Logo
Getu Temesgen
የዩኒቨርስቲ ዲግሪ ማግኘት ከዕውቀት በላይ ከፍተኛ የፋይናንስ አቅም የሚጠይቅ ሆኗል
#ethiopia | የትምህርት ክፍያቸው እጅግ ከፍተኛ የሆኑ ሀገራት ደረጃ ሲወጣ አሜሪካ እና እንግሊዝ አሁንም የደረጃውን አናት ይዘው ይገኛሉ።

በአሜሪካ የሚገኙ ታዋቂ የግል ዩኒቨርሲቲዎች ለአንድ ተማሪ በአመት እስከ 60,000 ዶላር እና ከዚያ በላይ የሚያስከፍሉ ሲሆን ይህም የመኖሪያ እና የምግብ ወጪዎችን ሳይጨምር ነው።

በአንፃሩ እንደ ጀርመን እና ኖርዌይ ያሉ ሀገራት ዩኒቨርሲቲዎቻቸው ትምህርትን በነፃ ወይም እጅግ አነስተኛ በሆነ ክፍያ በማቅረብ የተለያየ የትምህርት ፖሊሲ አቀራረብ እያሳዩ ይገኛሉ።

አውስትራሊያ ለአለም አቀፍ ተማሪዎች በጣም ውድ ከሆኑ ሀገራት አንዷ ስትሆን የመኖሪያ ወጪዎችን ጨምሮ አንድ ተማሪ በአመት እስከ 40,000 ዶላር ታስከፍላለች።

በትምህርት ጥራት አለምን እየመራች ያለችው ካናዳ ለአካባቢው ተማሪዎች የትምህርት ክፍያ በአንፃራዊነት ተመጣጣኝ ክፍያ ቢሆንም ለአለም አቀፍ ተማሪዎች ግን ክፍያው በየዓመቱ እየጨመረ ይገኛል።

በዚህም አንድ ተማሪ በአመት እስከ 36,000 ዶላር ክፍያ ይከፍላል።

ይህ ከፍተኛ የትምህርት ወጪ ተማሪዎችን ከምረቃ በኋላ ለከፍተኛ የብድር ዕዳ እየዳረጋቸው ሲሆን የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የዋጋ ንረት አሁንም በዓለም አቀፍ ደረጃ አልቀመስ ብሏል።

ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#ethiopia #getutemesgen #getunews #worldwide #costeducation #university #expenses #students #income

2 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.