Logo
Getu Temesgen
ኤስሚላን የራስሙስ ሆይሉንድን ሁኔታ ጠይቋል
#ethiopia | የጣልያን ሴሪአው ክለብ ኤሲሚላን በማንችስተር ዩናይትድ ጥሩ ጊዝያትን ማሳለፍ የተሳነው ዴንማሪካዊው አጥቂ ራስሙስ ሆይሉንድን ማሰፈረም በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ክለቡን መጠይቁ ተዘግቧል፡፡

እኤአ በ2023 ከጣልያኑ ክለብ አታላንታ 72 ሚሊዮን ፓውንድ በሚጠጋ የዝውውር ዋጋ ማንችስተር ዩናይትድን የተቀላቀለው ራስሙስ ሆይሉንድ በመጀመርያው የውድድር አመት የኦልድትራፎርድ ቆይታው ትልቅ ተስፋን የሰጠ እንቅስቃሴን ማደረግ ችሎ እንደነበር ይታወቃል፡፡

ሆይሉንድ በ2023/24 የውድድር ዘመን በ43 ጨዋታዎች 16 ጎሎችን አስቆጥሮ 2 ለግብ የሚሆኑ ኳሶችን ደግሞ አመቻችቶ ማቀበሉ የሚታወስ ነው፡፡

የ22 አመቱ ሆይሉንድ በአሰልጣኝ ኤሪክ ቴን ሀግ ስር አጀማመሩ ጥሩ እንደነበር ቢታወስም አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም ወደ ክለቡ ከመጡ ወዲህ ደካማ የተባለ ጉዞን ያሳለፈበት ሆኗል፡፡

በተጠናቀቀው የውድድር አመት ባጠቃላይ 10 ጎሎችን ብቻ ያስቆጠረው ሆይሉንድ በተለይም በፕሪሚየር ሊጉ ያስቆጠራቸው ጎሎች 4 ብቻ መሆናቸው ተጨዋቹ በቀጣይ የኦልድትራፎርድ ቆይታው ትልቅ ጥያቄ እንዲነሳበት ያደረገ ሆኗል፡፡

የጣልያኑ ክለብ ኢንተርሚላን ሆይሉንድን ማስፈረም ፍላጎት ካላቸው ክለቦች መካከል ቀዳሚው እንደነበር ቢገለጸም ሌሎች አጥቂዎችን መመልከት መጀመሩን ተከትሎ በተቀናቃኙ ኤስሚላን አይን አርፎበታል፡፡

በአሰልጣኝ ማስሚላኖ አሌግሪ የሚመራው ኤስሚላን ስለተጨዋቹ ሁኔታ ማንችስተር ዩናይትድን ማናገራቸው ተዘግቧል፡፡

በማንችስተር ዩናይትድ እንዲሁም በተጨዋቹ በኩል እስካሁን በይፋ የተባለ ነገር ባይኖርም ነገር ግን ክለቡ ትክክለኛ ዋጋ ከቀረበለት አጥቂውን ለመሸጥ አይኑን እንደማያሽ በመዘገብ ላይ ይገኛል፡፡ #hagerietv

11 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.