Logo
Getu Temesgen
⚡️ በግማሽ ዓመት ብቻ ከ266 ሺህ በላይ አዳዲስ ደንበኞች የኤሌክትሪክ ብርሃን አግኝተዋል

​#ethiopia | "ተቋሙ በ6 ወራት ከ52 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ሰብስቧል" - ኢንጂነር ጌቱ ገረመው

​የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ስድስት ወራት ያከናወናቸውን ዋና ዋና ተግባራት ይፋ አድርጓል። ዋና ሥራ አስፈፃሚው ኢንጂነር ጌቱ ገረመው በሰጡት መግለጫ የሚከተሉት ዋና ዋና ውጤቶች ተመዝግበዋል፡-

​✅ አዳዲስ ደንበኞች:
በስድስት ወራት ውስጥ 266,916 አዳዲስ ደንበኞች የኤሌክትሪክ አገልግሎት ያገኙ ሲሆን፤ ይህም ካለፈው ዓመት ጋር ሲነፃፀር የ13.2% ጭማሪ አሳይቷል። አጠቃላይ የደንበኞች ቁጥርም 5.46 ሚሊዮን ደርሷል።

​✅ ገጠር ኤሌክትሪፊኬሽን:
​ከዋናው ቋት (Grid): 47 የገጠር ቀበሌዎች (ከዕቅድ በላይ)፣
​ከፀሐይ ኃይል (Off-grid): 16 ቀበሌዎች፣
​በድምሩ 63 የገጠር ቀበሌዎችና መንደሮች የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ሆነዋል።

​✅ የገቢ አፈጻጸም:
ከተለያዩ አገልግሎቶች 52.26 ቢሊዮን ብር በመሰብሰብ የዕቅዱን 96% ማሳካት ተችሏል።

​✅ መሰረተ ልማት:
አገልግሎቱን አስተማማኝ ለማድረግ ከ52 ቢሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የመሰረተ ልማት ማሻሻያ እና መልሶ ግንባታ ተከናውኗል።
​ተቋሙ የኤሌክትሪክ ተደራሽነትን ለማስፋት እና ጥራቱን ለመጠበቅ እየሰራ መሆኑን ገልጿል።

​#ethiopianelectricutility #eeu #energyaccess #ethiopia #development #infrastructure #power #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን

4 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.