2 hours ago
ዶ/ር ቴዎድሮስ በደቡብ አፍሪካ በኢትዮጵያውያን
ላይ የተፈጸመውን አሳዛኝ የጥላቻ ጥቃት አወገዙ
#ethiopia | የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴዎድሮስ አድኃኖም ገብረኢየሱስ በደቡብ አፍሪካ በቅርቡ ያገረሸውንና በውጭ ዜጎች ላይ ያነጣጠረውን አሰቃቂ የመጤ ጥላቻ (Xenophobia) ጥቃት አጥብቀው ኮነኑ።
በጥቃቱ ሳቢያ ቢያንስ አምስት ኢትዮጵያውያንና አምስት የሞዛምቢክ ዜጎች ሕይወታቸው ማለፉን የገለጹት ዋና ዳይሬክተሩ፣ ድርጊቱን «እጅግ ልብ ሰባሪ» እና ደቡብ አፍሪካ ከአፓርታይድ ሥርዓት ለመውጣት በታገለችበት ወቅት አፍሪካውያንና በተለይም ኢትዮጵያ ለኔልሰን ማንዴላ ያሳዩትን ታሪካዊ አጋርነት የካደ «አሳዛኝ ድርጊት» ሲሉ ገልጸውታል።
ዶ/ር ቴዎድሮስ በማኅበራዊ ገጻቸው ባስተላለፉት መልእክትም፣ ማንኛውም ቅሬታ በሕግ የበላይነት እንጂ በቡድን ጥቃት መፈታት እንደሌለበት አሳስበው፣ ጥላቻው በአስቸኳይ እንዲቆምና ተጋላጭ ወገኖች ጥበቃ እንዲደረግላቸው ጥሪ አቅርበዋል።
በደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በተለይም «ኦፕሬሽን ዱዱላ» ከተሰኘው ንቅናቄ ጋር በተያያዘ ከሚሰነዘሩ የማግለልና የማጥቃት ቅስቀሳዎች የተነሳ በከፍተኛ ፍርሃትና ስጋት ውስጥ እንደሚገኙም ገልጸዋል።
የደቡብ አፍሪካ ባለሥልጣናት የዜጎችን ደኅንነት ለመጠበቅ ቃል ቢገቡም፣ የማስፈራራት፣ የአካላዊ ጥቃትና የዝርፊያ አደጋዎች አሁንም ቀጥለዋል።
የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርና የኤምባሲ ልዑካን ቡድን ከደቡብ አፍሪካ ባለሥልጣናት ጋር ተወያይተው ማረጋገጫ ማግኘታቸውንና ዲፕሎማሲያዊ ጥረት እያደረጉ መሆኑን ቢገልጹም፣ በአካባቢው የሚኖሩ አንዳንድ ስደተኞች ግን የመንግሥት ምላሽ ከችግሩ አጣዳፊነት አንጻር «የዘገየ» ነው ሲሉ ተችተዋል።
#stopxenophobia #southafrica #ethiopia #humanrights #africaunite #drtedros

Comments