የሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ የመውጫ ፈተና ማጭበርበር ቅሌትና የቀጠለው ውዝግብ
የሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ የ2017 የመውጫ ፈተና (Exit Exam) ጋር በተያያዘ የሰባት (7) ባለሥልጣናት ሚስቶች፣ የክልሉ ፕሬዚዳንት ባለቤት ጨምሮ፣ ባልተለመደ ሁኔታ 100% ውጤት ማምጣታቸው ከፍተኛ ውዝግብ ፈጥሯል።
ይህ ፈተና ከትምህርት ሚኒስቴር አሰራርና ከዩኒቨርሲቲው እውቅና ውጪ በወንዶ ገነት ደንና የተፈጥሮ ሃብት ኮሌጅ ውስጥ በልዩ ሁኔታ መሰጠቱ ተጋልጧል። የኮሌጁ ማኔጂንግ ዳይሬክተር አቶ በላይ ባልጉዳ በማመቻቸት፣ ተፈታኞች ስልክና ChatGPT (AI) በመጠቀም በልዩ ክፍል ውስጥ ፈተናውን እንደወሰዱ ተጠቁሟል።
የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶ/ር ችሮታው አየለ ባደረጉት ማጣራት፣ ሁለት (2) የICT ባለሙያዎች (አቶ አስፋው አሻንጎ እና አቶ አዱኛ ጌታቸው) ከሥራ ሲታገዱ፣ የአቶ በላይ ባልጉዳ እና የኮሌጁ ዲን ዶ/ር ተሻለ ወ/አማኑኤል ጉዳይ በምርመራ ላይ ይገኛል።
ይህ ክስተት ከቀድሞ ፕሬዚዳንት ዶ/ር አያኖ ባራሶና አቶ በላይ ባልጉዳ ጋር የተያያዘ የዩኒቨርሲቲው ሙስና ታሪክ አካል እንደሆነ እየተነገረ ነው። ዶ/ር ችሮታው አየለ እያደረጉት ያለው ማሻሻያ ደስ ያላላቸው የቀድሞ አመራሮችና ግብረ አበሮቻቸው በዩኒቨርሲቲው ላይ የሐሰት ዘመቻ ከፍተዋል ተብሎም ይታመናል። የሲዳማ ማህበረሰብም ዩኒቨርሲቲውን እንዲደግፍ እና በሙስና ፈጻሚዎች ላይ እርምጃ እንዲወሰድ ጥሪ ቀርቧል።
Source :- zena ethiopia
Seledadotio

11 months ago