1 day ago
የዩኒቨርስቲ ዲግሪ ማግኘት ከዕውቀት በላይ ከፍተኛ የፋይናንስ አቅም የሚጠይቅ ሆኗል
#ethiopia | የትምህርት ክፍያቸው እጅግ ከፍተኛ የሆኑ ሀገራት ደረጃ ሲወጣ አሜሪካ እና እንግሊዝ አሁንም የደረጃውን አናት ይዘው ይገኛሉ።
በአሜሪካ የሚገኙ ታዋቂ የግል ዩኒቨርሲቲዎች ለአንድ ተማሪ በአመት እስከ 60,000 ዶላር እና ከዚያ በላይ የሚያስከፍሉ ሲሆን ይህም የመኖሪያ እና የምግብ ወጪዎችን ሳይጨምር ነው።
በአንፃሩ እንደ ጀርመን እና ኖርዌይ ያሉ ሀገራት ዩኒቨርሲቲዎቻቸው ትምህርትን በነፃ ወይም እጅግ አነስተኛ በሆነ ክፍያ በማቅረብ የተለያየ የትምህርት ፖሊሲ አቀራረብ እያሳዩ ይገኛሉ።
አውስትራሊያ ለአለም አቀፍ ተማሪዎች በጣም ውድ ከሆኑ ሀገራት አንዷ ስትሆን የመኖሪያ ወጪዎችን ጨምሮ አንድ ተማሪ በአመት እስከ 40,000 ዶላር ታስከፍላለች።
በትምህርት ጥራት አለምን እየመራች ያለችው ካናዳ ለአካባቢው ተማሪዎች የትምህርት ክፍያ በአንፃራዊነት ተመጣጣኝ ክፍያ ቢሆንም ለአለም አቀፍ ተማሪዎች ግን ክፍያው በየዓመቱ እየጨመረ ይገኛል።
በዚህም አንድ ተማሪ በአመት እስከ 36,000 ዶላር ክፍያ ይከፍላል።
ይህ ከፍተኛ የትምህርት ወጪ ተማሪዎችን ከምረቃ በኋላ ለከፍተኛ የብድር ዕዳ እየዳረጋቸው ሲሆን የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የዋጋ ንረት አሁንም በዓለም አቀፍ ደረጃ አልቀመስ ብሏል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#ethiopia #getutemesgen #getunews #worldwide #costeducation #university #expenses #students #income

10 months ago
ቢል ጌትስ ሮቦቶች ላይ ግብር እንዲጣል ሀሳብ አቀረቡ
#ethiopia | የማይክሮሶፍት ተባባሪ መስራች የሆኑት ቢል ጌትስ፣ ሮቦቶች የሰዎችን ሥራ ሲረከቡ የገቢ ምንጭ የሆኑ ሮቦቶች ላይ ግብር የመጣል ሀሳባቸው አሁን ባለው የቴክኖሎጂ ለውጥ ዘመን ዳግም ትኩረት አግኝቷል።
ይህን ያልተለመደ አስተያየት ለመጀመሪያ ጊዜ ያቀረቡት እ.ኤ.አ. በ2017 ዓ.ም ሲሆን፣ ሀሳቡም ሠራተኞች ላይ ከሚከፈለው የደመወዝ ታክስ ጋር በሚመሳሰል መልኩ፣ ሥራቸውን በሮቦት ለተኩ የንግድ ተቋማት የሮቦት ግብር እንዲጣል የሚያስችል ነው።
በወቅቱ እንደ ረቂቅ አስተያየት የታየው ሀሳብ፣ አሁን አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) በምርትና በአገልግሎት ዘርፎች የሰውን ጉልበት በከፍተኛ ፍጥነት እየተካ በመጣበት በዚህ ጊዜ፣ የረዥም ጊዜ አስተዋይነት የታየበት መፍትሔ ሆኖ ቀርቧል።
ምንም እንኳን ጌትስ የሮቦት ግብርን በቀጥታ ከዩኒቨርሳል መሰረታዊ ገቢ (Universal Basic Income – UBI) ጋር ባያያይዙትም፣ እነዚህ ሁለት ጽንሰ-ሐሳቦች የሥራ መጥፋት የሚያስከትለውን ኢኮኖሚያዊ ቀውስ ለመቋቋም በሚደረጉ ዓለም አቀፍ ውይይቶች ላይ ተደጋግመው ይነሳሉ።
ጌትስ በ2017 ባደረጉት አንድ ቃለ ምልልስ ላይ ዩናይትድ ስቴትስ UBIን ለመቀበል ገና የሚበቃ ሀብት እንደሌላት ገልጸው ነበር። ሆኖም፣ በቅርቡ በ2024 በኔትፍሊክስ ባቀረቡት ተከታታይ ፊልም (What's Next? The Future With Bill Gates) ላይ ያካፈሉት አስተያየት ለውጥ አሳይቷል።
እንደ መናኸሪያ ኤፍ ኤም ዘገባ ከሆነ በድህነት ቅነሳ ላይ ያተኮሩ የUBI ዓይነት ፕሮግራሞች በመጨረሻ የረዥም ጊዜ ወጪ ቁጠባ እንደሚያስገኙ ይከራከራሉ።
ይህንንም ሲያብራሩ፣ በዩናይትድ ስቴትስ የአዋቂዎች ድህነት በዓመት ከ1 ትሪሊዮን ዶላር በላይ እንደሚያስወጣ የሚያመላክተውን መረጃ በመጥቀስ፣ የድህነት ቅነሳ ከጊዜ በኋላ ከሚደረገው ወጪ የበለጠ ጥቅም እንደሚያስገኝ አሳስበዋል።

11 months ago
ሜታ (ፌስቡክ) በኢትዮጵያ የይዘት ገቢ ማግኛ (Monetization) አገልግሎት አለማስጀመሩ ምክንያቶች ምንድን ናቸው?
#ethiopia | የዓለማችን ግዙፉ የማኅበራዊ ሚዲያ መድረክ የሆነው ፌስቡክ (ሜታ)፣ በበርካታ ሀገራት ለይዘት ፈጣሪዎች የገንዘብ ክፍያ የሚያስገኙ እንደ In-Stream Ads ያሉ ዋና ዋና የገቢ ማግኛ አገልግሎቶችን በኢትዮጵያ በይፋ አለማስጀመሩ ጉዳይ የማኅበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎችን እና Content Creators ዎችን ጥያቄ ሲያጭር ቆይቷል።
ለዚህም ዋነኛ ምክንያቶች የሆኑት የንግድ፣ የክፍያ እና የሕግ ተግዳሮቶች መሆናቸው ተመላክቷል።
የዘርፉ ባለሙያዎች እንደሚጠቁሙት፣ ሜታ (Meta) አንድን አገልግሎት ወደ አዲስ ሀገር ከማስፋፋቱ በፊት የሚከተሉትን ቁልፍ ነጥቦች በዋናነት ይመረምራል፦
1. የገንዘብ ዝውውር እና የክፍያ ሥርዓት ውስብስብነት
ፌስቡክ ገቢ ላስገኙ የይዘት ፈጣሪዎች ዓለም አቀፍ የገንዘብ ዝውውር ማድረግ ይጠበቅበታል። በኢትዮጵያ ያለው ዓለም አቀፍ የክፍያ መቀበያ ዘዴ (International Payment System) ውስንነት እና የውጭ ምንዛሪ ቁጥጥር፣ ኩባንያው ክፍያዎችን በአስተማማኝ ሁኔታ ለመፈጸም እንዲቸገር ከሚያደርጉ ዋና ዋና ምክንያቶች መካከል ይጠቀሳሉ።
በተጨማሪም የKnow Your Customer (KYC) መስፈርቶችን ማሟላት ፈታኝ ነው ተብሏል።
2. የማስታወቂያ ገበያው መጠን (Ad Market Volume)
የፌስቡክ Monetization በቀጥታ የሚመነጨው በContent ፈጣሪዎች ቪዲዮ ወይም ገጽ ላይ በሚታዩ ማስታወቂያዎች ነው። ሜታ አገልግሎቱን ከመጀመሩ በፊት በአገሪቱ ውስጥ ያለው ትልቅ የማስታወቂያ ፍላጎትና የማስታወቂያ አስነጋሪዎች ቁጥር እንዲሁም ኩባንያው ከዚህ ገበያ የሚያገኘው የሚጠበቅ ገቢ መኖሩን ያረጋግጣል። የኢትዮጵያ የዲጂታል ማስታወቂያ ገበያ መጠን ከሌሎች የዓለም አገራት አንጻር ሲታይ ዝቅተኛ በመሆኑ፣ ይህ እንደ አንድ ምክንያት ሊወሰድ ይችላል ተብሏል።
3. የሕግ ማዕቀፎች እና የግብር ጉዳዮች
የገንዘብ ክፍያ መፈጸም ሲጀመር፣ ኩባንያው የአገሪቱን የግብር (Tax) እና የፋይናንስ ቁጥጥር ሕጎች ሙሉ በሙሉ ማክበር ይኖርበታል። በኢትዮጵያ ውስጥ ለዲጂታል ገቢ (Digital Income) እና ለዓለም አቀፍ የንግድ ልውውጦች ግልጽ እና ቀጥተኛ የሆኑ የሕግ ማዕቀፎች እና የአፈጻጸም ሂደቶች ገና በመገንባት ላይ መሆናቸው፣ ለፌስቡክ አገልግሎቱን ለማስጀመር እንቅፋት መሆኑ ይነገራል።
ሜታ በአፍሪካ ቀስ በቀስ የገቢ ማግኛ አማራጮችን እያሰፋ በመምጣቱ (ለምሳሌ በሌሎች አፍሪካ ሀገራት የReels Play Bonus Program መጀመሩ)፣ በቅርብ ጊዜ ውስጥ በኢትዮጵያም የገቢ ማግኛ መንገዶችን ለማስጀመር ጥናት እያደረገ ሊሆን እንደሚችል ይጠበቃል።
#menaharia_fm

1 year ago
ለዩኒቨርሲቲ መምህሩ አስናቀ ብርሃኑ እንድረስለት
Lets support Our Teacher
Yilkal Andualem is organizing this fundraiser.
Donation protected
መምህራችን_ታሞብናል
ወደ ካንሰር ሊቀየር ይችላል....ሀኪሞች
ወጣት መ/ር አስናቀ ብርሃኑ አላምነህ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በቅንነትና በታማኝነት እያገለገለ ያለ በሙያውም አንቱታን ያተረፈ በሥነ ምግባሩ ምስጉን ሰው አክባሪ፣ ለተቸገሩ ፈጥኖ ደራሽ ወንድማችን ነው::
በሒሳብ ትምህርት ክፍል የኑሜሪካል አናላይሲስ መምህር ሲሆን በዩኒቨርሲቲ ቆይታውም ከማስተማር ስራው ጎን ለጎን በጥናትና ምርምር ዘርፍ በሙያው አለም አቀፍ ተቀባይነት ያላቸው 6 (ስድስት) ጥናትና ምርምሮችን በማሳተም ለአንባቢያን አድርሷል::
ወንድማችን መ/ር አስናቀ ድንገት በገጠመው የጤና እክል በህይወት እና በሞት መካከል ሆኖ የድረሱልኝ ተማፅኖውን እያሰማ ይገኛል:: በገጠመው የጤና ዕክል በተለያዩ ስድስት (6) ሆስፒታሎች ህክምና ሲያደርግ ቆይቷል::
ከነዚህም ውስጥ በአንዱ ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ሪፈራል ሆስፒታል ሰርጀሪ ተሰርቶ ሊሻለው ባለመቻሉ ወደ አዲስ አበባ አለርት ኮምፕርሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ሪፈር ተፅፎለት ክትትል እያደረገ ይገኛል::
በመሆኑም የአለርት ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የህክምና ቦርድ 30% አጠቃላይ ቋሚ የአካል ጉዳተኛ እንደሆነና የሚከተሉትን ውሳኔዎችን ወስኗል::
1ኛ. በግራ እግሩ ላይ ስድስት (6) ዓመት የቆየ ከባድ ቁስለት ወደ ካንሰር የመቀየር እድሉ እጅግ በጣም ከፍተኛ መሆኑን፣
2ኛ. ሁለቱም እግሮቹ ነርቫቸው የተጎዳና ስሜት አልባ መሆናቸውን፣
3ኛ. የግራ እግሩ ሙሉ አጥንቶቹ የተጎዱና ይዘታቸውን የቀየሩ መሆናቸውን
4ኛ. ቁሞ ማስተማርም ሆነ በእግሩ መንቀሳቀስ እንደማይችል የአለርት ሆስፒታል ሜዲካል ቦርዱ አረጋግጧል
መምህር አስናቀ ባለብዙ ተስፋና ብዙ ህልም የነበረዉ ሩጦ ያልጠገበ ወንድማችን እግሮቹ ደክመው እቤት እንዲውል ተገዷል::
የህመሙ ሁኔታ አሳሳቢ እና ለህይወቱም አስጊ ደረጃ ላይ በመድረሱ ወደ ህንድ አገር ሂዶ ህክምና እንዲያደርግ ሪፈር ተፅፎለታል:: የህክምና ወጭውም ከሁለት ሚሊየን (2,000,000) ብር በላይ እንደሚያስፈልገው ተነግሮታል::
ወንድማችንን ለማገዝ አነሰ በዛ ሳንል በአገር ውስጥና በውጭ ያላችሁ ትዉልደ ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን የእርዳታ እጃችሁን ትዘርጉ ዘንድ በፈጣሪ ስም እንጠይቃለን::
Asinake Birihanu Alamneh
ስልክ_ቁጥር 09 23 53 45 01
Lecturer Asnake Berhanu, who has been serving Hawassa University with integrity and honesty, is a respected, respectful, and helpful person who has earned a reputation in his profession.
He is a Numerical Analysis Lecturer in the Department of Mathematics.
During his time at the university, he has published 6 (six) internationally recognized studies and research papers in his field, and has reached readers.
Our brother,Teacher Asnake is suddenly in the middle of life and death due to a health problem he encountered.
He has been receiving treatment in six (6) different hospitals for his health problem. In one of them, he underwent surgery at Hawassa University Referral Hospital and was referred to Addis Ababa Alert Compressive Specialized Hospital for follow-up.
Therefore, the Alert Specialized Hospital Medical Board has determined that he is 30% permanently disabled and has made the following decisions:
1st. The six (6) year old severe ulcer on his left leg has a very high chance of turning into cancer,
2nd. Both his legs are nerve damaged and numb,
3rd. The entire bones of his left leg are damaged and their contents have changed,
4th. The Alert Hospital Medical Board has confirmed that he cannot stand or walk.
Our brother, Teacher Asnake, who had many hopes and dreams, has been forced to stay home due to tired legs. His condition is serious and life-threatening, so he has been referred to India for treatment. He has been told that the medical expenses will cost more than $15000 .
Please help support this visionary teacher as they navigate through an incredibly difficult time. The funds raised will go towards the cost of surgical treatment , and to help to cover the loss of income while taking some much needed time to recover.
Thank you for your generosity.
I am grateful for your help and wishes.
Thank you
"Let's save the life of the visionary teacher with sincere hearts and united hands!
Show your support for this GoFundMe

ሲንቄ ባንክ
#ethiopia | የሲንቄ ባንክ የ2024/2025 በጀት አመት አፈጻጸም እና ያለፉት ሶስት አመታት ስኬታማ ጉዞን በማስመልከት በዛሬው ዕለት ሰኔ 26 ቀን 2017 ዓ/ም በባንኩ ዋና መ/ቤት ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል።
የባንኩ ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ ንዋይ መገርሳ በሰጡት መግለጫ ባንኩ የበጀት ዓመቱን በላቀ አፈጻጸም ማጠናቀቁን እና በዚህ አጭር 3 አመታት ውስጥ የባንኩ ጠቅላላ ተቀማጭ ገንዘብ(Total deposit) ብር 102.5 ቢሊየን መድረሱን እና የባንኩ ጠቅላላ ገቢ (Total income) ብር 15 ቢሊየን ገልፀው ለዚህ ስኬት አስተዋፅኦ ላደረጉ የባንኩን ስራ አመራሮች፣ደንበኞች፣ሰራተኞችና ሁሉንም ባለድርሻ አካላት አመስግነዋል።
ክቡር አቶ ንዋይ አክሎም ለቀጣዩ የስራ ዘመን የባንኩን ስኬትና ትርፋማነትን በእጥፍ የሚያድግበት ዘመን እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን በመግለፅ የባንኩ ስራ አመራሮች፣ሰራተኞች እና ባለድርሻ አካላት የባንኩን እቅድ ለማሳካት በቁርጠኝነት እና በትጋት እንዲሰሩ አሳስበዋል።
በአንድነት ወደ ስኬት!
#siinqee_bank #baankii_siinqee #ሲንቄ_ባንክ #siinqee_digital #siinqee_ihsan #siinqee_digital #financial_inclusion #empowered_together

Comments