የዝውውር ገበያውን ክብረወሰን የሰበረችው ኦሊቪያ ስሚዝ
#ethiopia | በናኦሚ ግርማ ተይዞ የነበረውን የሴት እግር ኳስ ተጫዋቾች የዝውውር ክፍያ ክብረ ወሰን ለአርሰናል በፈረመችው አጥቂ ኦሊቪያ ስሚዝ ተሰብሯል፡፡
ካናዳዊቷ አጥቂ ኦሊቪያ ስሚዝ በሴቶች እግርኳስ ታሪክ ክብረወሰን የሆነውን የናኦሚ ግርማ የ900 ሺህ ፓውንድ ዝውውር እንደሰበረችው ታውቋል፡፡
ናኦሚ ባሳለፍነው ጥር ከአሜሪካው ክለብ ሳን ዲዬጎ ቼልሲን መቀላቀሏ ይታወሳል፡፡
አሁን ላይ ሌላኛውን ክብረውሰን የሰበረችው ኦሊቪያ ስሚዝ 1 ሚሊዮን ፓውንድ በሆነ ዋጋ ከሊቨርፑል አርስናልን በመቀላቀል ነው ያሻሻለችው፡፡
በዚህም በሴቶች የእግር ኳስ ታሪክ ከፍተኛውን ክፍያ በማግኘት ወደ ሌላ ክለብ የተዘዋወረች ተጫዋች ለመሆን ችላለች።የ20 ዓመቷ ወጣት ስሚዝ ከሻምፒየንስ ሊጉ ባለቤት አርስናል ጋር የአራት ዓመት ኮንትራት ፈርማለች።
ኦሊቪያ ስሚዝ ከአንድ አመት በፊት ከፖርቹጋሉ ክለብ ስፖርቲንግ ሊዝበን ሊቨርፑል መቀላቀሏ ይታወሳል፡፡
ተጨዋቿ ከመርሲሳይዱ ክለብ ጋር ቀሪ የሁለት ዓመት ውል ቢኖራትም ሊቨርፑል የቀረበለትን ከፍተኛ የዝውውር ገንዘብ ውድቅ ማድረግ እንዳልቻለ ታውቋል፡፡
ስሚዝ በመጀመሪያ የውድድር ዘመን ለሊቨርፑል በተሰለፈችባቸው ጨዋታዎች ሰባት ግቦችን ማስቆጠር ስትችል እንዲሁም ለሀገሯ ካናዳ 18 ጨዋታዎችን በማድረግ አራት ግቦችን ማስቆጠር ችላለች፡፡ #hagerietv

11 months ago