስትሪ ዘርፍ በስፋት በመግባት ላይ ይገኛሉ።
በኢንቨስትመንት እንቅስቃሴያቸው ውስጥ ያጋጠማቸው የአስተዳደር ፈተና ስለመኖሩ ለቀረበላቸው ጥያቄ አቶ ሰይድ ሲመልሱ፣ ምንም ዓይነት ችግር እንዳልገጠማቸው በአጽንኦት ተናግረዋል። በአካባቢው የሚገኙ ከላይ እስከ ታች ያሉ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎችና የአስተዳደር አካላት አንድ ባለሀብት እውነተኛ አልሚ መሆኑን ከተረዱ አስፈላጊውን እገዛ እንደሚያደርጉ የገለጹት አቶ ሰይድ፣ ለእሳቸውም የተደረገላቸውን ተገቢውን ድጋፍና ትብብር በሙሉ አመስግነዋል።
የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ
"በዞናችን ኢንቨስት ለሚያደርጉ ባለሀብቶች ሁሉ ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር ዝግጁ ነን፣ በቁርጠኝነትም እንሠራለን! ... ዛሬ ኑ" ሲሉ ተደምጠዋል።
ርዕሰ መስተዳድሩ ዶ/ር እንዳሻው ጣሰው ፦ "የጉራጌ ማህበረሰብ በሀገሪቱ በሁሉም አካባቢዎች ከተሞችን በማልማትና ጠንካራ የንግድ ሥርዓት በመዘርጋት የሚታወቅ ቢሆንም፣ አሁን ላይ ባለሀብቶች ወደ አካባቢያቸው ተመልሰው በልማት እየሳተፉ መሆኑ እጅግ ያስደስታል። ይህ ፋብሪካ የሀገር ሀብት በመሆኑ ልንጠብቀው ይገባል። ሌሎች ባለሀብቶችም በክልሉ ኢንቨስት እንዲያደርጉ ጥሪ አቀርባለሁ።"ለአገርና ለሕዝብ መልዕክታቸውን አሰምተዋል።
በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ፕሬዝዳንት ዶክተር እንዳሻው ጣሰው፣ የክልሉ ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ፣ የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ እና የክልሉ ኢንቨስትመንትና ኢንዱስትሪ ቢሮ ኃላፊ ዶክተር አባስ መሀመድን ጨምሮ በርካታ የአመራር አካላት ተገኝተዋል።
"Vita, saluti, peace, life" blends Italian and English expressions of well-being, translating roughly to "life, greetings, peace, and life." This combination evokes a deep desire for a harmonious, healthy existence filled with good energy and wellness.
#manufacturing #factoryinauguration #centralethiopia #guragezone #investment #harotrealestate #vitasaluti #economicgrowth #realestate #housing #bolebulbula #homeownership #ethiopianbusiness #ኢንቨስትመንት #ሪልስቴት #ኢንዱስትሪ #ልማት #የሥራዕድል #ቢዝነስ #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

የኢትዮጵያ ታላቅ ወዳጅ:
የፕሮፌሰር ኮሎኔል ኤንሪኮ ፒዬሮ ቦሲ መታሰቢያ
* ጣሊያናዊ ምሁር፣ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ናቸው
* ባለቤታቸው ወይዘሮ ሳራ የማነ እና ከልጃቸው ካሌብ ጆርጂ ሌጋሲያቸውን ( Legacy ) ለማስቀጠል እየታተሩ ናቸው
#ethiopia | በአፍሪካና በኢትዮጵያ ለበርካታ ዓመታት በሕክምና ሙያቸው፣ በደራሲነታቸውና በሰብአዊ ድጋፍ ሥራዎቻቸው ደካማና ረዳት የሌላቸውን ወገኖች ሲረዱ የቆዩት ታዋቂው ጣሊያናዊ ምሁር ፕሮፌሰር ኮሎኔል ኤንሪኮ ፒዬሮ ቦሲ (ዶክተር) በተወለዱ በ81 ዓመታቸው ሰኔ 10 ቀን 2024 ዓ.ም. ተለይተውናል።
ፕሮፌሰሩ ለአርባ አምስት ዓመታት በዘለቀው ሙያዊ ሕይወታቸው በአርባ ሁለት የአፍሪካ ሀገራት እየተዘዋወሩ በበጎ ፈቃደኝነት የሕክምና አገልግሎት የሰጡ ሲሆን፣ በኦርቶፔዲክስ (የአጥንት) እና በዴርማቶሎጂ (የቆዳ) ሕክምና ስፔሻሊስት ነበሩ።
በሱዳን የሚገኘውን ትልቅ ሆስፒታል ጣሊያኖች በሚገነቡበት ወቅት ከፍተኛ የገንዘብ ፈንድ በማምጣት ረገድ የላቀ አስተዋጽኦ አበርክተዋል።
በሀገራችን ኢትዮጵያም ለሀያ ዓመታት ያህል ያገለገሉ ሲሆን፣ የአዳማ አጠቃላይ ሆስፒታልን በማቋቋም የመጀመሪያው ዳይሬክተር በመሆን ሰርተዋል።
በተጨማሪም በዳኑ ሆስፒታል፣ በአቤት ሆስፒታል ድንገተኛ አደጋ ክፍል በአጥንት ስፔሻሊስትነት የሰሩ ሲሆን፣ በየዓመቱ ከጣሊያን ወደ ወሊሶ ሆስፒታል እየመጡ ሰፊ የኦፕራሲዮን ሕክምና አገልግሎት በነፃ ይሰጡ ነበር።
ፕሮፌሰር ኤንሪኮ የሰውን ልጅ በዘር፣ በቋንቋ፣ በቆዳ ቀለምና በሃይማኖት የማይለዩ ፍፁም የሰብአዊነት ተምሳሌት ነበሩ። በአውሮፓ የኮሶቮ ጦርነት ወቅት የአንድ ዓመት ደሞዛቸውን በመተው በጦርነቱ መሃል በነፃ የሕክምና አገልግሎት የሰጡ ሲሆን፣ በኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ወቅትም በመጀመሪያዎቹ አምስት ጣሊያናውያን የሕክምና ባለሙያዎች ቡድን ውስጥ በመሆን በሄሊኮፕተር ወደ ስፍራው ያቀኑ ታላቅ ባለውለታ ናቸው።
በጣሊያን ሚላኖ "ናጋ" የተሰኘ የሕክምና ማዕከል በማቋቋምም አፍሪካውያንና የሌሎች ሀገራት ስደተኞችን፣ በተለይም የሕጋዊ ሰነድና የገንዘብ አቅም የሌላቸውን ወገኖች በነፃ ሲያክሙ ቆይተዋል።
ብዙዎች ስለ ሀገር ሲያነሱ "የአባት ሀገር" ወይም "የእናት ሀገር" ቢሉም፣ ፕሮፌሰሩ ግን ለኢትዮጵያ የነበራቸው ፍቅር ጥልቅ በመሆኑ ሁልጊዜም "የልጄ የካሌብ ሀገር" በማለት በኩራት ይገልጿት ነበር።
ስለ ኢትዮጵያ ታሪክ፣ ባህልና ወታደራዊ ታሪክ በርካታ ምርምሮችን ያደረጉት ፕሮፌሰሩ፣ በአጠቃላይ ከ46 በላይ መጻሕፍትን በኢንግሊዘኛና በጣሊያንኛ ቋንቋዎች አሳትመዋል።
ከእነዚህም መካከል "The History of Imperial Ethiopian Army" የተሰኘውና ለኢትዮጵያ ወታደራዊ ምርምር ማዕከል ያበረከቱት መጽሐፍ፣ "ደስታስ ይርስ ኤንድ ላይፍ 1892-1937" እና "Aethiopia la moneta Africana" የሚሉት ተጠቃሽ ናቸው። የቡና አመጣጥ ከኢትዮጵያ መሆኑን ለአለም ካስተዋወቁበት ስራቸው ባሻገር የዘመነ መሳፍንትን ፍፃሜ የሚያሳይ ታሪካዊ መጽሐፍ ይጠቀሳሉ።
እኝህ ታላቅ ምሁር ስኮላር፣ ዶክተር፣ የሚሊተሪ ኦፊሰር እና ደራሲ ብቻ ሳይሆኑ፣ በሚላኖ ካቶሊክ ዩኒቨርሲቲ "ትንሹ ልዑል" የተሰኘውን የሕጻናት መጽሐፍ በ55 ዓለም አቀፍ ቋንቋዎች በመተርጎም ያሳተሙ ተርጓሚና ድንቅ የቅብ ሥራዎችን ያበረከቱ ሰዓሊም ነበሩ።
ምንም እንኳን ሞት በድንገት ከሚወዷቸው ባለቤታቸው ወይዘሮ ሳራ የማነ እና ከልጃቸው ካሌብ ጆርጂ ቢለያቸውም፣ ያኖሩት ታላቅ አሻራ ግን ከመቃብር በላይ ሁሌም ሕያው ሆኖ ይኖራል።
ባለቤታቸውና ልጃቸው የፕሮፌሰሩን ውርስና ሌጋሲ ለማስቀጠል፣ እሳቸው ሳይታተሙ የተዉትንና ስለ ኢትዮጵያ ጉዳይ በአምስት መቶ አምስት መቶ ገጾች የተቀነበቡ ሁለት አዳዲስ መጻሕፍትን ለሕትመት ለማብቃት እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ።
ፕሮፌሰሩ ኢትዮጵያን የመወደዳቸው ምዕራፍ የተገለጠው፤ የተጀመረው በባለቤታቸውና በልጃቸው እንደሆነ ይናገሩ ነበር። በዚህ መሠረት ቤተሰቦቻቸው በኢትዮጵያ ምድር በስማቸው ሙዚየም ለመክፈት አልያም በእርሳቸው የተሰሩ ሥራዎችን እንዲሁም ልዩ ልዩ ቁሳቁሶችን ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ሙዚየም ለማበርከት ሰፊ እንቅስቃሴ ላይ ናቸው።
የፕሮፌሰር ኮሎኔል ኤንሪኮ ፒዬሮ ቦሲን ሕይወትና ሥራዎች ፤ ለአገርና ለሕዝብ ያበረከቱትን አስተዋጸኦ በክብር የሚዘክር ሥራ ከኢትዮጵያ ቅርስ ባለሥልጣን ይጠበቃል።
#ethiopiaheritage #italianscholar #enricopierobossi #ethiopianhistory #humanitarian #enricobossi #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa
Ethiopia’s Great Friend:
In Memory of Professor Colonel Enrico Piero Bossi
Italian scholar and human rights advocate
His wife, Mrs. Sara Yemane, and their son, Caleb Giorgi, are working to preserve and continue his legacy.
#ethiopia | The renowned Italian scholar, Professor Colonel Enrico Piero Bossi (M.D.), who dedicated many years of his life in Africa and Ethiopia through his medical profession, authorship, and humanitarian activities, helping vulnerable and disadvantaged communities, passed away at the age of 81 on June 17, 2024.
During his distinguished 45-year professional career, Professor Bossi volunteered medical services across 42 African countries. He was a specialist in Orthopedics (bone and musculoskeletal medicine) and Dermatology (skin medicine).
He made a significant contribution to securing major funding for the construction of a large hospital in Sudan built by Italian organizations.
In Ethiopia, where he served for nearly twenty years, he played a key role in establishing Adama General Hospital and served as its first director.
Additionally, he worked as an orthopedic specialist at Danu Hospital and in the Emergency Department of Abet Hospital. Every year, he traveled from Italy to Woliso Hospital, where he provided extensive surgical services free of charge.
Professor Enrico was a true symbol of humanity, treating all people equally regardless of race, language, skin color, or religion. During the Kosovo War in Europe, he gave up an entire year’s salary to provide free medical services in the war zone. Likewise, during the Ethio-Eritrean War, he was among the first five Italian medical professionals who flew by helicopter to the conflict area to provide humanitarian assistance.
In Milan, Italy, he founded the medical center known as “NAGA,” where he provided free healthcare services to African immigrants and migrants from other countries, particularly those lacking legal documentation or financial means.
While many people refer to their homeland as their “fatherland” or “motherland,” Professor Bossi’s love for Ethiopia was so profound that he proudly referred to it as “the country of my son, Caleb.”
A dedicated researcher of Ethiopian history, culture, and military history, Professor Bossi authored and published more than 46 books in English and Italian.
Among his notable works are:
The History of Imperial Ethiopian Army
Destas Yirs and Life 1892–1937
Aethiopia la Moneta Africana
His work helped introduce Ethiopia’s role as the birthplace of coffee to the wider world. He also authored historical works documenting the end of the Era of the Princes (Zemene Mesafint).
Professor Bossi was not only a scholar, physician, military officer, and author, but also a translator and artist. At the Catholic University of Milan, he translated and published The Little Prince in 55 international languages and contributed remarkable artistic and illustrative works.
Although death unexpectedly separated him from his beloved wife, Mrs. Sara Yemane, and his son, Caleb Giorgi, the remarkable legacy he left behind will remain alive far beyond his grave.
To preserve Professor Bossi’s legacy, his wife and son are working to complete and publish two previously unpublished manuscripts. These extensive works, each consisting of approximately 500 pages, focus on Ethiopian subjects and were left unfinished by the professor.
The professor used to say that the chapter of his love for Ethiopia was revealed—and indeed began—with his wife and his child. Based on this, his family is actively working either to open a museum in Ethiopia bearing his name or to donate his works, along with various personal artifacts and items, to the Ethiopian National Museum.
It is hoped that the Ethiopian Heritage Authority will undertake initiatives to honor and commemorate Professor Colonel Enrico Piero Bossi’s life, work, and invaluable contributions to the nation and its people.
May his memory and contributions continue to inspire future generations.
#ethiopiaheritage #italianscholar #enricopierobossi #ethiopianhistory #humanitarian #enricobossi

Sponsored by
Surafel
8 months ago
🌿 እንኳን ወደ ጋርደን ሒልስ በደህና መጡ
Escape to the Extraordinary ✨
#ethiopia | በአዲስ አበባ እምብርት፣ የካ ኮረብታን ተንተርሶ የተገነባው ጋርደን ሒልስ ሆቴል እና ስፓ፤ ከተፈጥሮ ጋር የተሳሰረ ቅንጦትን ሊያስተዋውቅዎ ዝግጅቱን ጨርሷል።
የምሥራች ✨
በዓለም አቀፍ ባለሙያዎች የተደራጀ - ከከተማው ግርግር ተነጥለው፣ በንጹህ አየር እና በወፍ ዝማሬ ታጅበው መንፈስዎን የሚያድሱበት አዲሱ "የአዲስ አበባ ማረፊያዎ"ነ አዘጋጅተናል።
🍽 Culinary Excellence ✨
በታዋቂው "La Tavola" ሬስቶራንታችን የጣልያን የምግብ ጥበብን (Authentic Italian Cuisine) ከልዩ የቡና እና ኬክ ያጣጥማሉ።
🛏 Luxury Living ✨
የከተማዋን እና የተፈጥሮን እይታ የሚሰጡ 40 ዘመናዊ እና ምቹ የመኝታ ክፍሎች (Suites)።
bi Rejuvenation:
አካልና መንፈስን የሚያድስ ስፓ እና ዌልነስ ማዕከል።
🎉 Grand Events ✨
ከ10 እስከ 300 እንግዶችን ማስተናገድ የሚችሉ፣ ለሰርግም ሆነ ለኮርፖሬት ስብሰባዎች የተዘጋጁ ዘመናዊ አዳራሾች።
🥂 You Are Invited!
( በክብር ተጋብዘዋል!)
ለሆቴል ኢንዱስትሪው፣ ለቱሪዝም፣ ለኪነ-ጥበብ እና ለሚዲያ ቤተሰቦች እንዲሁም ለክቡራት ደንበኞቻችን በሙሉ፤ በዚህ ታሪካዊ የምርቃት በዓል ላይ ተገኝተው የደስታችን ተካፋይ እንዲሆኑ በአክብሮት ጠርተናል።
📅 ቅዳሜ ጥር 30 እና እሁድ የካቲት 1 ቀን 2018 (Feb 7 & 8, 2026)
📍 ሾላ፣ ከእንግሊዝ ኤምባሲ አጠገብ፣ ሚናሮል ሕንፃ ጀርባ።
ለቦታ ማስያዝ እና ለበለጠ መረጃ (RSVP):
📞 +251-990-41-87-12
📞 +2519-29906490
🌐 www.gardenhillshotel.com
📧 infogardenhillshotel.com
#gardenhills #luxurylifestyle #addisababa #grandopening #urbanoasis #ethiopia #boutiquehotel #latavola #spaday #getutemesgen

Comments