2 months ago
የኢኮኖሚ ሉዓላዊነት በተግባር፡ ከነዳጅ ጥገኝነት ወደ ዘላቂ ታዳሽ ኃይል
***********************
በአሁኑ ወቅት ዓለም አቀፍ የጂኦ-ፖለቲካዊ መናወጦችና ቀውሶች በተለይም የዩክሬንና ሩስያ ጦርነት እንዲሁም በመካከለኛው ምስራቅ የሆርሙዝ ሰርጥ ላይ በተደጋጋሚ የሚጋረጡት የፀጥታ ስጋቶች በነዳጅ አስመጪ ሀገራት ላይ የፈጠሩት የጥገኝነት ፈተና እጅግ የከፋ ሆኖ ታይቷል።
ከእነዚህ እና መሰል ተደራራቢ ዓለም አቀፍ ክስተቶች በመነሳት ኢትዮጵያ የጀመረችው የነዳጅ ጥገኝነትን የመስበር እና ወደ አረንጓዴ ኢኮኖሚ የመሸጋገር ስትራቴጂ ምን ያህል አርቆ አሳቢነት የታከለበት መሆኑ በተግባር እየታየ ነው።
የውጭ ምንዛሬን ጠራርጎ የሚወስደውን እና የሀገር ሀብትን የሚያባክነውን የነዳጅ ድጎማ በግለሰቦች ደረጃ በማስቀረት ሀብቱን ለብዙኃን ትራንስፖርት እና ለዘላቂ ልማት የማዋል ፖሊሲ ተግባራዊ እየተደረገ ነው።
በዚሁ መሠረት ያገለገሉ የነዳጅ ተሽከርካሪዎች ወደ ሀገር እንዳይገቡ እገዳ በመጣል በአንፃሩ በኤሌክትሪክ የሚሠሩ ተሽከርካሪዎች እንዲገቡ የተዘረጋው አሠራር የዚሁ አረንጓዴ ትራንስፖርት ወይም ‘ግሪን ሞቢሊቲ’ ስትራቴጂ ዋነኛ ምሰሶ ነው።
ይህ የታዳሽ ኃይል እና አረንጓዴ ትራንስፖርት ሽግግር በመንግሥት የፖሊሲ ማዕቀፍ ብቻ የተወሰነ ሳይሆን፣ በመሬት ላይ በሚታዩ ግዙፍ የመሠረተ ልማት ሥራዎች ጭምር የታጀበ ነው።
በአዲስ አበባ ከተማ በመከናወን ላይ ያሉት የኮሪደር ልማቶች በተለይም የብስክሌት እና ሰፋፊ የእግረኛ መንገዶች ደረጃውን የጠበቀ የስማርት ከተማ ግንባታ ማሳያ ናቸው።
ከጥራት አንፃርም በሀገራችን ለመጀመሪያ ጊዜ ጥቅም ላይ የዋለው የግራናይት ንጣፍ እና ዘመናዊ መብራቶች ከተማዋን ለነዋሪዎቿ ምቹ ከማድረግ ባለፈ አነስተኛ የካርቦን ልቀት ላለው የትራንስፖርት ሥርዓት ምቹ ምህዳር ፈጥረዋል።
ከዚሁ ጋር ተያይዞ በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ ሥራ የሚገቡት በተፈጥሮ ጋዝ የሚሠሩ የሕዝብ ትራንስፖርት አውቶቡሶች፣ የነዳጅ ጥገኝነትን በዘላቂነት ከመቅረፍ አኳያ ወሳኝ ሚና ይጫወታሉ።
ከኃይል እና ትራንስፖርት ሴክተር ባሻገር ኢትዮጵያ ይህን የተፈጥሮ ሀብት አጠቃቀም ከምግብ ሉዓላዊነት ጋር በማስተሳሰር በመስኖ ልማት እና በግድቦች ግንባታ ያገኘችው ስኬት ሀገራዊ የመቋቋም አቅሟን በእጅጉ አጠንክሮታል።
እነዚህ ሁሉ እርስ በርስ የተሳሰሩ ፕሮጀክቶች፣ ሀገራችን ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር ጠንካራ ኢኮኖሚ እየገነባች መሆኗን ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በተግባር ያረጋገጡ እርምጃዎች ናቸው።
ከአረንጓዴ ዐሻራ እስከ አረንጓዴ ሞቢሊቲ የተስተዋለው ይህ ተጨባጭ እርምጃ ኢትዮጵያን በአፍሪካ ተምሳሌት አድርጎ 32ኛውን የተባበሩት መንግሥታት የአየር ንብረት ጉባኤ (COP32) እንድታስተናግድ የዲፕሎማሲ ድል ያቀዳጃት ነው።
በበረከት ሽመልስ
#ethiopia #greenenergy #cleanenergy #greenmobility #energysovereignty #cop32 #fuel #ebc

u1260u1295u1341u1205 u12a2u1290u122du1302 u1235u12acu1275 u1208u12a0u134du122au12ab u121du1233u120c u12e8u1206u1290u127du12cd u12a2u1275u12eeu1335u12eb
#cleanenergy #pmabiyahmed #ethiopia #africa ","delight_ranges":[],"image_ranges":[],"inline_style_ranges":[],"aggregated_ranges":[],"ranges":[{"entity":{"__typename":"Hashtag","__isEntity":"Hashtag","url":"https://www.facebook.com/h...
በንፁህ ኢነርጂ ስኬት ለአፍሪካ ምሳሌ የሆነችው ኢትዮጵያ
#cleanenergy #pmabiyahmed #ethiopia #africa
2 months ago
u12d3u1208u121d u12a5u12cdu1245u1293 u12e8u1230u1320u12cd u1225u122b
#ethiopia #pmabiyahmed #greenlegacy #cleanenergy ","delight_ranges":[],"image_ranges":[],"inline_style_ranges":[],"aggregated_ranges":[],"ranges":[{"entity":{"__typename":"Hashtag","__isEntity":"Hashtag","url":"https://www.facebook.com/h...
ዓለም እውቅና የሰጠው ሥራ
#ethiopia #pmabiyahmed #greenlegacy #cleanenergy
Sponsored by
Surafel
2 months ago
u12d3u1208u121du1295 u12ebu1235u1308u1228u1218u12cd u12a0u123bu122bu127du1295
#cleanenergy #greenlegacy #ethiopia ","delight_ranges":[],"image_ranges":[],"inline_style_ranges":[],"aggregated_ranges":[],"ranges":[{"entity":{"__typename":"Hashtag","__isEntity":"Hashtag","url":"https://www.facebook.com/h...
ዓለምን ያስገረመው አሻራችን
#cleanenergy #greenlegacy #ethiopia
2 months ago
የኢትዮጵያ እና የአሜሪካ የኃይል ዘርፍ ትብብር
******************
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የሀገሪቱን የኢነርጂ ዘርፍ ወደ ላቀ የዲጂታል እና የዘመናዊነት ምዕራፍ ለማሸጋገር ያለመ ወሳኝ ውይይት ከአሜሪካ መንግሥት ከፍተኛ ልዑካን ጋር አካሂዷል።
ውይይቱ የተካሄደው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኢንጂነር ጌቱ ገረመው፣ በአሜሪካ መንግስት ምክትል ረዳት ፀሐፊ ሚስተር ማርክ ትራውንተር ሚቼል የተመራውን ልዑክ በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው ባነጋገሩበት ወቅት ነው።
በምክክሩ ላይ የኤሌክትሪክ ስርጭት አውታር መረብን (Grid) ማዘመን፣ የዲጂታል ሽግግርን ማፋጠን፣ ስማርት ቆጣሪዎችን ማስፋፋት፣ ንጹህ ኢነርጂን ማልማት እና የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን (EVs) ማበረታታት ዋነኛ አጀንዳዎች ነበሩ። ከዚህም በተጨማሪ ያልተነኩ የኢንቨስትመንት አማራጮች እና የአቅም ግንባታ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ትኩረት ተሰጥቶባቸዋል።
ኢንጂነር ጌቱ ገረመው በውይይቱ ወቅት፣ ተቋማቸው ለደንበኞች ምቹ፣ ጠንካራ እና ዘመናዊ አገልግሎት ለመስጠት ፈጠራንና ቴክኖሎጂን አቅፎ በቁርጠኝነት እየሰራ ይገኛል ብለዋል።
አክለውም በኢትዮጵያ እና በአሜሪካ መካከል ያለው የረጅም ዓመታት ታሪካዊ ግንኙነት ወደ ተጨባጭ የልማት ፕሮጀክቶች እንደሚሸጋገር ያላቸውን ጽኑ እምነት መግለጻቸውን ከአገልግሎቱ የተገኘው መረጃ አመልክቷል።
ሚስተር ማርክ ትራውንተር ሚቼል እና ልዑካን ቡድናቸው በበኩላቸው፤ በኢትዮጵያ የኢነርጂ ዘርፍ እየተከናወኑ ያሉ የዘመናዊነት እርምጃዎችን አድንቀው፣ የሀገሪቱን የኃይል ዘርፍ አስተማማኝነት ይበልጥ ለማጠናከር በጋራ ለመስራት ያላቸውን ዝግጁነት አረጋግጠዋል።
ይህ የሁለቱ ሀገራት ስትራቴጂያዊ አጋርነት የኤሌክትሪክ ተደራሽነትን በማስፋፋት የሀገሪቱን ኢኮኖሚያዊ እድገትና የኢንዱስትሪ ሽግግር በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚደግፍ ተጠቁሟል።
#ethiopia #ethiopianelectricutility #energysector #cleanenergy #usethiopia

6 months ago
📢 አዲስ አገልግሎት በአዲስ መንፈስ! - እንኳን ደስ አላችሁ🔋
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የኤሌክትሪክ ተሸከርካሪ ተጠቃሚዎችን እርካታ ለማሳደግ 24 ሰዓት የሚሰሩ #ቻርጅ_ማድረጊያ_ጣቢያዎችን በከፍተኛ መዋለ ንዋይ በመገንባት ለአገልግሎት ዝግጁ ማደረጉን በደስታ ይገልፃል፡፡
🚗 የኤሌክትሪክ ቻርጅ ማድረጊያ ጣቢያዎቹ የት ይገኛሉ❓
✨ ኮተቤ – ከማዕድን ሚኒስቴር ፊት ለፊት
✨ ፒያሳ – ኤሌክሪክ ህንፃ ግቢ ውስጥ | በቀድሞው የአገልግሎቱ ዋና መሥሪያ ቤት
💵 የአገልግሎት ክፍያ
🖍️ የኤሌክትሪክ ኃይል አጠቃቀም ባህልን ለማሻሻልና ከፍተኛ የኃይል ጭነት በማይኖርበት ጊዜ ደንበኞች ኃይል እንዲጠቀሙ ለማበረታታት
🖌️ በሚጠቀሙበት ጊዜ ላይ መሰረት ያደረገ ምክንያታዊ የቻርጅ ማድረጊያ ዋጋ እንዲተገበር ተደርጓል፡፡
🚘 ለአገልግሎቱ ተጠቀሚዎች ለአንድ ኪሎ ዋት ሶስት የክፍያ ዋጋ አማራጮች ቀርቧል፡-
☑️ Off-Peak:- (10:00፡01 PM - 6:00፡00 AM - ከምሽቱ 4:00 እስከ ጠዋቱ 12:00 ድረስ) - 14.85 ብር
☑️ Shoulder: - (10:00፡01 AM-5 - :00፡00 PM - ከጠዋቱ 4:00 አስከ ቀኑ 11:00 ድረስ) - 16.57 ብር
☑️ On-Peak: - (5:00፡01 PM – 10:00፡00 PM & 6:01AM - 10:00AM - ከቀኑ 11፡00 እስከ ምሽቱ 4፡00 እንዲሁም ከጠዋቱ 12፡00 እስከ 4:00 ድረስ) - 18.28 ብር
⚠️ልብ ይበሉ - የተዘጋጀው የቻርጅ ማድረጊያ ዋጋ ደንበኞች የኃይል ጭነት በማይኖርበት ጊዜ በዝቅተኛ ዋጋ ቻርጅ በማድረግ ገንዘባቸውን #እንዲቆጥቡ የሚያስችል ነው፡፡
#cleanenergy #poweryourjourney #eeu #ultrafast #driveclean #charge_green_drive_clean” #smart_power_for_smart_mobility”
#ethiopianelectricutility 🚗⚡️

Comments