የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ለአፍሪካ ቡድኖች መልካም ምኞታቸውን ገለጹ!
#ethiopia | ለመጀመሪያ ጊዜ 48 ሀገራት የሚሳተፉበትን የ2026 ዓለም ዋንጫ ዛሬ መጀመሩን አስመልክቶ፣ የአፍሪካ ህብረት (AU) ኮሚሽን ሊቀመንበር ማህሙድ አሊ ዩሱፍ በትልቁ መድረክ አህጉሪቱን ለሚወክሉ 10 ቡድኖች መልካም ምኞታቸውንና ጠንካራ ድጋፋቸውን ገልጸዋል።
“ይህ በታሪክ ከፍተኛው የአፍሪካ ሀገራት ተሳትፎ፣ የአፍሪካ እግር ኳስ እያሳየ የመጣውን ቀጣይነት ያለው እድገት እንዲሁም የተጫዋቾቹን ተሰጥኦ እና ጥንካሬ የሚያንጸባርቅ ነው። ይህ ሁሉንም አፍሪካውያንን በጋራ ተስፋ እና ደስታ የሚያስተሳስር የአህጉራዊ ኩራት የምዕራፍ ማሳያ ነው” ብለዋል ማህሙድ አሊ ዩሱፍ።
ሊቀመንበሩ አክለውም፣ ዓለም ዋንጫ ሀገራትን የሚያስተሳስር እና በሰላም የሚገናኝበት መድረክ በመሆኑ አፍሪካውያን አመርቂ ውጤት በማስመዝገብ አርአያ እንደሚሆኑ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።
የአፍሪካ የእግር ኳስ ዕድገት የወጣቶቿ ጥንካሬ ነጸብራቅ ነው ያሉት ሊቀመንበሩ ተፎካካሪ ቡድኖቹ የሀገራቸውን ህዝብ ተስፋ ብቻ ሳይሆን የአንድ ሙሉ ትውልድ ምኞትና ፍላጎት ጭምር የተሸከሙ እንደሆኑ ተናግረዋል።
የአፍሪካ ህብረት ይህ ታሪካዊ ምዕራፍ እውን እንዲሆን ላደረጉ ተጫዋቾች፣ አሰልጣኞች፣ የስፖርት አመራሮች እና ደጋፊዎች አድናቆቱን የሚገልጽ ሲሆን፣ ሁሉም ቡድኖች በላቀ ብቃት፣ በስነ-ስርዓት እና ለታማኝነት ክብር በመስጠት እንዲወዳደሩ ያበረታታል ብለዋል።
ለ39 ቀናት የሚቆየው የዓለም ዋንጫ ዛሬ ሲጀመር በመክፈቻው ደቡብ አፍሪካ ከሜክሲኮ የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #digitalhagerie #au #hagerietv #2026worldcup #africateam

2 months ago