Logo
SeledaPost
የሬሜዲል ፈተና መስጫ ቀን ተራዘመ።

ከግንቦት 17 እስከ 20 ቀን 2018 ዓ/ም ሊሰጥ ፕሮግራም ወጥቶለት የነበረው የሬሜዲያል (የአቅም ማሻሻያ) ፈተና ከግንቦት 27 እስከ ሰኔ 3 ቀን 2018 ዓ/ም እንዲሰጥ ተራዝሟል።

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት " የሪሜዲያል ፈተና እና የቅድመ ምረቃ ትምህርት መውጫ ፈተና (Exit Exam) የሚሰጥበት ቀን ተቀይሯል " ብሏል።

" ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጋር ምክክር በማድረግ የሪሜዲያል እና EXIT EXAM ፈተናዎች የሚሰጥባቸው ቀናት ተሸጋሽጓል " ሲል አሳውቋል።

በዚህም የሬሜዲያ ፈተና ከግንቦት 27 እስከ ሰኔ 3 ቀን 2018 ዓ/ም ፤ የቅድመ ምረቃ መውጫ ፈተና ደግሞ ከሰኔ 4 እስከ ሰኔ 12 ቀን 2018 ዓ/ም እንደሚሰጥ ገልጿል።

seledadotio
seledadotio
25 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.