Logo
Getu Temesgen
“የግድያ ማስፈራሪያ ደርሶብኝ ነበር” ሩኒ
#ethiopia | እንግሊዛዊው የቀድሞ የማንችስተር ዩናይትድ አጥቂ ዋይን ሩኒ የልጅነት ክለቡን ኤቨርተንን ለቆ ወደ ወደ ኦልድትራፎርድ ባቀናበት ወቅት የግድያ ማስፈራሪያ ዛቻዎች ይደርሱት እንደነበር ተናግሯል፡፡

እ.ኤ.አ 2004 በ27 ሚሊዮን ፓውንድ ከኤቨርተን ማንችስተር ዩናይትድን በተቀላቀለበት ወቅት የመርሲሳይዱ ክለብ ደጋፊዎች የማስፈራሪያ እና የግድያ ዛቻ ይልኩበኝ ነበር ሲል ገልጿል፡፡

የቤተሰቦቹ ቤት ላይ ሳይቀር የማስፈራሪያ ጽሁፎች ጭምር ተፅፈው እንደነበር የተናገረው የቀድሞ የማንችስተር ዩናይትድ ታሪካዊ ተጨዋች እንደዚህ አይነት ነገር ሲገጥማቸው ተጨዋቾች በአዕምሮ ጠንካራ መሆን አለባቸው ሲል ለቢቢሲ ስፖርት በሰጠው ቃል ገልጿል።
#hagerietv

6 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.