24 days ago
🔔 ያረጋግጡ!
የሪሚዲያል ተማሪዎች ፈተና ለመውሰድ የተመዘገባቹ በአስቸኳይ የማረጋገጥ ሥራ እንድታደርጉ ትምህርት ሚኒስቴር አሳስቧል።
የማረጋገጥ ሥራው (Self Verification) ከ2-3 ደቂቃዎች ብቻ የሚወስድና የተፈታኞችን የትምህርት ሰነዶች ከፋይዳ መታወቂያ ጋር ለማስተሳሰር የሚያስችል መሆኑ ተመላክቷል።
ተከታዩን ሊንክ (https://verify.ethernet.ed... ከተጫኑ በኋላ Remedial Examination የሚለውን ይጫኑ፣ Start Verification የሚለውን በመጫንና የሚያስፈልገውን በመሙላት ያረጋግጡ።
የሪሚዲያል ፈተና ከግንቦት 27 እስከ ሰኔ 03/2018 ዓ.ም እንደሚሰጥ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት መግለፁ ይታወቃል።
seledadotio

25 days ago
የሬሜዲል ፈተና መስጫ ቀን ተራዘመ።
ከግንቦት 17 እስከ 20 ቀን 2018 ዓ/ም ሊሰጥ ፕሮግራም ወጥቶለት የነበረው የሬሜዲያል (የአቅም ማሻሻያ) ፈተና ከግንቦት 27 እስከ ሰኔ 3 ቀን 2018 ዓ/ም እንዲሰጥ ተራዝሟል።
የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት " የሪሜዲያል ፈተና እና የቅድመ ምረቃ ትምህርት መውጫ ፈተና (Exit Exam) የሚሰጥበት ቀን ተቀይሯል " ብሏል።
" ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጋር ምክክር በማድረግ የሪሜዲያል እና EXIT EXAM ፈተናዎች የሚሰጥባቸው ቀናት ተሸጋሽጓል " ሲል አሳውቋል።
በዚህም የሬሜዲያ ፈተና ከግንቦት 27 እስከ ሰኔ 3 ቀን 2018 ዓ/ም ፤ የቅድመ ምረቃ መውጫ ፈተና ደግሞ ከሰኔ 4 እስከ ሰኔ 12 ቀን 2018 ዓ/ም እንደሚሰጥ ገልጿል።

1 month ago
የመውጫ ፈተና‼️
የቅድመ ምረቃ የመውጫ ፈተና በድጋሚ በግል መፈትን ለምትፈልጉ ምዝገባው ከዛሬ ግንቦት 8 እስከ 12/2018 ዓ.ም በዚህ https://exam.ethernet.edu....
ድረገፅ መመዝገብ ትችላላችሁ።
ለመመዝገብ የፋይዳ መታወቂያ እንዲሁም በቴሌብር የሚከል 750 ብር ግዴታ ነው።

የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ለሚወስዱ ተፈታኞች
ከመጪው ሰኔ 24/2018 ዓ/ም ጀምሮ የሚሰጠውን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ለሚወስዱ ተፈታኞች የተዘጋጀ የመፈተኛ ክፍል መግቢያ ካርድ (Admission Card) በፈተና አስተዳደር ሲስተም (https://exam.eaes.et/) ከ03/09/2018 ዓ/ም ጀምሮ ለክልል ትምህርት ቢሮ፣ ለዞን ትምህርት መምሪያዎች እና ለትምህርት ቤት ተወካዮች መለቀቁን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።
አገልግሎት መ/ቤቱ ፦
1. እያንዳንዱ ተፈታኝ ተማሪ በአድሚሽን ካርዱ ጀርባ ላይ የትምህርት ቤቱን ወይም የወረዳው አስተዳደር ትምህርት ጽ/ቤት ማህተም የተደረገበትን አድሚሽን ካርድ ከትምህርት ቤቱ ወስዶ በእጁ መያዝ መያዝ እንዳለበት አሳስቧል።
2. በምዝገባ ወቅት በተፈታኙ ወይም በመዝጋቢው የተከሰተ የትምህርት መስክ ፣ የጾታ ፣ የፎቶ እና መሰል ማስተካከያዎች ካሉ ከግንቦት 30/2018 ዓ.ም በፊት ለትምህርት ቤቱ ማሳወቅና ሂደቱን ጠብቆ መስተካከሉንም ከትምህርት ቤቱ ማረጋገጥ እንደሚገባ ገልጿል።
3. እያንዳንዱ ተፈታኝ አድሚሽን ካርዱን ወደ መፈተኛ ማዕከል ሆነ መፈተኛ ክፍል ለመግባት የሚጠቀምበት በመሆኑ በአግባቡና በጥንቃቄ እንዲይዝ አሳስቧል።
4. ተፈታኞች ፈተና ላይ ከአድሚሽን ካርድ በተጨማሪ የፋይዳ መታወቂያ መያዝ እንደሚጠበቅባቸው ገልጿል።
tikvahethiopia

#grade12
#nationalexam

Sponsored by
Surafel
2 months ago
የ12ኛ ክፍል ፈተና የሚሰጥበት ቀን ይፋ ሆነ
#ethiopia | የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ሠርተፊኬት (12ኛ ክፍል ፈተና) ከሰኔ 24 እስከ ሃምሌ 17 ቀን 2018 ዓ/ም ድረስ እንደሚሰጥ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቆናል።
በሌላ በኩል ፦
- የሬሜዲያል ፕሮግራም ሀገር አቀፍ ፈተና ከግንቦት 17 እስከ ግንቦት 20 ቀን 2018 ዓ/ም ➡️ ግንቦት 19 ኢድ አልአድሃ
- የቅድመ ምረቃ ትምህርት መውጫ ፈተና ከሰኔ 2 እስከ ሰኔ 12 ቀን 2018 ዓ/ም
- የድህረ ምረቃ ትምህርት መግቢያ ፈተና (NGAT) ከሃምሌ 29 እስከ ሃምሌ 30 ቀን 2018 ዓ/ም
- የመሰረታዊ የንባብና የስሌት ክህሎት ምዘና ጥናትና ምርምር መረጃ መሰብሰብ ከሚያዚያ 26 እስከ ግንቦት 7 ቀን 2018 ዓ/ም ... ይሰጣል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን) #getutemesgen #getu #tikvah #education #exam #12grade #graduated

3 months ago
#exitexamresult
ከየካቲት 18-27/2018 ዓ.ም የተሰጠው የ2018 ዓ.ም አጋማሽ የከፍተኛ ትምህርት የመውጫ ፈተና ውጤት ተለቋል።
ውጤትዎን ለማየት 👇
https://result.ethernet.ed...
ሊንኩን ከተጫኑ በኋላ 'Exit Examination' ላይ 'View Results' የሚለውን በመጫንና Username በማስገባት ውጤትዎን ይመልከቱ።

4 months ago
#exitexamschedule : የ2018 አጋማሽ ዓመት የከፍተኛ ትምህርት የመውጫ ፈተና መስጫ የጊዜ ሰሌዳ ከላይ በፋይል ተያይዟል።
የ2018 ዓ.ም አጋማሽ ዓመት የመዉጫ ፈተና (Exit Exam) ከየካቲት 16 እስከ 27/2018 እንደሚሰጥ መገለፁ ይታወቃል።
seledadotio
seledadotio
የ2018 ዓ.ም አጋማሽ ዓመት የመዉጫ ፈተና (Exit Exam) ከየካቲት 16 እስከ 27/2018 እንደሚሰጥ መገለፁ ይታወቃል።
seledadotio
seledadotio
4 months ago
የ2018 ዓ.ም አጋማሽ ዓመት የመዉጫ ፈተና (Exit Exam) ከየካቲት 16-27/2018 ዓ.ም እንደሚሰጥ መገለፁ ይታወቃል።
ፈተናው አንድ ሳምንት ብቻ የቀረው ሲሆን፤ አሁን ላይ ዩኒቨርሲቲዎች የመውጫ ፈተና መለማመጃ (Mock Exam) በመስጠት ላይ ይገኛሉ፡፡
ዕጩ ተፈታኞች የፈተናው የይለፍ ካርድ እና ፋይዳ መታወቂያ ማዘጋጀታችሁን እንዳትዘነጉ፡፡ Via_tikvah
seledadotio
seledadotio
ፈተናው አንድ ሳምንት ብቻ የቀረው ሲሆን፤ አሁን ላይ ዩኒቨርሲቲዎች የመውጫ ፈተና መለማመጃ (Mock Exam) በመስጠት ላይ ይገኛሉ፡፡
ዕጩ ተፈታኞች የፈተናው የይለፍ ካርድ እና ፋይዳ መታወቂያ ማዘጋጀታችሁን እንዳትዘነጉ፡፡ Via_tikvah
seledadotio
seledadotio
4 months ago
ለ12ኛ ክፍል ተፈታኞች፦ ፈተናው በበይነ-መረብ (Online) ብቻ ይሆናል!
የዘንድሮው (2018 ዓ.ም) የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና 100% በበይነ-መረብ (Online) ለመስጠት መወሰኑን ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል።
የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ የግማሽ ዓመት አፈፃፀም መድረክ ላይ እንደገለጹት፣ ባለፉት ሁለት ዓመታት በከፊል ሲሞከር የነበረው የኦንላይን ፈተና ዘንድሮ ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ይደረጋል።
🔍 ዋና ዋና ነጥቦች እና የተደረጉ ዝግጅቶች፡-
ቴክኒካዊ ዝግጅት፡ በፈተና ጣቢያዎች አስተማማኝ የኢንተርኔት አገልግሎት እንዲኖር ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር የጋራ ስምምነት ተደርጓል።
የግብዓት አቅርቦት፡ ክልሎች የኮምፒውተር፣ የኔትወርክ መሠረተ ልማት እና አማራጭ የኃይል አቅርቦት (Generator/UPS) እንዲያሟሉ ጥብቅ መመሪያ ተሰጥቷል።
የተማሪዎች ስልጠና፡ ተማሪዎች ከሲስተሙ ጋር እንዲላመዱ የዲጂታል ትምህርትና አይሲቲ ሥራ አስፈፃሚ ዘላለም አሰፋ (ዶ/ር) እንደገለጹት በቂ የሞዴል (Model Exam) ፈተናዎች ተዘጋጅተዋል።
💡 ተማሪዎችና ወላጆች ሊያውቋቸው የሚገቡ ጥቅሞች፡-
ፍትሃዊነት፡ የኦንላይን ፈተና የፈተና ስርቆትን (Leakage) እና ኩረጃን ሙሉ በሙሉ ለማስቀረት ይረዳል።
ፈጣን ውጤት፡ ውጤትን ለማረም የሚወስደውን ጊዜ ስለሚያሳጥር፣ ተማሪዎች ውጤታቸውን በተሻለ ፍጥነት እንዲያውቁ ያስችላል።
ዝግጁነት፡ ተማሪዎች ማንኛውም ቴክኒካዊ ችግር እንዳይገጥማቸው ከፈተናው በፊት በቂ ስልጠና እንደሚሰጣቸው ተገልጿል።
ማሳሰቢያ፦ ክልሎችና የከተማ መስተዳድሮች ለፈተናው ስኬታማነት አስፈላጊውን የኮምፒውተር እና የኔትወርክ ድጋፍ እንዲያደርጉ ሚኒስቴሩ ጥሪ አቅርቧል።
ተማሪዎች አሁኑኑ በየሳምንቱ የሚለቀቁ የኦንላይን ሞዴል ፈተናዎችን በመለማመድ ራሳችሁን እንድታዘጋጁ ይመከራል።

የፋይዳ መታወቂያ ያውጡ!
ማንኛውም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች የብሔራዊ መታወቂያ (ፋይዳ) ማውጣት እንዳለባቸው ትምህርት ሚኒስቴር አቅጣጫ መስጠቱ ይታወቃል፡፡
ይህንንም ተከትሎ የመንግሥት እና የግል ዩኒቨርሲቲዎች የሁለተኛ ዓመት እና ከዚያ በላይ ተማሪዎቻቸው በሙሉ የብሔራዊ መታወቂያ (ፋይዳ) እንዲያወጡ እያደረጉ ነው፡፡
ብሔራዊ መታወቂያው ለምዝገባ፣ ለፈተና እንዲሁም ለተለያዩ የግቢ ውስጥ አግልጋሎቶች ግዴታ እንደሚሆንም እየተገለፀ ነው፡፡
የመውጫ ፈተና (Exit Exam) ለመውሰድ፣ ሀገር አቀፍ የድኅረ-ምረቃ መግቢያ ፈተና (NGAT) ለመፈተን፣ የብቃት ምዘና ፈተና (Licensing Exam) ለመውሰድ እንዲሁም በ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና (ESSLCE) ለመውሰድ ብሔራዊ መታወቂያ ማውጣት የግድ እንደሆነ በመንግሥት መገለፁ ይታወቃል፡፡

5 months ago
#exitexam
የመውጫ ፈተና (Exist Exam) የሚሰጥበት ጊዜ ከየካቲት 16 እስከ የካቲት 27 ቀን 2018 ዓ.ም መሆኑ ተገለጸ።
የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ባወጣው መርሃ-ግብር መሰረት፣ የ2018 ትምህርት ዘመን አጋማሽ የከፍተኛ ትምህርት መውጫ ፈተና (Exit Exam) ከየካቲት 16 - 27 ቀን 2018 ዓ.ም ይሰጣል።
ይህንን የፈተና ፕሮግራም ተቋማት ለተማሪዎቻቸው እያሳወቁ ይገኛሉ።

ትኩረት ለተመራቂ ተማሪዎች፦ የ2018 አጋማሽ የብቃት መመዘኛ (Exit Exam) መርሃ-ግብር ይፋ ሆነ
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ትምህርታቸውን አጠናቀው ወደ ስራው ዓለም ለመቀላቀል የሚወስዱት የመውጫ ፈተና (Exit Exam) የሚሰጥበት ትክክለኛ ቀን መወሰኑን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አስታውቋል።
📅 የፈተናው የጊዜ ሰሌዳ፦
የፈተና መጀመሪያ፦ የካቲት 16 ቀን 2018 ዓ.ም
የፈተና ማጠቃለያ፦ የካቲት 27 ቀን 2018 ዓ.ም
የፈተናው አሰጣጥ፦ ፈተናው በበይነ-መረብ (Online) የሚሰጥ ሲሆን፣ ተማሪዎች በተመደቡባቸው የኮምፒውተር ማዕከላት ተገኝተው ፈተናውን ይወስዳሉ።
የተፈታኞች መታወቂያ፦ ተፈታኞች ፈተናው ከመጀመሩ በፊት የፈተና መግቢያ ካርድ (Admission Card) እና የተቋሙን መታወቂያ መያዛቸውን ማረጋገጥ ይኖርባቸዋል።
የሙከራ ፈተና (Mock Exam)፦ ተማሪዎች ከሲስተሙ ጋር እንዲላመዱ እና የቴክኒክ ችግሮችን ቀድሞ ለመለየት፣ ከዋናው ፈተና ጥቂት ቀናት ቀደም ብሎ የሙከራ ፈተና ሊሰጥ ስለሚችል ዝግጁ መሆን ያስፈልጋል።
የውጤት አሰጣጥ፦ የመውጫ ፈተናው ተማሪዎች በስራው ዓለም ብቁ መሆናቸውን ማረጋገጫ በመሆኑ፣ ማለፊያ ውጤት ያላመጡ ተማሪዎች በድጋሚ የመፈተን እድል ቢኖራቸውም ዲግሪያቸውን ለመቀበል ውጤቱን ማለፍ ግዴታ ነው።
💡 ማሳሰቢያ፦ ተማሪዎች የየተቋሞቻቸውን የውስጥ ማስታወቂያዎች በቅርበት በመከታተል፣ የተመደቡበትን ላብራቶሪ (Lab) እና የፈተና ክፍለ-ጊዜ (Shift) ቀድመው እንዲያውቁ ይመከራል።
#exitexam #ethiopia #education #ministryofeducation #exitexam2018

በ2018 ዓ.ም አጋማሽ የመውጫ ፈተና (Exit Exam) ተፈታኞች የፈተና ጊዜ ተራዝሟል፡፡
ትምህርት ሚኒስቴር ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በጻፈው ደብዳቤ የዚህ ዓመት አጋማሽ የመውጫ ፈተና ከጥር 14/2018 ዓ.ም ጀምሮ እንደሚሰጥ ማስታወቁ ይታወሳል።
ነገር ግን "ከፈተና ዝግጅት ሥራዎች ጋር በተያያዘ ምክንያት" የፈተናው ቀን የተራዘመ መሆኑ ተገልጿል።
ምዝገባ ያደረጋችሁና በማድረግ ላይ የምትገኘ ተመዛኞች ፈተናው የሚሰጥበት ትክክለኛ ቀን በትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት / በትምህርት ሚኒስቴር እስከሚገለጽ ድረስ በትዕግስት አንድትጠብቁ ተብሏል።
(ከላይ የተያያዘው የምስል መረጃ ከወለጋ ዩኒቨርሲቲ የተገኘ ነው።)

8 months ago
የፋይዳ መታወቂያ ተመዝጋቢዎች ቁጥር ከ26 ሚሊዮን 500 ሺሕ በላይ መድረሱ ተገለጸ
👉 በመጪዎቹ ቅዳሜ እና እሁድ በመላ ሀገሪቱ የፋይዳ መታወቂያ ምዝገባ ዘመቻ ይካሄዳል ተብሏል
የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ አገልግሎት መሰጠት ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ እስከ አሁን ድረስ ከ26 ሚሊዮን 500 ሺሕ በላይ ነዋሪዎች መመዝገባቸውን የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ለአሐዱ አስታውቋል።
አብዛኞቹ አገልግሎቶች ከፋይዳ መታወቂያ ጋር እየተሳሰሩ መምጣታቸውን ተከትሎ፤ በርካታ ነዋሪዎች በመታወቂያው ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማድረግ ሲሰራ መቆየቱን፤ በብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም የባለድርሻ አካላት እና የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ሳሚናስ ሰይፉ ተናግረዋል።
የፋይዳ መታወቂያ የፋይናንስ ተቋማትን ጨምሮ በርካታ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ላይ የሚስተዋለውን ማጭበርበርና ሕገ-ወጥ የሆነ አሰራር በመከላከል ከደንበኞቻቸው ጋር መተማመን እንዲኖር የሚያስችል መሆኑን ገልጸዋል።
ተቋማት መታወቂያውን በመጠቀም የደንበኞቻቸውን ሙሉ ማንነት ከመለየት ባሻገር የሚኖረውን መተማመንና የአገልግሎት ጥራትን እንደሚያዘምን ተናግረዋል።
ይህ አሰራር የፋይናንስ ስርዓቱ ላይ በተለይም ባንኮች ላይ አዲስ ሂሳብ ማስከፈትን ጨምሮ ተግባራዊ እየሆነ በመምጣቱ ጥሩ የሆኑ ለውጦች መገኘታቸውን ያነሱ ሲሆን፤ በአጠቃላይ እስከ አሁን ባለው ሂደት ከ26 ሚሊዮን 500 ሺሕ በላይ ነዋሪዎች መመዝገባቸውን ገልጸዋል።
ዳይሬክተሩ አያይዘውም በዘንድሮው በጀት ዓመት ማለትም ከሐምሌ 1 ቀን 2017 ዓ.ም እስከ ሰኔ 30 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ 40 ሚሊዮን ተጨማሪ ነዋሪዎችን ለመመዝገብ መታቀዱን አስታውቀዋል።
የዚሁ በጀት ዓመት የመጀመሪያው ሩብ ዓመት መጠናቀቁን በመግለፅ፤ በዚህም ጥሩ የሆነ አፈፃፀም መገኘቱን አመላክተዋል።
በበጀት ዓመቱ አጠቃላይ 40 ሚሊዮን ነዋሪዎችን ለመመዝገብም ከተለያዩ የመንግሥትና የግል ተቋማት ጋር ትስስር በመፍጠር እንዲሁም የማህበረሰቡን ግንዛቤ በማስፋት እየተሰራ እንደሆነ ተናግረዋል።
ይህንንም ተግባራዊ ለማድረግ ነገ ጥቅምት 15 ቅዳሜ እና ጥቅምት 16 ማለትም እሁድ በልዩነት የ12ኛ ክፍል ተማሪዎችንና ግብር ከፋዮችን እንዲሁም ሌሎች የተለያዩ የማህበራዊ አገልግሎት ተጠቃሚውን ህብረተሰብ ታሳቢ ያደረገ የፋይዳ መታወቂያ የምዝገባ ዘመቻ እንደሚካሄድ አስታውቀዋል፡፡
የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናን ለሚወስዱ ተማሪዎች የፋይዳ መታወቂያን መያዝ ግዴታ መደረጉን ያነሱት ዳይሬክተሩ፤ በመሆኑም በዋናነት እነዚህን ተማሪዎች ጨምሮ የመውጫ ፈተናን (exit exam) የሚወስዱና የሁለተኛ ድግሪ መግቢያ ተፈታኞችን ታሳቢ ያደረገ ዘመቻ እንደሚካሄድ አስታውቀዋል።
በተጨማሪም ፋይዳ መታወቂያ ተግባራዊ ከመደረጉ አስቀድመው የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያወጡ ግለሰቦችና ተቋማት ከፋይዳ መታወቂያቸው ጋር እንዲያስተሳስሩ ለማድረግ የሚያስችል የኦንላይን አሰራር በቅርቡ ሥራ ላይ እንደዋለ ገልጸዋል።
የሁለት ቀኑ ዘመቻም ከተማሪዎች ባሻገር ይህንን አሰራር የበለጠ ለማጠናከር የሚደረግ እንደሆነ ተናግረዋል።
ከዚህም ሌላ በልዩ ሁኔታ የከተማ ሴፍቲኔት እና የጤና መድህን ተጠቃሚዎችን ለመመዝገብ እና በአጠቃላይ የፋይዳ መታወቂያ ተመዝጋቢዎችን ቁጥር ለመጨመር ታሳቢ ያደረገ ነው ብለዋል።
በዚህም መሰረት ከሰኞ እስከ አርብ ባለው ጊዜ ውስጥ አብዛኛው ሰው ሥራ ላይ እንደሚሆን ከግምት ውስጥ በማስገባት፤ ከሥራ ሰአት ውጪ ቅዳሜና እሁድ በሁሉም የሀገሪቱ ክፍል የሚገኙ የምዝገባ ጣቢያዎች ክፍት ሁነው አገልግሎት እንደሚሰጡ አስታውቀዋል።
የክልል ተቋማትና የከተማ አስተዳደሮችም ህብረተሰቡን መቀስቀስን ጨምሮ ለምዝገባው ስኬት ትብብር እንደሚያደርጉ ገልጸዋል።
በጊዜያዊነት የቅዳሜና እሁድ ምዝገባ የሚካሄደው ለአንድ ዙር ብቻ መሆኑን ያነሱት ዳይሬክተሩ፤ ወደፊት አፈፃፀሙ ታይቶ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል።
ዳይሬክተሩ አክለውም ለሁለት ቀን በሚደረገው ዘመቻ ሁሉም ህብረተሰብ ተጠቃሚ እንዲሆንና ምዝገባውን እንዲያከናውን ጥሪ አቅርበዋል።

ስለ ጡት ካንሰር እራስዎ ይማሩ፣ ለሌሎች የመማር እድል ይስጡ
ጥቅምት በዓለም ዙሪያ የጡት ካንሰር ግንዛቤ ማሳደጊያ ወር ተብሎ ይከበራል። በየዓመቱ በጥቅምት ወር፣ የጡት ካንሰርን ለመከላከል እንደ የግንዛቤ ምልክት የሚያገለግሉ ሮዝ ሪባን እንለብሳለን። ሮዝ ሪባን በመልበስ በአንድ በኩል በጡት ካንሰር ለሞቱት ሰዎች ክብር የምንሰጥ ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ ይህንን በሽታ በድፍረት እየተዋጉ ላሉት አክብሮት እና ድጋፍ እንገልጻለን።
በአለም ላይ ከግማሽ ሚልየን በላይ ሴቶች በበሽታው ይሞታሉ። ለዚህ ከፍተኛ የሞት መጠን ዋነኛ ምክንያቶች መካከል ወቅታዊ ምርመራ አለመኖር እና የህዝብ ግንዛቤ ማነስ ናቸው። በተለይም ሴቶች በማህበራዊ እፍረት፣ በሃፍረት እና በስህተት ግንዛቤ ምክንያት ችግሮቻቸውን በቅድመ-ደረጃዎች ውስጥ በሚስጥር ይይዛሉ፣ ይህም በሽታውን የሚያወሳስብ እና የሞት አደጋን ይጨምራል።
ምልክቶች : በአጠቃላይ በጡት ውስጥ አዲስ እብጠት ወይም ጠጣር ነገር መፈጠር፣ የጡት መጠን ወይም ቅርጽ ለውጥ፣ የቆዳ መገርጣት፣ መቅላት ወይም ማበጥ፣ ከጡት ጫፍ ያልተለመደ ደም ወይም ፈሳሽ መፍሰስ፣ በብብት ስር እብጠት መሰማት የመሳሰሉት ምልክቶች የጡት ካንሰር ምልክት ሊሆኑ ይችላሉ። እንደነዚህ ያሉ ምልክቶች ከተከሰቱ ችላ ሳይባሉ ወዲያውኑ የሕክምና ዕርዳታ መፈለግ አስፈላጊ ነው።
አደጋ : በእድሜ መጨመር፣ ፣ በቤተሰብ ታሪክ ውስጥ የጡት ካንሰር መኖር፣ ጥቅጥቅ ያለ የጡት ቲሹ፣ እንደ መደበኛ ያልሆነ የአመጋገብ ልማድ፣ ከመጠን ያለፈ ውፍረት፣ ማጨስ፣ አልኮል መጠጣት የመሳሰሉ የአኗኗር ዘይቤዎች ለጡት ካንሰር ያጋልጣሉ።
ምርመራ : የጡት ካንሰር ገና በለጋ ደረጃ ላይ ከታወቀ ሙሉ በሙሉ ሊድን ይችላል። ስለዚህ መደበኛ የጤና ምርመራ እና የግንዛቤ ማስጨበጫ ተግባራት ይህንን በሽታ ለመከላከል በጣም ውጤታማ መንገዶች ናቸው። በዚህ ረገድ ሦስት እርምጃዎች በተለይ አስፈላጊ ናቸው። በመጀመሪያ፣ 20 ዓመት እና ከዚያ በላይ የሆናቸው ሴቶች በወር አንድ ጊዜ የራስ-ጡት ምርመራ (self-breast examination) ማካሄድ አለባቸው። ጡትን በእጅ በመንካት እና በመስታወት በመመልከት የቅርጽ መዛባት፣ እብጠት፣ መቅላት፣ ሽፍታ ወይም የቆዳ መሸብሸብን ማወቅን ያካታል።ከ29 እስከ 39 ዓመት የሆናቸው ሴቶች ከ1 እስከ 3 ዓመት ባለው ጊዜ ውስጥ አንድ ጊዜ የጡት ካንሰር ምርመራ ማድረግ አለባቸው።ከ40 ዓመት በኋላ በየዓመቱ በባለሙያ ሐኪም የጤና ምርመራ ማድረግ አለባቸው። በተለይም በማሞግራፊ ምርመራ አማካኝነት በጡት ላይ ያለ ማንኛውንም ያልተለመደ ነገር ቀድሞ ማወቅ ይቻላል።
መከላከል እና ቁርጠኝነት
መከላከል : የጡት ካንሰርን ለመከላከል አንዳንድ ቀላል ግን ውጤታማ ልማዶችን ማዳበር ይቻላል። 'ካንሰር ቀድሞ ከታወቀ ይድናል' የሚለውን አስታውሱ፣ ይህም ማለት በጊዜ ከተገኘ የጡት ካንሰርን ሙሉ በሙሉ ማስወገድ ይቻላል። ስለዚህ ዛሬውኑ ግንዛቤ ይኑርዎት። ራስዎን ይወቁ፣ ሌሎች እንዲያውቁ እድል ይስጡ። የጡት ካንሰርን ግንዛቤ በማስፋፋት ስፍር ቁጥር የሌላቸውን ህይወት ማዳን እንችላለን—ይህም የእኛ ቁርጠኝነት መሆን አለበት።
በባንግልድሻዊው ዶክተር ሮውሻን አራ ቤገም የተፃፈ

አንድ ታላቅ ሰው ወደቀ !
ፕሮፌሰር አመዘነ ታደሰ ጥር 1 ቀን 1963 ዓም አዲስ አበባ ከተማ ተወለዱ። አባታቸው አቶ ታደሰ ሮበሌ ሲሆኑ እናታቸው ደግሞ ወ/ሮ (አሁን እማሆይ) እማሙ ገቢ ይባላሉ።
የመጀመሪያና መለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በሃዋሳ ታቦር የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ደግሞ በሃዋሳ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ያጠናቀቁ ከመሆናቸውም በላይ በ1980 ዓም የተሰጠውን ሃገር አቀፍ የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና ወይንም ESCLC እጅግ ከፍ ያለ ነጥብ በማምጣት በከፍተኛ ማዕረግ With Great Distinction ትምህርታቸውን አጠናቀዋል።
መንግስት በወቅቱ በሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና ከፍተኛ ነጥብ ያመጡ ተማሪዎችን በሚመድብበት የጎንደር ህክምና ሳይንስ ኮሌጅ ተመድበው በ1981 የ Common Course ትምህርታቸውን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሳይንስ ፋኩልቲ ካጠናቀቁ በኋላ ከ1982 ዓም ጀምሮ እስከ 1987 ድረስ ለስድስት ዓመታት የህክምና ትምህርታቸውን ተከታትለው በማዕረግ ወይም በ Distinction በሐኪምነት ለመመረቅ በቅተዋል።
ወደ ስራው አለም በመሰማራትም ከ1987 ዓም እስከ 1988 ዓም ድረስ በተመደቡበት የሆሳዕና ሆስፒታል በጠቅላላ ሐኪምነት፣ ከ1988 ዓም ጀምሮ ደግሞ ወደተማሩበት እና ወደተመረቁበት የጎንደር ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ዝውውር በማድረግ በቀዶ ጥገና ክፍል ረዳት መምህርነት እና ጠቅላላ ሐኪም በመሆን ለሶስት አመታት ወገኖቻቸውን አገልግለዋል።
ከዚያም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ስር በሚገኘው የጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ውስጥ የሚሰጠውን የሶስት ዓመታት የድህረ ምረቃ ትምህርት በመከታተል የቀዶ ጥገና ስፔሻሊስት ሐኪም ሆነው ከመመረቃቸውም በላይ የረዳት ፕሮፌሰርነት ማዕረግም አግኝተዋል። በመቀጠልም ህንድ ሃገር በሚገኘው ቬሎር ክርስቲያን ሜዲካል ኮሌጅ ውስጥ የፌሎውሺፕ ትምህርታቸውን ተከታትለው በ1999 ዓም የህፃናት ቀዶ ጥገና ሰብ ስፔሻሊስት በመሆን ተመርቀዋል።
ፕሮፌሰር አመዘነ ታደሰ ከዚህ ሁሉ ትምህርት ጎን ለጎን በህክምናው ዘርፍም ከተመረቁበት ጊዜ አንስቶ እስከ 1988 ዓም ድረስ የሆሳዕና ከተማ እና የአካባቢውን ማህበረሰብ፣ ከዚያም እስከ ህዳር 2002 ዓም ድረስ ደግሞ የጎንደር ከተማና የአካባቢውን ማህበረሰብ፣ ከ2002 ዓም በኋላ ደግሞ በአዲስ አበባ ከተማ ጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ውስጥ ከመላው ኢትዮጵያ የሚመጡ ህሙማንን በተለይም ደግሞ ህፃናት ታካሚዎችን ከፈጣሪያቸው በተሰጣቸው ጥበብና ፀጋ አማካይነት ቀዶ ጥገና በማከናወን እንዲፈወሱ የሚያደርጉ ደከመኝን የማያውቁ ታታሪ የህክምና ባለሙያና ምሁር ነበሩ።
በሌላ በኩል ደግሞ በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ለማስተማር የሚያስችላቸውን የከፍተኛ ዲፕሎማ ፕሮግራም Higher Diploma Program ተከታትለው ያጠናቀቁ ከመሆናቸውም በላይ በ2011 ዓም ደግሞ በጤና ባለሙያዎች ትምህርት Health Professional Education ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የማስተርስ ዲግሪ አግኝተዋል። ከዚሁ ጋር ተያይዞም የቀዶ ጥገና ተባባሪ ፕሮፌሰርነት ማዕረግም አግኝተዋል።
ፕሮፌሰር አመዘነ ታደሰ በርካታ ስልጠናዎችንና የአጭር ጊዜ ኮርሶችን የወሰዱ ሲሆን ከነዚህም መካከል ዋና ዋናዎቹ ከዚህ የሚከተሉት ናቸው።
እንግሊዝ ሃገር በሚገኘው Paediatric Surgery at Leicester Royal Infirmary,
እስራኤል ሃገር በሚገኘው University of Negev, Beersheba Soroka Medical Center,
ሲያትል አሜሪካ በሚገኘው University of Washington Institute of Simulation and Interpersonal Skills, Royal College of Surgeons of England and David Nutt Foundation በጋራ ባዘጋጁት Surgery in Austere Environment Course in Manchester University,
እንግሊዝ ሃገር በሚገኘው Global Surgery Course at University of Oxford ይጠቀሳሉ።
ፕሮፌሰር አመዘነ በሰሩባቸው ተቋማት ውስጥ ህክምና ከመስጠት ጎን ለጎን በተለያዩ ደረጃዎች ሃገራቸውን ሲያገለግሉ ቆይተዋል። ከነዚህም ውስጥ በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የቀዶ ጥገና ክፍል ሃላፊ፣ በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ውስጥ የህፃናት ቀዶ ጥገና ክፍል ሃላፊ፣ የSurgical Skills Lab ተባባሪ ዳይሬክተር፣ የSimulation Center of College of Social Sciences ተባባሪ ሊቀመንበር፣ በድህረ ምረቃ ትምህርት ክፍል የድህረ ምረቃ ኮሚቴ ሊቀመንበር፣ የኢትዮጵያ ህክምና ማህበር ምክትል ፕሬዘዳንት፣ የምስራቅ፣ መካከለኛው እና ደቡባዊ አፍሪካ የህፃናት ቀዶ ጥገና ፕሮግራም Panel Head፣ እንዲሁም የአሜሪካ የቀዶ ህክምና ኮሌጅ አባል ነበሩ።
በአካዳሚክ ዘርፉም በጎንደር ዩኒቨርሲቲ፣ በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ፣ በመቀሌ ዩኒቨርሲቲ፣ በጅማ ዩኒቨርሲቲ፣ በአርሲ ዩኒቨርሲቲ እና በሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ ለቅድመ ምረቃ እና ድህረ ምረቃ External Examiner የነበሩ ሲሆን የቀብሪ ደሃር ዩኒቨርሲቲ የቦርድ አባል በመሆን አገልግሎት እየሰጡ ነበር። ከዚህም በተጨማሪ ሞምባሳ ኬንያ፣ ማፑቶ ሞዛምቢክ፣ ኪጋሊ ሩዋንዳ እንዲሁም ካምፓላ ዩጋንዳ ለሚገኙ የህክምና Examiners በተለያዩ ጊዜያት ስልጠና ሲሰጡ ቆይተዋል።
በምርምር ረገድም 34 አርቲክሎችን እና የመፅሃፍ ክፍሎችን አገር አቀፍ እና አለም አቀፍ እውቅና ባላቸውና በተገመገሙ ጆርናሎች ላይ ፅሁፎቻቸውን ከማሳተማቸውም በላይ ስድስት ፅሁፎቻቸው ለመታተም በሂደት ላይ ነበሩ። ከዚሁ ጋር ተያይዞም የተወሰኑ ፅሁፎቻቸውን በሃራሬ ዚምባቡዌ እንዲሁም በካልጋሪ ካናዳ ያቀረቡ ሲሆን የ Surgical Platform የኢትዮጵያ ተወካይ እና Health System Strengthening in Sub-Saharan Africa በሚለው የ ASSET project ውስጥ ተባባሪ ተመራማሪ ነበሩ።
ፕሮፌሰር አመዘነ ታደሰ ከዚህ በላይ ለተጠቀሱት ዋና ዋና እና ሌሎችም አገልግሎታቸው ከበርካታ ተቋማት ሽልማቶች የተበረከቱላቸው ሲሆን ከነዚህም መካከል
Award for Presenting Best Scientific Paper entitled ‘Implementing Ultrasound Guided Hydrostatic Reduction of Intussusception in a Low Resource Countries, Larry J. Anderson Award for Outstanding Public Health Science in the United States of America, Winner of International Guest Scholars by the American College of Surgeons, Chicago, USA ዋና ዋናዎቹ ናችው።
በአጠቃላይ በህፃናት ቀዶ ጥገና በሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ በሃገራችን ከሚገኙት ሁለት የህክምና ምሁራን ውስጥ አንዱ ፕሮፌሰር አመዘነ ታደሰ ነበሩ።
በመጨረሻም ፕሮፌሰር አመዘነ ታደሰ ከትምህርታቸው እና ስራቸው ባሻገር ባለው ህይወታቸውም ከዶ/ር ራሔል ደምሰው ጋር ከ2003 ዓ.ም ጀምሮ በትዳር በመጣመር ደስተኛ ህይወት ይመሩ የነበረ ሲሆን ከዚሁ ትዳራቸውም ሁለት ወንዶች ልጆች እና አንዲት ሴት ልጅ በድምሩ ሶስት ልጆችን አፍርተዋል።
ከዚህ ሁሉ ልፋት በኋላ እኚህ የሚሊዮኖችን ህይወት ሲታደጉ የኖሩት የሃገር መድሐኒት ለራሳቸው የሚሆን መድሐኒት ሊያገኙ ባለመቻላቸው ባደረባቸው ህመም ምክንያት በአሜሪካን ሃገር እና በኢትዮጵያ ውስጥ በህክምና ሲረዱ ቢቆዩም የፈጣሪ ጥሪ ደርሷቸው በርካታ አገልግሎት ሊሰጡ በሚችሉበት ዕድሜ ላይ እያሉ ጥቅምት 5 ቀን 2018 ዓም ልክ ከረፋዱ 5 ሰዓት ከሩብ ላይ በተወለዱ በ54 ዓመት ዕድሜያቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።
የፕሮፌሰር አመዘን ታደሰ አስክሬን ሽኝት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ፡ ጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ተካሂዷል ፣ሥርዓተ ቀብራቸው አርብ ጥቅምት 7/2018 ዓ,ም በሀዋሳ ከተማ ይፈፀማል ።
ልዑል እግዜብሔር ነፍሳቸውን በአፀደ ገነት ያኑርልን፣ አሜን።

Unlock your child's potential!!
ልጅዎን ቤት ለ ቤት ወይንም ባሉበት ሆነው ማብቃት ይፈልጋሉ? እንግዲያውስ Tech tutor / ቴክ አስጠኝን ይቀላቀሉ።
የኛን አገልግሎት ሲመርጡ ምን ይጠቀማሉ :
👉 ብቃት ያላቸው መምህራንን በቤተዎ ወይንም ባሉበት ሆነው ልጅዎን ማብቃት።
👉 በግል ወይነም በጋራ
📌 Home-to-home tutors
📌 GAT,
📌 Remedial,
📌 Exit exam
📌 Computer skill
📌 Coding መዘጋጀት።
📌 Website development, Database, Software development, IA, Security , Networking, ERP...
👉ከ አዲስ አበባ ውጪ ያላችሁትን ጨምሮ የለ ቦታ ገደብ ልጅዎን ማብቃት እና ተወዳዳሪ ማድረግ።
👉ልጅዎ ከኮምፒውተር (ቴክኖሎጂ) ጋር ሚኖረው ቁርኝት ይዳብራል ።
ማሳሰቢያ ✍️
የ online አገልግሎት ለመጠቀም ኮምፒውተር ወይም ስማርት ስልክ እና ኢንተርኔት ሊኖረዎ ይገባል ።
ለመመዝገብ:-
ከዚህ በታች ባለው ስልክ ቁጥር እና የቴሌግም አድራሻ ያናግሩን
Phone number 👉 +2519 42 95 06 37 / +2519 34 76 83 05
ቴሌግራም 👉t.me/Techtutors1
👉https://forms.gle/Pn481Bq2...
አድራሻ :- ልደታ MB center 4 ወለል። #techtutor #smartlearning #digitalskills #futureready #learnwithexperts #edtech #codingforall #innovationstartshere

9 months ago
Global Korea Scholarship 2026 | Fully Funded | Study in Korea
No. of Scholarships: 280
Link: https://scholarshipscorner...
Scholarships for Undergraduate Degrees
Benefits:
Tuition fees covered
One year of Korean language training
Round-trip airfare
Monthly allowance (includes living expenses, health insurance, Korean proficiency grants, settlement allowance, TOPIK exam fee coverage, and a degree completion grant)

የ 2017 ዓ.ም የ 12ኛ ክፍል Entrance Exam ተፈታኞች መካከል ከፍተኛውን ውጤት ያመጣው ተማሪ ይሄ ልጅ ነው። 591 / 600 ነው ያመጣው።
ከ 6 Subject ውስጥ አምስቱን 100 አምጥቶ ባዮሎጂ ላይ ብቻ ነው 9 ኤክስ የገባበት። Amazing..! ❤
seledadotio
ከ 6 Subject ውስጥ አምስቱን 100 አምጥቶ ባዮሎጂ ላይ ብቻ ነው 9 ኤክስ የገባበት። Amazing..! ❤
seledadotio
10 months ago
ጂቲቲፍ (GTTF) ማርሻል አርት ስልጠና እና ዉድድር ተጀመረ
#fastmereja I በ193 ሀገራት ዓለም አቀፍ እውቅና ያለው ጂቲቲኤፍ በኢትዮጵያ ሌጀንድ ኢንተርናሽናል ፕሮፌሽናል ቴኳንዶ አሶሴሽን እና በጂቲቲፍ አዘጋጅነት የማርሻል አርት ስልጠና እና ዉድድር ዛሬ በካፒታል ሆቴል ተጀመረ::
እስከ ነሀሴ 4/2017 ዓ.ም በካፒታል ሆቴል የሚካሄደው ስልጠና በዓለም አቀፍ ደረጃ ተጽኖ ፈጣሪ የሆኑ አሥራ ሦስት ታዋቂ ባለሙያዎች ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት ትልቅ የልምድ ልውውጥ እና የጂቲቲፍ ፈተና (GTTF Dan Exam) የሚሰጡ ይሆናል።
በስልጠናው ከ250 በላይ ሰዎች ተሳታፊ ሲሆኑ ከስልጠናው በኃላ ውድድሩን ለሚያሸንፉ የገንዘብ ሽልማት ይሰጣል ተብሏል።

11 months ago
ሌጀንድ ኢንተርናሽናል ፕሮፌሽናል ታይኳንዶ ግሩፕ አብረውን መስራት ለሚፈልጉ ሁሉ ጥሪ አቀረበ
#ethiopia | በኢትዮጵያ ሌጀንድ ኢንተርናሽናል ፕሮፌሽናል ቴኳንዶ አሶሴሽን እና በጂቲቲፍ አዘጋጅነት ለ5 ቀናት የሚቆይ ስልጠና እና ውድድር ከሐምሌ 30 እስከ ነሐሴ 4 ቀን 2017 ድረስ መዘጋጀቱ ተገልጿል፡፡
ስልጠና እና ውድድሩን አስመልክቶ በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ፤ በስልጠናው ላይ 193 ሀገራትን የሚወክሉ በዓለም አቀፍ ደረጃ ትልቅ እውቅና ያላቸው እና በዘርፉ ላይ ተጽኖ ፈጣሪ የሆኑ ባለሙያዎች እውቀታቸውንና ልምዳቸውን እንደሚያካፍሉ የተገለጸ ሲሆን፤ የጂቲቲፍ ፈተና ወይንም (Global traditional taekwondo federation DANE EXAM) ይሰጣሉ ተብሏል።
ለዚህ ስልጠና እና ውድድር እስካሁን ከ250 በላይ ሰዎች የተመዘገቡ ሲሆን፤ አሸናፊ ለሚሆኑትም ሽልማት ይበረከትላቸዋል ተብሏል።
193 ሀገራትን ወክለው የሚመጡት አሰልጣኞች ለ7 ቀናት እንደሚቆዩ የተነገረ ሲሆን፤ በቆይታቸውም በስፖርቱ፣ በቱሪዝሙ፣ በኢንቨስትመንቱ እና በሌሎች የሥራ ዘርፎች ላይ በርካታ ሥራዎችን ለመስራት በማለም ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ ተገልጿል፡፡
የዓለም የጂቲቲኤፍ ም/ፕሬዚዳንት እና የELIPTA ፕሬዝዳንት የሆኑት ዶክተር ግራንድ ማስተር ሄኖክ ግርማ በመድረኩ የመክፈቻ እና የመዝጊያ ንግግር ያደረጉ ሲሆን፤ በንግግራቸውም "የዚህ ስልጠና እና ውድድር መዘጋጀት በዘርፉ ከሚያበረክተው አስተዋጽኦ ባሻገር ለሀገራችን ኢትዮጵያ የመልካም ገጽታ ግንባታ ትልቅ ዋጋ አለው" ብለዋል
ሌጀንድ ኢንተርናሽናል ፕሮፌሽናል ግሩፕ በ1998 ዓ/ም ተመስርቶ ለዓመታት ብዙ ሥራዎችን ሲሰራ ከቆየ በኋላ፤ በ2016 ዓ/ም በኢትዮጵያ ሕጋዊ እውቅና አግኝቶ በማርሻል አርት ስልጠና፣ በጂም ፊትነስ (የአካል ብቃት እንቅስቃሴ) አመርቂ ሥራ ሰርቷል ተብሏል።

ዓለም አቀፍ እውቅና ያለው ጂቲቲፍ ማርሻል አርት ስልጠና እና ዉድድር በኢትዮጵያ ይካሄዳል።
#fastmereja I በ193 አገራት አለም አቀፍ እውቅና ያለው ጂቲቲፍ (GTTF) ማርሻል አርት ስልጠና እና ዉድድር ከሐምሌ 30 - ነሀሴ 4/2017 ዓ.ም በኢትዮጵያ እንደሚካሄድ አዘጋጆቹ ሌጀንድ ኢንተርናሽናል ፕሮፌሽናል ቴኳንዶ አሶሴሽን ዛሬ በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል።
በዓለም አቀፍ ደረጃ ተጽኖ ፈጣሪ የሆኑ 13 ታዋቂ ባለሙያዎች ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት ትልቅ የልምድ ልውውጥ እና የጂቲቲኤፍ ፈተና (GTTF Dan Exam) የሚሰጡ ሲሆን ውድድሩን ለሚያሸንፉ የገንዘብ ሽልማት እንደሚሰጥ ተገልጿል።
በስልጠናው እስካሁን ከ250 በላይ ሰዎች የተመዘገቡ ሲሆን።
ሌጀንድ ኢንተርናሽናል ፕሮፌሽናል ግሩፕ ከተመሰረተበት ከ1996 ዓ.ም ሕጋዊ እውቅና አግኝቶ በሀገር ውስጥ በርካታ ስራዎችን የሚሰራ ሲሆን እነዚህም በማርሻል አርት ሥልጠና፤ በጂም ፊትነስ (የአካል ብቃት እንቅስቃሴ)፤ በሪል ስቴት ፕሮፐርቲ ማናጅመንት፤ በሆም ላንድ ሴኩሪቲ፤ በሜዲካል ኮንሰልተንሲ ፤ በሜዲካል ቱሪዝም እና ተያያዥ ስራዎችን በመስራት ላይ ያለ ድርጅት ነው ፡፡

የሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ የመውጫ ፈተና ማጭበርበር ቅሌትና የቀጠለው ውዝግብ
የሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ የ2017 የመውጫ ፈተና (Exit Exam) ጋር በተያያዘ የሰባት (7) ባለሥልጣናት ሚስቶች፣ የክልሉ ፕሬዚዳንት ባለቤት ጨምሮ፣ ባልተለመደ ሁኔታ 100% ውጤት ማምጣታቸው ከፍተኛ ውዝግብ ፈጥሯል።
ይህ ፈተና ከትምህርት ሚኒስቴር አሰራርና ከዩኒቨርሲቲው እውቅና ውጪ በወንዶ ገነት ደንና የተፈጥሮ ሃብት ኮሌጅ ውስጥ በልዩ ሁኔታ መሰጠቱ ተጋልጧል። የኮሌጁ ማኔጂንግ ዳይሬክተር አቶ በላይ ባልጉዳ በማመቻቸት፣ ተፈታኞች ስልክና ChatGPT (AI) በመጠቀም በልዩ ክፍል ውስጥ ፈተናውን እንደወሰዱ ተጠቁሟል።
የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶ/ር ችሮታው አየለ ባደረጉት ማጣራት፣ ሁለት (2) የICT ባለሙያዎች (አቶ አስፋው አሻንጎ እና አቶ አዱኛ ጌታቸው) ከሥራ ሲታገዱ፣ የአቶ በላይ ባልጉዳ እና የኮሌጁ ዲን ዶ/ር ተሻለ ወ/አማኑኤል ጉዳይ በምርመራ ላይ ይገኛል።
ይህ ክስተት ከቀድሞ ፕሬዚዳንት ዶ/ር አያኖ ባራሶና አቶ በላይ ባልጉዳ ጋር የተያያዘ የዩኒቨርሲቲው ሙስና ታሪክ አካል እንደሆነ እየተነገረ ነው። ዶ/ር ችሮታው አየለ እያደረጉት ያለው ማሻሻያ ደስ ያላላቸው የቀድሞ አመራሮችና ግብረ አበሮቻቸው በዩኒቨርሲቲው ላይ የሐሰት ዘመቻ ከፍተዋል ተብሎም ይታመናል። የሲዳማ ማህበረሰብም ዩኒቨርሲቲውን እንዲደግፍ እና በሙስና ፈጻሚዎች ላይ እርምጃ እንዲወሰድ ጥሪ ቀርቧል።
Source :- zena ethiopia
Seledadotio

ጃፓን በባህር ውሃ ውስጥ የሚሟሟ እና አፈርን የሚያበለጽግ አዲስ ፕላስቲክ ፈጠረች
በጃፓን የሪከን ማዕከል (RIKEN Center) እና የቶኪዮ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎች በአዲስ መልክ የተሰራ ባዮዲግሬድድ (Biodegradable) ፕላስቲክ ይፋ አድርገዋል። ይህ ፕላስቲክ በሰዓታት ውስጥ በባህር ውሃ ውስጥ ሊሟሟ የሚችል ሲሆን፣ በአፈር ውስጥ ደግሞ በ10 ቀናት ውስጥ ሙሉ በሙሉ በመከፋፈል እንደ ፎስፈረስ እና ናይትሮጅን ያሉ ንጥረ ነገሮችን በመልቀቅ የአፈርን ለምነት ይጨምራል ነው የተባለው።
ይህ አዲስ ፕላስቲክ የተሰራው ከሶዲየም ሄክሳሜታፎስፌት (sodium hexametaphosphate) እና ከጉዋኒዲኒየም-መሰረት ካላቸው ሞኖመሮች (guanidinium-based monomers) ነው ተብሏል። ሲበሰብስ የማይክሮፕላስቲክ ቅሪት የማይተው፣ መርዛማ ያልሆነ እና 91 በመቶ እንደገና ጥቅም ላይ ሊውል የሚችል ነው ተብሏል፡፡
ይህ ፈጠራ ለእርሻ ስራ የሚያገለግሉ ቁሳቁሶች ፤ የአሳ ማጥመጃ መሳሪያዎች እና ለአካባቢ ጥበቃ ተስማሚ የሆኑ ማሸጊያዎች (eco-friendly packaging) ተስማሚ ነው ተብሏል፡፡
በመሆኑም የፕላስቲክ ብክለትን ለመቀነስ እና ዘላቂነት ያለው ግብርናን ለማሳደግ ወሳኝ ሚና ይጫወታል ተብሎ ይጠበቃል ተብሏል።

Comments