Logo
Getu Temesgen
ሌጀንድ ኢንተርናሽናል ፕሮፌሽናል ታይኳንዶ ግሩፕ አብረውን መስራት ለሚፈልጉ ሁሉ ጥሪ አቀረበ
#ethiopia | በኢትዮጵያ ሌጀንድ ኢንተርናሽናል ፕሮፌሽናል ቴኳንዶ አሶሴሽን እና በጂቲቲፍ አዘጋጅነት ለ5 ቀናት የሚቆይ ስልጠና እና ውድድር ከሐምሌ 30 እስከ ነሐሴ 4 ቀን 2017 ድረስ መዘጋጀቱ ተገልጿል፡፡

ስልጠና እና ውድድሩን አስመልክቶ በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ፤ በስልጠናው ላይ 193 ሀገራትን የሚወክሉ በዓለም አቀፍ ደረጃ ትልቅ እውቅና ያላቸው እና በዘርፉ ላይ ተጽኖ ፈጣሪ የሆኑ ባለሙያዎች እውቀታቸውንና ልምዳቸውን እንደሚያካፍሉ የተገለጸ ሲሆን፤ የጂቲቲፍ ፈተና ወይንም (Global traditional taekwondo federation DANE EXAM) ይሰጣሉ ተብሏል።

ለዚህ ስልጠና እና ውድድር እስካሁን ከ250 በላይ ሰዎች የተመዘገቡ ሲሆን፤ አሸናፊ ለሚሆኑትም ሽልማት ይበረከትላቸዋል ተብሏል።

193 ሀገራትን ወክለው የሚመጡት አሰልጣኞች ለ7 ቀናት እንደሚቆዩ የተነገረ ሲሆን፤ በቆይታቸውም በስፖርቱ፣ በቱሪዝሙ፣ በኢንቨስትመንቱ እና በሌሎች የሥራ ዘርፎች ላይ በርካታ ሥራዎችን ለመስራት በማለም ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ ተገልጿል፡፡

የዓለም የጂቲቲኤፍ ም/ፕሬዚዳንት እና የELIPTA ፕሬዝዳንት የሆኑት ዶክተር ግራንድ ማስተር ሄኖክ ግርማ በመድረኩ የመክፈቻ እና የመዝጊያ ንግግር ያደረጉ ሲሆን፤ በንግግራቸውም "የዚህ ስልጠና እና ውድድር መዘጋጀት በዘርፉ ከሚያበረክተው አስተዋጽኦ ባሻገር ለሀገራችን ኢትዮጵያ የመልካም ገጽታ ግንባታ ትልቅ ዋጋ አለው" ብለዋል

ሌጀንድ ኢንተርናሽናል ፕሮፌሽናል ግሩፕ በ1998 ዓ/ም ተመስርቶ ለዓመታት ብዙ ሥራዎችን ሲሰራ ከቆየ በኋላ፤ በ2016 ዓ/ም በኢትዮጵያ ሕጋዊ እውቅና አግኝቶ በማርሻል አርት ስልጠና፣ በጂም ፊትነስ (የአካል ብቃት እንቅስቃሴ) አመርቂ ሥራ ሰርቷል ተብሏል።

1 year ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.