Logo
Getu Temesgen
ሲንቄ ባንክ
#ethiopia | የሲንቄ ባንክ የ2024/2025 በጀት አመት አፈጻጸም እና ያለፉት ሶስት አመታት ስኬታማ ጉዞን በማስመልከት በዛሬው ዕለት ሰኔ 26 ቀን 2017 ዓ/ም በባንኩ ዋና መ/ቤት ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል።

የባንኩ ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ ንዋይ መገርሳ በሰጡት መግለጫ ባንኩ የበጀት ዓመቱን በላቀ አፈጻጸም ማጠናቀቁን እና በዚህ አጭር 3 አመታት ውስጥ የባንኩ ጠቅላላ ተቀማጭ ገንዘብ(Total deposit) ብር 102.5 ቢሊየን መድረሱን እና የባንኩ ጠቅላላ ገቢ (Total income) ብር 15 ቢሊየን ገልፀው ለዚህ ስኬት አስተዋፅኦ ላደረጉ የባንኩን ስራ አመራሮች፣ደንበኞች፣ሰራተኞችና ሁሉንም ባለድርሻ አካላት አመስግነዋል።

ክቡር አቶ ንዋይ አክሎም ለቀጣዩ የስራ ዘመን የባንኩን ስኬትና ትርፋማነትን በእጥፍ የሚያድግበት ዘመን እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን በመግለፅ የባንኩ ስራ አመራሮች፣ሰራተኞች እና ባለድርሻ አካላት የባንኩን እቅድ ለማሳካት በቁርጠኝነት እና በትጋት እንዲሰሩ አሳስበዋል።

በአንድነት ወደ ስኬት!
#siinqee_bank #baankii_siinqee #ሲንቄ_ባንክ #siinqee_digital #siinqee_ihsan #siinqee_digital #financial_inclusion #empowered_together

1 year ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.