12 days ago
በትግራይ ክልል የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና እየተሰጠ ነው
******************
የትግራይ ክልል ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና በአዲስ አበባ፣ በመቐለ እና በአክሱም ዩኒቨርሲቲዎች ማዕከላት በወረቀት እና በበይነ-መረብ መውሰድ ጀምረዋል።
በትምህርት ሚኒስቴር እና በፌዴራል መንግሥት የተደረገውን አጠቃላይ ርብርብ ተከትሎ አስፈላጊው የቅድመ ዝግጅት ሥራ ተጠናቅቆ ተማሪዎች ወደ ፈተና አዳራሾች ገብተዋል።
ተማሪዎቹ ያለምንም እንግልትና ሥጋት ሂደቱን እንዲከታተሉ የጸጥታና የትምህርት ባለሙያዎች የተቀናጀ ድጋፍ እያደረጉ ይገኛሉ።
በዘንድሮው መርሐ ግብርም 30 ሺህ ገደማ የክልሉ ተማሪዎች በፈተናው በመሳተፍ ላይ እንደሆኑ ተገልጿል።
ከትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው፤ የፈተናው መጀመር በክልሉ የሚገኙ ወጣቶች የወደፊት ዕጣ ፈንታ እንዲቃና እና የቋረጡትን ትምህርት በዘላቂነት እንዲቀጥሉ የሚያስችል ትልቅ ማኅበራዊና ሥነ-ልቦናዊ ፋይዳ ያለው ነው።
#ethiopia #ebc #tigraystudents #nationalexam #educationforall

1 month ago
የ2018 ትምህርት ዘመን 12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና በተለያዩ ዙሮች በስኬት እየተካሄደ ነው፡-የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት
**************
የ2018 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና በሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች በተለያዩ ዙሮች በስኬት እየተካሄደ መሆኑን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አስታወቀ።
አገልግሎቱ እንዳመለከተው፣ ፈተናው በአብዛኛው በበይነ መረብ (ኦንላይን) እየተሰጠ ሲሆን፣ ተፈታኞች በስድስት ዙሮች ተከፋፍለው በተሳካ ሁኔታ ፈተናቸውን እየወሰዱ ይገኛሉ።
ሆኖም የተወሰኑ የመሠረተ ልማት ተደራሽነትና የኮምፒውተር እጥረት ባለባቸው አካባቢዎች ፈተናውን በአራት ዙሮች በወረቀት ለመስጠት አስፈላጊው ዝግጅት መደረጉ ተገልጿል።
ከዚሁ ጋር ተያይዞ በትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በበይነ መረብ ለመፈተን ለተመዘገቡ 14 ሺህ 755 ተፈታኞች በስድስቱ ዙር ከሰኔ 23 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ፈተናው እየተሰጠ ይገኛል።
በሌላ በኩል በወረቀት ለመፈተን ለተመዘገቡ 15 ሺህ 325 የክልሉ ተፈታኞች ፈተናው ከሐምሌ 22 እስከ 24 ቀን 2018 ዓ.ም በመቐለ እና በአክሱም ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ እንደሚሰጥ ተመላክቷል።
እነዚህ በወረቀት የሚፈተኑ ተማሪዎች ሐምሌ 20 ቀን 2018 ዓ.ም ወደ መቐለ እና አክሱም ዩኒቨርሲቲዎች በመግባት፣ ሐምሌ 21 ቀን 2018 ዓ.ም የሚሰጠውን ገለጻ (ኦሬንቴሽን) በመከታተል ፈተናቸውን መውሰድ እንደሚችሉ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ጨምሮ ገልጿል።
#ethiopianbroadcastingcorporation #grade12exam #nationalexam #mekelleuniversity #axumuniversity

2 months ago
የ2018 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የሚሰጥበት የጊዜ ሰሌዳ ይፋ ሆነ።
የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የ2018 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የሚሰጥበትን የጊዜ ሰሌዳ ይፋ አድርጓል።
በዚሁ መሠረት በኦንላይን (Computer-based Testing (CBT) የሚፈተኑ ተፈታኞች በስድስት ዙር የሚፈተኑ ሲሆን ከአንደኛ እስከ ሶስተኛ ዙር የተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች ይፈተናሉ። ከአራተኛ እስከ ስድስተኛ ዙር የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች የሚፈተኑ ይሆናል።
ፈተናውን በወረቀት የሚፈተኑ ተፈታኞች የተፈጥሮ ሳይንስ በሶስተኛ ዙር ላይ የሚፈተኑ ሲሆን የማህበራዊ ሳይንስ በአራተኛ ዙር በዩኒቨርሲቲ ውስጥ የሚፈተኑ ይሆናል። (ዝርዝሩን ከላይ በምስሉ ይመልከቱት)
#grade12
#nationalexam
Seledadotio

3 months ago
#grade12
#nationalexam
ከመጪው ሰኔ 24/2018 ዓ/ም ጀምሮ የሚሰጠውን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ለሚወስዱ ተፈታኞች የተዘጋጀ የመፈተኛ ክፍል መግቢያ ካርድ (Admission Card) በፈተና አስተዳደር ሲስተም (https://exam.eaes.et/) ከ03/09/2018 ዓ/ም ጀምሮ ለክልል ትምህርት ቢሮ፣ ለዞን ትምህርት መምሪያዎች እና ለትምህርት ቤት ተወካዮች መለቀቁን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።
አገልግሎት መ/ቤቱ ፦
1. እያንዳንዱ ተፈታኝ ተማሪ በአድሚሽን ካርዱ ጀርባ ላይ የትምህርት ቤቱን ወይም የወረዳው አስተዳደር ትምህርት ጽ/ቤት ማህተም የተደረገበትን አድሚሽን ካርድ ከትምህርት ቤቱ ወስዶ በእጁ መያዝ መያዝ እንዳለበት አሳስቧል።
2. በምዝገባ ወቅት በተፈታኙ ወይም በመዝጋቢው የተከሰተ የትምህርት መስክ ፣ የጾታ ፣ የፎቶ እና መሰል ማስተካከያዎች ካሉ ከግንቦት 30/2018 ዓ.ም በፊት ለትምህርት ቤቱ ማሳወቅና ሂደቱን ጠብቆ መስተካከሉንም ከትምህርት ቤቱ ማረጋገጥ እንደሚገባ ገልጿል።
3. እያንዳንዱ ተፈታኝ አድሚሽን ካርዱን ወደ መፈተኛ ማዕከል ሆነ መፈተኛ ክፍል ለመግባት የሚጠቀምበት በመሆኑ በአግባቡና በጥንቃቄ እንዲይዝ አሳስቧል።
4. ተፈታኞች ፈተና ላይ ከአድሚሽን ካርድ በተጨማሪ የፋይዳ መታወቂያ መያዝ እንደሚጠበቅባቸው ገልጿል።
seledadotio

4 months ago
#nationalexam
#grade12
የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት በ2018 ትምህርት ዘመን 12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የሚዘጋጅባቸውን የትምህርት ዓይነቶችና የክፍል ደረጃዎች ይፋ ማድረጉን የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር እሸቱ ከበደ (ዶ/ር) ገልጸዋል።
በዚሁ መሠረት ፡-
1) ፈተና የሚሰጥባቸው የትምህርት ዓይነቶች
በተፈጥሮ ሳይንስ ፦
- እንግሊዘኛ
- ሒሳብ
- ስኮላስቲክ አፕቲትዩድ
- ባዮሎጂ
- ኬሚስትሪ
- ፊዝክስ
በማህበራዊ ሳይንስ ፦
° እንግሊዘኛ፣
° ሒሳብ፣
° ስኮላስቲክ አፕቲትዩድ፣
° ታሪክ፣
° ጂኦግራፊ
° ኢኮኖሚክስ ናቸው
2) ፈተናው በየትምህርት ዓይነቱ ከ9ኛ ክፍል እስከ 12ኛ ክፍል ያሉትን ሁሉንም ምዕራፎች የሚሸፍን ይሆናል።
የዝግጅት አግባቡም 9ኛ ክፍል ላይ የቀድሞውና የአዲሱ ስርዓተ ትምህርቶች የጋራ ይዘት (Common Contents) ላይ ያተኩራል።
ከ10ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ድረስ ያለው በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት ላይ የተመሠረተ ይሆናል። የኢኮኖሚክስ የትምህርት ዓይነት ግን በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት መሠረት ሆኖ ከ10ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ያለውን የሚሸፍን ይሆናል።
(የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት)

Sponsored by
Surafel
Comments