Logo
FastMereja
ዓለም አቀፍ እውቅና ያለው ጂቲቲፍ ማርሻል አርት ስልጠና እና ዉድድር በኢትዮጵያ ይካሄዳል።
#fastmereja I በ193 አገራት አለም አቀፍ እውቅና ያለው ጂቲቲፍ (GTTF) ማርሻል አርት ስልጠና እና ዉድድር ከሐምሌ 30 - ነሀሴ 4/2017 ዓ.ም በኢትዮጵያ እንደሚካሄድ አዘጋጆቹ ሌጀንድ ኢንተርናሽናል ፕሮፌሽናል ቴኳንዶ አሶሴሽን ዛሬ በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል።

በዓለም አቀፍ ደረጃ ተጽኖ ፈጣሪ የሆኑ 13 ታዋቂ ባለሙያዎች ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት ትልቅ የልምድ ልውውጥ እና የጂቲቲኤፍ ፈተና (GTTF Dan Exam) የሚሰጡ ሲሆን ውድድሩን ለሚያሸንፉ የገንዘብ ሽልማት እንደሚሰጥ ተገልጿል።

በስልጠናው እስካሁን ከ250 በላይ ሰዎች የተመዘገቡ ሲሆን።

ሌጀንድ ኢንተርናሽናል ፕሮፌሽናል ግሩፕ ከተመሰረተበት ከ1996 ዓ.ም ሕጋዊ እውቅና አግኝቶ በሀገር ውስጥ በርካታ ስራዎችን የሚሰራ ሲሆን እነዚህም በማርሻል አርት ሥልጠና፤ በጂም ፊትነስ (የአካል ብቃት እንቅስቃሴ)፤ በሪል ስቴት ፕሮፐርቲ ማናጅመንት፤ በሆም ላንድ ሴኩሪቲ፤ በሜዲካል ኮንሰልተንሲ ፤ በሜዲካል ቱሪዝም እና ተያያዥ ስራዎችን በመስራት ላይ ያለ ድርጅት ነው ፡፡

11 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.