የእስር ቤት ጥበቃ ሰራተኛው ዴኒስ ኦሜዲ በአፍሪካ ዋንጫ
#ethiopia | ዴኒስ ኦሜዲ ይባላል የቀድሞ የኪታራ ኤፍሲ አጥቂ እና ለዩጋንዳ ክሬንስ ቁልፍ ተጫዋች የነበረ ነው፡፡በወቅቱም የዓመቱ ምርጥ ተጫዋች ተብሎ ተሸልሟል።
አጥቂው ዩጋንዳ ለ2025 የአፍሪካ ዋንጫ እንድታልፍ በመርዳት እና የ2024ቱን የስታንቢክ ኡጋንዳ ዋንጫ ከኪታራ ኤፍሲ ጋር በማሸነፍ ያሳየው አስደናቂ ብቃት ከፍተኛውን ሽልማት አስገኝቶለታል።
ዴኒስ ኦሜዲ ያስቆጠራት ምርጥ ቄንጠኛ ጎል በ2024 የፊፋ ፖሽካሽ የአመቱ ምርጥ ጎል በመባል እጩ እንደነበረች የሚታወስ ነው::
ታዲያ ይህ አጥቂ ከሀገሩ ዩጋንዳ ጋር በአፍሪካ ዋንጫ ውድድር ሞሮኮ ላይ ከትሟል፡፡በምድብ ሶስት ላይ የምትገኘው ዩጋንዳ ትናንት ምሽት ከቱኒዝያ ጋር ያደረገችውን ጨዋታ 3ለ1 መሸነፏ ይታወሳል፡፡
ብቸኛዋን አንድ ጎል ለዩጋንዳ ብሔራዊ ቡድን በ90 ደቂቃ ጭማሪ ያስቆጠረው አጥቂው ዴኒስ ኦሜዲ ሲሆን ይህም ተጨዋች በመጀመሪያ የአፍሪካ ዋንጫ ተሳትፎውም ለሀገሩ ጎል ማስቆጠር ችሏል።
ዴኒስ ኦሜዲ የትርፍ ጊዜ እግር ኳስ ተጨዋች እንደነበር ብዙ መረጃዎች የሚያሳዩ ሲሆን እንዲሁም ትምህርቱን በሚገባ ተከታትሎ በነርሲንግ ዲፕሎማውን እንዳገኘ ታውቋል፡፡
ሌላው የዴኒስ ኦሜዲ አስገራሚ የህይወት ጉዞ ሲቀጥል ወደ አፍሪካ ዋንጫ ከማቅናቱ በፊት የህይወት መንገዱ ተቀይሮ የእስር ቤት ጥበቃ ሰራተኛ በመሆን እያገለገለ እንደነበር ተገልጿል።
31 ዓመቱ ላይ የሚገኘው ዴኒስ ኦሜዲ ከስድስት አመታት በኋላ ዩጋንዳን በአፍሪካ ዋንጫ ውድድር ወክሎ ሞሮኮ ከትሟል፡፡
ዩጋንዳ በምድቡ የሁለተኛ ዙር ጨዋታ የፊታችን ቅዳሜ ከታንዛኒያ ጋር የምትጫወት ይሆናል፡፡
#hagerietv

5 months ago