በሚቀጥሉት ቀናት ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ሊኖር እንደሚችል ተጠቆመ
#ethiopia | በሚቀጥሉት ቀናት በምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ሰሜን እና መካከለኛው የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚኖር የኢትዮጵያ ሜትሮሎጂ ኢንስቲቲዩት አስታወቀ፡፡
በተጨማሪም በደቡብ ምዕራብ፣ ሰሜን ምስራቅ እና ምስራቅ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ ተብሏል፡፡
በመጪዎቹ የነሃሴ የመጀመሪያዎቹ አሥር ቀናት ዝናብ ሰጭ የሚቲዎሮሎጂ ገጽታዎች የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የተሻለ የዝናብ መጠንና ሥርጭት እንደሚኖራቸው የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ።
ይህም የሚጠበቀው እርጥበት ለወቅቱ የግብርና ስራ እንቅሥቃሴ በአመዛኙ አዎንታዊ ሚና የሚኖረው ቢሆንም፤ ተያያዥ ስጋቶችን ለመቀነስና የሚኖሩትን መልካም አጋጣሚዎች በላቀ ሁኔታ ለመጠቀም የቀረቡትን ቦታ ተኮር የግብርና ሚቲዎሮሎጂ ምክረ ሀሳቦች መተግበር ይገባል ተብሏል፡፡ #hagerietv

11 months ago